ጌታነህ ግብ አስቆጠረ….”ዛሬ ዋልያዉ ማሸነፍ አለበት!!!” መልካም እድል!!!

IMG_3581

ብሎምፎንቴን ሴልቲክ ጌታነህ ከበደ ደቡብ አፍሪካ እንደመጣ ለሙከራ የሄደበት ክለብ ነበር፡፡የብሂራዊ ቡድኑም በቻን ዉድድር ልምምድ የሚሰራዉ በዚህ ሜዳ ላይ ነዉ፡፡ዛሬ ረፋዱን ጌታነህ የሚጫወትበት ክለብ ቢድ ዊትስ ከ ብሎምፎንቴን ሴልቲክ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ አድርግዋል፡

ጌታነህ ከበደ በዚህ ጨዋታ ግብ አስቆጥርዋል፡፡ጨዋታዉን 3ለ2 ተሸንፈዋል፡፡ከጨዋታዉ በኋላ ጌታነህን በስልክ አገኘሁት፡-

ማሸነፍ ነበረብን፡-የወዳጅነት ሆነ የነጥብ እዚህ ሀገር ሁሉም ከባድ ጨዋታ ነዉ፡፡ሁሉንም ማሸነፍ ነዉ የሚጠበቅብህ ብልዋል፡፡

ጌታነህ ልቡ ከዋልያዉ ጋር ነዉ፡፡መምጣት ባይችልም አሰላለፍ ደዉሎ ይጠይቃል በየቀኑ አዳዲስ ነገሮችን ለመስማትም ይሞክራል፡፡ምክሩንም እየለገሰ ነዉ፡፡”ዛሬ ማሸነፍ ግዴታ ነዉ፡፡እኔ ባለሁበትም ሀሆነ ሌላ ቦታ በመጀመሪያዉ ሽንፈት የተሰማዉ ሰዉ ብዙ ነዉ፡፡እናም ጓደኞቼ ዛሬ ይህንን ሀዘን ወደ ደስታ እንደሚቀይሩት እምነቴ ነዉ፡፡አሰላለፉንም ሰምቻለሁ፡-እናም ለማጥቃት የሚሆንም ነዉ፡፡እና ዛሬ እንሚያስደስቱን እርግጠኛ ነኝ፤ለማለፍ ደግሞ የግድ የግድ ድሉ ያሥፈልገናል”ብለዋል

የመጀመሪያ ጨዋታዉን 400ኪ.ሜትር አቋርጦ የመጣዉ ጌታነህ ዛሬ ጨዋታ ስለነበረበት መምጣት አልቻለም፡፡በቀጣዩ ማክሰኞ የጋና ጨዋታ ግን ከቡድኑ ጋር እንደሚኖር ገልጽዋል፡፡ለቡድኑም መልካም አድል ተመኝትዋል፡፡አስተላልፍያለሁ!!!

የዋልያዉና ኮንጎ ጨዋታ ሊጀመር 1 ሰአት ከ20 ደቂቃ ይቀራል፡፡ሊቢያ እና ጋና 1-1 ናቸዉ፡፡72ኛዉ ደቂቃ ላይ ይገኛሉ!!

1 thought on “ጌታነህ ግብ አስቆጠረ….”ዛሬ ዋልያዉ ማሸነፍ አለበት!!!” መልካም እድል!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.