Advertisements

አሏህ እና መሐመድ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ክፍል 3 (ማብራሪያውን ያብቡት)

0
0

Advertisements

1727 days ago, 1566 views
አሏህ እና መሐመድ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ክፍል 3 (ማብራሪያውን ያብቡት) ኦሪት ዘዳግም 18:18-20 ከወንድሞቻቸው መካከል እንደ አንተ ያለ ነቢይ አስነሣላቸዋለሁ ቃሌንም በአፉ አደርጋለሁ፥ ያዘዝሁትንም ቃል ሁሉ ይነግራቸዋል፤ በስሜም የሚናገረውን ቃሌን የማይሰማውን ሰው እኔ እበቀልለታለሁ። ነገር ግን ይናገር ዘንድ ያላዘዝሁትን በስሜ በድፍረት የሚናገር ወይም በሌላ አማልክት ስም የሚናገር ነቢይ፥ እርሱ ይገደል። የሐዋርያት ሥራ 3:15-26 የሕይወትንም ራስ ገደላችሁት፤ እርሱን ግን እግዚአብሔር ከሙታን አስነሣው፥ ለዚህም ነገር እኛ ምስክሮች ነን። በስሙም በማመን ይህን የምታዩትንና የምታውቁትን የእርሱ ስም አጸናው፥ በእርሱም በኩል የሆነው እምነት በሁላችሁ ፊት ይህን ፍጹም ጤና ሰጠው። አሁንም፥ ወንድሞቼ ሆይ፥ እናንተ እንደ አለቆቻችሁ ደግሞ ባለማወቅ እንዳደረጋችሁት አውቄአለሁ፤ እግዚአብሔር ግን ክርስቶስ መከራ እንዲቀበል አስቀድሞ በነቢያት ሁሉ አፍ የተናገረውን እንዲሁ ፈጸመው። እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ፥ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም። እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ የተናገረው፥ ነገር ሁሉ እስከሚታደስበት ዘመን ድረስ ሰማይ ይቀበለው ዘንድ ይገባልና። ሙሴም ለአባቶች፦ ጌታ አምላክ እኔን እንዳስነሣኝ ነቢይን ከወንድሞቻችሁ ያስነሣላችኋል፤ በሚነግራችሁ ሁሉ እርሱን ስሙት። ያንም ነቢይ የማትሰማው ነፍስ ሁሉ ከሕዝብ ተለይታ ትጠፋለች አለ። ሁለተኛም ከሳሙኤል ጀምሮ ከእርሱም በኋላ የተናገሩት ነቢያት ሁሉ ደግሞ ስለዚህ ወራት ተናገሩ። እናንተ የነቢያት ልጆችና እግዚአብሔር ለአብርሃም፦ በዘርህ የምድር ወገኖች ሁሉ ይባረካሉ ብሎ፥ ከአባቶቻችን ጋር ያደረገው የኪዳን ልጆች ናችሁ። ለእናንተ አስቀድሞ እግዚአብሔር ብላቴናውን አስነሥቶ፥ እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ እየመለሰ ይባርካችሁ ዘንድ፥ ሰደደው። የዮሐንስ ወንጌል 8:21-24 ኢየሱስም ደግሞ፦ እኔ እሄዳለሁ ትፈልጉኛላችሁም በኃጢአታችሁም ትሞታላችሁ እኔ ወደምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም አላቸው። አይሁድም፦ እኔ ወደ ምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም ማለቱ ራሱን ይገድላልን? እንጃ አሉ። እናንተ ከታች ናችሁ፥ እኔ ከላይ ነኝ፤ እናንተ ከዚህ ዓለም ናችሁ፥ እኔ ከዚህ ዓለም አይደለሁም። እንግዲህ፦ በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ አልኋችሁ፤ እኔ እንደሆንሁ ባታምኑ በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁና አላቸው። አሏህ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኢየሱስ መስቀል ላይ ሆኖ አሏህ ነው የጠራው ይላሉ ዶር ዛኪር። እውነት አሏህ የሚለው ቃል መጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛልን? ጌታ ኢየሱስ በመቀል ላይ በተሰቀለበት ወቅት የጠራው 'አሏህ አሏህ' ብሎ ነውን? የማቴዎስ ወንጌል 27:46 በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ፦ ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህም፦ አምላኬ አምላኬ፥ ስለ ምን ተውኸኝ? ማለት ነው። የማርቆስ ወንጌል 15:34 በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ፦ ኤሎሄ፥ ኤሎሄ፥ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ ትርጓሜውም አምላኬ፥ አምላኬ፥ ለምን ተውኸኝ? ማለት ነው። እስቲ አላህ የሚለውን ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውጽት እንመለከት! ትርጉሙስ ምን ይሆን? 1. አላህ ማለት መርገም ማለት፤ የተረገመ ማለት ነው። አፉ መርገምንና ሽን( אָלָה )ን ገላን ተንኰልን የተመላ ነው፤ ከምላሱ በታች ጉዳትና መከራ ነው። መዝሙረ ዳዊት 10:7 2. አላህ ማለት መርገም ወይም የተረገመ ማለት ነው። ዘሑልቁ 5፡23 ካህኑም እነዚህን መርገሞች ( አላሆች(אָלָה) ወትይም መርገሞች ) በሰሌዳ ይጽፈዋል፥ በመራራውም ውኃ ይደመስሰዋል 3. አላህ ማለት መርገም ወይም የተረገመ ማለት ነው። አምላክህም እግዚአብሔር ይህችን መርገም(אָלָה) ሁሉ በጠላቶችህና በሚጠሉህ በሚያሳድዱህም ላይ ያመጣታል ኦሪት ዘዳግም 30:7 ስለዚህ ሙስሊሞች ወገኖቼ ሁሉ አትሳሳቱ አሏህ በመጽሀፍ ቅዱስ አለ ካላችሁ የተረገመ ነው ማለታችሁ እንደሆነ እውቁ! ማስተዋል ጥሩ ነው።

Advertisements

Advertisements

Advertisements