Advertisements

የእስልምና አስተማሪዎች ኢየሱስን ለማወቅ ያደረጉት ትግልና ያገኙት ውጤት! እናንተስ?

0
0

Advertisements

1867 days ago, 2694 views
የእስልምና አስተማሪዎች ኢየሱስን ለማወቅ ያደረጉት ትግልና ያገኙት ውጤት! እናንተስ? መልካም ባልሆነው መንገድ፥ አሳባቸውን እየተከተሉ፥ ወደሚሄዱ ወደ ዓመፀኛ ሕዝብ ቀኑን ሁሉ እጆቼን ዘረጋሁ።ትንቢተ ኢሳይያስ 65:2 እግዚአብሄር በነብዩ በኢሳያስ አልፎ ከብዙ ሽህ አመታት በፊት አስቀድሞ እንደተናገርወ በራሱ ስርዓትና ሐይማኖት ለሚኖር ሕዝብ የምህርትና የቸርነት በሩን ከፍቶ እነሆኝ ወደ እኔ ኑ እኔም አድናችሁሃለኑና አስተምራቹሃለሁ በማለት እጁን ዘረጋልን ግን ስንቱ የእርሱን መንገድ ይፈልጋል? ስንቱ እግዚአብሔርን ለማወቅና የምህረቱን ስጦታ ይቀበላል? ዛሬ በአለምናችን በተለያየ እምነትና ስራዓት ውስጥ የሚገኙ ግለሰቦች አጥብቀው ይፈልጉታል። ለዛሬም የምናየው ቪዲዮ የሚመሰክረው ይህን ነው። በተለያየ የአለም ክፍል እና በተለያየ የሕይወት ደረጃ ላይ የሚገኙ ሙስሊሞች ወደ ክርስቶስ ያደረጉትን ጥረትና በጥረታቸውም የዘላለምን ሕይወት ማግኘታቸውን በእርግጠኝነት ይናገራሉ። ከፈጣሪያቸው ጋርም መታረቃቸውንና ሕብረት መጀመራቸውን ያብራሩልናል። ዛሬ ይህን ቪዲዮ የምትመለከቱ በተለያየ ሐይማኖት ውስጥ የምትገኙ ሁሉ እንድታስቡበትና ወደ እውነተኛው አምላክ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንድትመጡ ጥሪ አቀርባለሁ። ምክኒያቱም መዳን በሌላ በማንም የለምና ልንድንበት የተሰጠን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ አበክሮ ይናገራል። በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና። በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል። ብርሃንም ወደ ዓለም ስለ መጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለ ወደዱ ፍርዱ ይህ ነው። ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፥ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤ እውነትን የሚያደርግ ግን ሥራው በእግዚአብሔር ተደርጎ እንደ ሆነ ይገለጥ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል።ዮሐንስ ወንጌል 3:16-21 ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም:: ዮሐንስ ወንጌል 14:6 መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።የሐዋርያት ሥራ 4:12 አዎ እኛም እንመሰክራለን መዳን በሌላ በማንም የለም ነገር ግን እውነተኛው መዳኛ እውነት መንገድ ሕይወትም የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። ዛሬ እጁን ዘረቶ ኑ ወደ እኔ ሲልም እምቢ አሻፈረን ብንል ጊዜው ያልፍና ወደ ዘላለም ፍርድ እራሳችን ወርውረን እናገኛለን። ስለዚ ወደ ኢየሱስ ኑና ዳኑ።

Advertisements

Advertisements

1000 chars left
Showing 1 to 5 of 5 comments.
Amos21 - 1865 days ago
Many people ask me who I am and to what denominations I belong to and to what sort of religous group I belong to? What I can say is I am a Christian who believes in the word of almighty God. As the Bible says that 'The righetous llives by faith", I do strongly believe I live by the faith of the word of God. I don't belong to any denomination nor do I want to. I don't affilate to any religous group and nor do I want to. being a Christian is more than enough for me.
commenter - 1866 days ago
እኔ ክርስትያን ነኝ
commenter - 1867 days ago
first who are you? what is your denomination? which religion you belong to?
commenter - 1867 days ago
ante rasih awkehewal. ene ende saul timeslegnaleh.lerasih kibir kalkomk beker yihenin anib 1koro 11:3, 1 koro 15:28, raei 3:2
efeson 1:3, 2 koro 1:3, etc etc
Amos21 - 1867 days ago
መልካም ባልሆነው መንገድ፥ አሳባቸውን እየተከተሉ፥ ወደሚሄዱ ወደ ዓመፀኛ ሕዝብ ቀኑን ሁሉ እጆቼን ዘረጋሁ።ትንቢተ ኢሳይያስ 65:2

እግዚአብሄር በነብዩ በኢሳያስ አልፎ ከብዙ ሽህ አመታት በፊት አስቀድሞ እንደተናገርወ በራሱ ስርዓትና ሐይማኖት ለሚኖር ሕዝብ የምህርትና የቸርነት በሩን ከፍቶ እነሆኝ ወደ እኔ ኑ እኔም አድናችሁሃለኑና አስተምራቹሃለሁ በማለት እጁን ዘረጋልን ግን ስንቱ የእርሱን መንገድ ይፈልጋል? ስንቱ እግዚአብሔርን ለማወቅና የምህረቱን ስጦታ ይቀበላል? ዛሬ በአለምናችን በተለያየ እምነትና ስራዓት ውስጥ የሚገኙ ግለሰቦች አጥብቀው ይፈልጉታል። ለዛሬም የምናየው ቪዲዮ የሚመሰክረው ይህን ነው። በተለያየ የአለም ክፍል እና በተለያየ የሕይወት ደረጃ ላይ የሚገኙ ሙስሊሞች ወደ ክርስቶስ ያደረጉትን ጥረትና በጥረታቸውም የዘላለምን ሕይወት ማግኘታቸውን በእርግጠኝነት ይናገራሉ። ከፈጣሪያቸው ጋርም መታረቃቸውንና ሕብረት መጀመራቸውን ያብራሩልናል። ዛሬ ይህን ቪዲዮ የምትመለከቱ በተለያየ ሐይማኖት ውስጥ የምትገኙ ሁሉ እንድታስቡበትና ወደ እውነተኛው አምላክ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንድትመጡ ጥሪ አቀርባለሁ። ምክኒያቱም መዳን በሌላ በማንም የለምና ልንድንበት የተሰጠን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ አበክሮ ይናገራል።

በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።

ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና።

በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል።

ብርሃንም ወደ ዓለም ስለ መጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለ ወደዱ ፍርዱ ይህ ነው።

ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፥ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤

እውነትን የሚያደርግ ግን ሥራው በእግዚአብሔር ተደርጎ እንደ ሆነ ይገለጥ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል።ዮሐንስ ወንጌል 3:16-21
ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም:: ዮሐንስ ወንጌል 14:6

መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።የሐዋርያት ሥራ 4:12
አዎ እኛም እንመሰክራለን መዳን በሌላ በማንም የለም ነገር ግን እውነተኛው መዳኛ እውነት መንገድ ሕይወትም የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። ዛሬ እጁን ዘረቶ ኑ ወደ እኔ ሲልም እምቢ አሻፈረን ብንል ጊዜው ያልፍና ወደ ዘላለም ፍርድ እራሳችን ወርውረን እናገኛለን። ስለዚ ወደ ኢየሱስ ኑና ዳኑ።

Advertisements