Advertisements

መጽሐፍ ቅዱስ እየፈረደላችሁ ወይስ እየፈረደባችሁ ክፍል አንድ

0
0

Advertisements

1497 days ago, 1859 views
አንድበመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት ባህርን መሻገር ማለት ምን ማለት ነው? የእግዚአብሔርን ቃል ከሚያጣጥሉና ለማጣመም ብዙ ትግል ከሚያደርጉ ሐይማኖተኞች እንድሚከተለው አይነት አባባልና አረዳድ እንዳለ ብዙ ሰምታችሁሃል፤ ሰምተናልም። ኢየሱስ ከአለም ፍፃሜ በሇላ አምላክ ብቻ ነዉ ወይስ ፍፁም ሰዉ ፍፁም አምላክ ??????? ፍፁም ሰዉ ፍፁም አምላክ ከሆነ ለምን ?????አሁንስ በሰማይ ፍፁም ሰዉ ነዉ ወይስ ፍፁም አምላክ ብቻ ????? ለምን ?????? አምላክ በላ ጠጣ ተኛ አንቀላፋ ደከመ አለቀሰ አላዋቂ ሆነ (ይህ ውሸት ነው? ኢየሱስ አላዋቂ አልሆነም፤ አይደለምም! )ስንል አምላክን ክብሩን አንነካዉም ወይ ???? ኢየሱስ መተኛቱ መራቡ ማንቀላፋቱ ማልቀሱ ምንም ማድረግ አለመቻሉ ሁሉን አዋቂ አለመሆኑ መጠማቱ በተፈጥሮ ቁጥጥር ስር ያለ ፍጡር አያረገዉም ወይ ???? ታዲያ ይህ የፍጡር ባህርይ ካልሆነ ምን ሊሆን ይችላል ???አንድ ሰዉ ሲርበዉ ካልበላ ይሞታል ፡፡ ኢየሱስም ተርቧል ፡፡ ምግብ ባያገኝ መሞቱ ይቀራልን ??? ለፍጡር ዉሀ ያስፈልገዋል ለመኖር ፡፡ ኢየሱስም ተጠምቷል ዉሀ ባይጠጣ ሊሞት ነዉን ???ደክሟል ድካም አንዱ የፍጡር ባህርይ ነዉ ፡፡ ታዲያ ኢየሱስ ምነዉ ፈጣሪ ከሆነ ከተፈጥሮ በላይ መሆን አቃተዉ???ኢየሱስ ይሰግድ ነበር ብቻዉን ሲፀልይ ሲያመልክ ያዉም ብቻዉን ያድር ነበር ፡፡ ይሄም አምላክ ላለመሆኑ ማስረጃ አይሆንምን ??? ፍፁም ሰዉ ፍፁም አምላክ የሚለዉስ በዉኑ ያስኬዳልን ? ነፃ አይምሮስ ይቀበለዋልን ??ፍፁም ሰዉ ነዉ ስትል ፍፁም አምላክ መሆኑን እየተቃወምክ ነዉ፡፡ ፍፁም አምላክም ነዉ ስትል ፍፁም ሰዉ ነዉ የሚለዉን እያፈረስከዉ ነዉ፡፡ ለምሳሌ አንድ ቀለም ፍፁም ነጭ ፍፁም ጥቁር ነዉ ቢባል ያስኬዳልን ??? ለመሆኑ እደነዚህ አይነቶች የአጉል ሐይማኖት ተከታዮች ስለ ምን እንደሚናገሩ ያውቃሉ? የመጽሐፍ ቅዱስስ መሰረታዊ እውቀት አላቸውን? መረዳታቸውስ ምን ያህል ነው? እንደሚናውቀው መጽሐፍ ቅዱስ እንኳን ለማያውቁትንና በሰነ መለኮት ትምህርት ዘመናቸውን ላሳለፉትና አውቀነዋል የሚሉት ብዙ የመረዳት ችግር እንዳለባቸው ስንመለከት ቆይተናል። ታዲያ እንዲህ አይነቱ ብደግ ብለው በሃይማኖትና ወግ እንድሁም ሰርዓት ቅናት ተቃትጥለው የእግዚአብሔርን ቃል አንስተው እግዚአብሔር እንድህ ብሎ ያስተምራል ለሚሉት ምን መልስ ለምስጠት ተዘጋጅታችሃል? እኛ ራሳቸን ለመማርና ለማዎቅ ዝግጅዎች ነን ወይ? ለዛሬው በጌታችንና በመዳህኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዙሪያ ስላነሱት ጉዳይ እጥር ያለ መልስ ለመስጠት እፈልጋለሁ። ባለፈው ጊዜ ጌታ ኢየሱስ ተርቦ በነበረበት ጊዜ በለሲትን እንደረገማት ያችም በለስ እስራኤል እንደምትወክል ከጽሐፍ ቅዱስ ሰፋ አድርግን አይተናል ዛሬ ደግሞ 'ኢየሱስ ተኛ" እያሉ ብዙ ሰልሚነጋገሩበት ጉዳይ እንመለከታለ። መልሱንም ከምስጠቴ በፊት ሐሳቡን በደንብ እንድንረዳው መሰረታዊ ጥያቅቅዎችን ለመጠየቅ እፈልጋለሁ። 1ኛ. በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት ባህርን መሻገር ማለት ምን ማለት ነው?መንፈሳዊ ትርጉም አለው? ካለውስ ትርጉሙ ምንድን ነው? 2ኛ. ለምን ጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባህሩን እንሻገር አላቸው? ከየት ወደ የትስ ነው የሚሻገሩት? 3ኛ. ለምንስ ጌታ ኢየሱስ በመረቡ ውስጥ ተኛ? ለምን መተኛት አስፈልገው? እግዚአብሔር ምን ሊያስተምረን ፈልጎ ነው? 4ኛ. ከእቅልፍ መነሳቱ ምንን ያሳያል? ከተነሳስ በሁዋላ ምን አደረገ? ነፋሱና ወጀቡ፤ እንዲሁም ማእበሉስ ምንን ይወክላል? 6ኛ. ባህሩን ከተሻገሩ በሁዋላ ኢየሱስ ክርስቶስሽና ደቀመዛምሩት የሄዱበት አገር ማን ይባላል? ምንስ አገኙ? ጌታ ኢየሱስ ምን አደርገ? ከዚህ ምን እንማራላን? 5ኛ.ነፋሱና ወጀቡ፤ እንዲሁም ማእበሉ ሲታዘሉትና ሲገዙለት እነዝህ ሐይማኖተኞች እንድሚሉት ጌታ ኢየሱስ ከተፈጥሮ በላይ ወይስ ከተፈጥሮ በታች መሆኑን ያሳያል? ለምን? የማቴዎስ ወንጌል 8፥27  ሰዎቹም፦ ነፋሳትና ባሕርስ ስንኳ የሚታዘዙለት፥ ይህ እንዴት ያለ ሰው ነው? እያሉ ተደነቁ። የማርቆስ ወንጌል 4፥41  እጅግም ፈሩና፦ እንግዲህ ነፋስም ባሕርም የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው? ተባባሉ። የሉቃስ ወንጌል 8፥25  እርሱም፦ እምነታችሁ የት ነው? አላቸው። ፈርተውም ተደነቁ፥ እርስ በርሳቸውም፦ እንዲህ ነፋሳትንና ውኃን እንኳ የሚያዝ ለእርሱም የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው? አሉ። የማርቆስ ወንጌል  4:35-41 በዚያም ቀን በመሸ ጊዜ፦ ወደ ማዶ እንሻገር አላቸው።   ሕዝቡንም ትተው በታንኳ እንዲያው ወሰዱት፥ ሌሎች ታንኳዎችም ከእርሱ ጋር ነበሩ። ብርቱ ዐውሎ ነፋስም ተነሣና ውኃ በታንኳይቱ እስኪሞላ ድረስ ማዕበሉ በታንኳይቱ ይገባ ነበር። እርሱም በስተኋላዋ ትራስ ተንተርሶ ተኝቶ ነበር፤ አንቅተውም፦ መምህር ሆይ፥ ስንጠፋ አይገድህምን? አሉት። ነቅቶም ነፋሱን ገሠጸው ባሕሩንም፦ ዝም በል፥ ፀጥ በል አለው። ነፋሱም ተወ ታላቅ ፀጥታም ሆነ። እንዲህ የምትፈሩ ስለ ምን ነው? እንዴትስ እምነት የላችሁም? አላቸው።   እጅግም ፈሩና፦ እንግዲህ ነፋስም ባሕርም የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው? ተባባሉ። የሉቃስ ወንጌል  8:22-32   ከዕለታቱም በአንዱ እርሱ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ታንኳ ገብቶ፦ ወደ ባሕር ማዶ እንሻገር አላቸው፤ ተነሡም።   ሲሄዱም አንቀላፋ። ዓውሎ ነፋስም በባሕር ላይ ወረደ፥ ውኃውም ታንኳይቱን ይሞላ ነበርና ይጨነቁ ነበር።   ቀርበውም፦ አቤቱ፥ አቤቱ ጠፋን እያሉ አስነሡት። እርሱም ነቅቶ ነፋሱንና የውኃውን ማዕበል ገሠጻቸው፤ ተዉም፥ ጸጥታም ሆነ።   እርሱም፦ እምነታችሁ የት ነው? አላቸው። ፈርተውም ተደነቁ፥ እርስ በርሳቸውም፦ እንዲህ ነፋሳትንና ውኃን እንኳ የሚያዝ ለእርሱም የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው? አሉ።   በገሊላም አንጻር ወዳለችው ወደ ጌርጌሴኖን አገር በታንኳ ደረሱ።   ወደ ምድርም በወጣ ጊዜ አጋንንት ያደሩበት አንድ ሰው ከከተማ ወጥቶ ተገናኘው፥ ከብዙ ዘመንም ጀምሮ ልብስ ሳይለብስ በመቃብር እንጂ በቤት አይኖርም ነበር።   ኢየሱስንም ባየ ጊዜ ጮኾ በፊቱ ተደፋ በታላቅ ድምፅም፦ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? እንዳትሣቀየኝ እለምንሃለሁ አለ።   ርኵሱን መንፈስ ከሰውዬው እንዲወጣ ያዘው ነበርና። ብዙ ዘመንም ይዞት ነበርና፥ በሰንሰለትና በእግር ብረትም ታስሮ ይጠበቅ ነበር፤ እስራቱንም ሰብሮ በጋኔኑ ወደ ምድረ በዳ ይነዳ ነበር።   ኢየሱስም፦ ስምህ ማን ነው? ብሎ ጠየቀው። እርሱም ብዙዎች አጋንንት ገብተውበት ነበርና፦ ሌጌዎን አለው።   ወደ ጥልቁም ሊሄዱ እንዳያዛቸው ለመኑት።   በዚያም በተራራው የብዙ እሪያ መንጋ ይሰማሩ ነበር፤ ወደ እነርሱም ሊገቡ እንዲፈቅድላቸው ለመኑት፤ ፈቀደላቸውም።   አጋንንትም ከሰውዬው ወጥተው ወደ እሪያዎች ገቡ፥ መንጋውም ከአፋፉ ወደ ባሕር ተጣደፉና ሰጠሙ። መጽሐፍ ቅዱስን ስንመረምረው ብዙ ስለ ባህርና ባህርን ስለሻገር ብዙ ነገር ያስተምረናል። እስራኤላዊያን በግብጽ ባርነት ለ400 ዓመታት ከተግዙ በሁዋላ ነጻ ለመውጣት ሲነሱ መጀመሪያ ያጋጠባቸው በጣም አስቸጋሪው ነገር ቢኖር በፊታቸው ተደቅኖ የነበረው የቀይ ባህር ነው። ቀይ ባህርን የግድ መሻገር ነበረባቸው አለበለዚያ ግን ከባርነት የመውጣት ሕልማቸው ፈጽሞ ያከትም ነበር። እግዚአብሔር ባህሩን መክፍል ነበረበት፤አደረገውም ክብር ለስሙ ይሆንና! እስራኤላዊያን 40ዎቹን አመታት ከተጉዋዙ በሁላ ወደ ትሰፋይቱ ምድር ለመግባት በቀረቡ ጊዜ ዮርዳኖስ ተደቅኖ ጠበቃቸው። ዮርዳኖስም ካልተከፈለ መሻገር ፍጹም አይታለምም ስለዚህ አምላካችን በብርቱ ክንዱ ዮርዳኖስን መክፈል ነበረበረበት። እግዚአብሔርም ዮርዳኖስን ከፈለው ህዝቡም በድል ተሻገሩ የተስፋይቱንም ምድር ወረሱ። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚል ብርቱ የእግዚአብሔር ነብይ የነበረው ኤልያስ ወደ ሰማይ ከመነጠቁ በፊት ባህሩን መሻገር ነበረበት። ባህሩም በፊቱ ጽንቶ ከመሻገር በከለከልው ጊዜ የጽድቅ ምልክት የሆነውን መጎናጸፊያውን አንስቶ በመምታትና በመሰነጣተቁ ኤልያስና ኤልሳ ሊሻገሩ ችለዋል። ከዚያም በሁዋላ ኤልያስ ወደ ዘላለም ቤቱ ወደ መንግስተ ሰማያት በክብር እንደተነጠቀ እንማራላን። እነዚህንና እነዚህን ከሚመሳስሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ስንመለክት እንድሁም " ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ ምበምለው የመጽሔፍ አጠናን ስልት ስንመለከትው እግዚአብሄር ብዙ ነገር ሊያስተምረን እንደወደደ እናያለን ወይም እንረዳለን። በተጨማሪም በመጨረሻው ዘመን ይህ ባህር በከፍተኛ ደረጃ እንደሚናወጥና አውረዎችም ከዚህ ባህር እንድመወጡና ብዞውችን እንደሚበሉ እግዚአብሔር በነብዩ ዳንኤል በኩል እንዲህ አስተጥንቅቆ ይናገረናል   ዳንኤልም ተናገረ እንዲህም አለ፦ በሌሊት በራእይ አየሁ፤ እነሆም፥ አራቱ የሰማይ ነፋሳት በታላቁ ባሕር ላይ ይጋጩ ነበር።   አራትም ታላላቅ አራዊት ከባሕር ወጡ፥ እያንዳንዲቱም ልዩ ልዩ ነበረች።   መጀመሪያይቱ አንበሳ ትመስል ነበር፥ የንስርም ክንፍ ነበራት፤ ክንፎችዋም ከእርስዋ እስኪነቀሉ ድረስ አይ ነበር፥ ከምድርም ከፍ ከፍ ተደረገች፥ እንደ ሰውም በሁለት እግር እንድትቆም ተደረገች፥ የሰውም ልብ ተሰጣት።ትንቢተ ዳንኤል  7:2-6   እነሆም፥ ሁለተኛይቱ ድብ የምትመስል ሌላ አውሬ ነበረች፥ በአንድ ወገንም ቆመች፥ ሦስትም የጐድን አጥንቶች በአፍዋ ውስጥ በጥርስዋ መካከል ነበሩ፤ እንደዚህም፦ ተነሥተሽ እጅግ ሥጋ ብዪ ተባለላት።   ከዚህም በኋላ፥ እነሆ፥ ነብር የምትመስል በጀርባዋም ላይ አራት የወፍ ክንፎች የነበሩአት ሌላ አውሬ አየሁ፤ ለአውሬይቱም አራት ራሶች ነበሩአት፥ ግዛትም ተሰጣት በነብዩ በዳንኔል ላይ የተገለጽውን ጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኢንዲህ ሲል በመጨረሻው ዘመን ሰለሚሆነውና ሰልሚያስፈራው ነገር ከባህሩና ከሞገዱ መትመም ጋር አያይዞ እንድህ ያስጠነቅቀናል።የሉቃስ ወንጌል 21፥25 በፀሐይና በጨረቃም በከዋክብትም ምልክት ይሆናል፤ በምድር ላይም አሕዛብ ከባሕሩና ከሞገዱም ድምፅ የተነሣ እያመነቱ ይጨነቃሉ

Advertisements

Advertisements

Advertisements