በአምላክ ተሰማ ወሳኙን ጨዋታ ይመራል፡ከኢሳ ሀያቱ አድናቆት ተችሮታል!!

bamalak

ዋልያዉ ከቻን ዉድድር ምድቡን ወድቅዋል፡፡አሁን የኢትዮጲያ ብቸኛዉ ተወካይ ኢንተርናሽናል ዳኛዉ በአምላክ ተሰማ ሁንዋል፡፡የመጀመሪያ ጨዋታዉን ሞሮኮ ከዝምባቡዌ ጋር አጫዉቶ ነበር፡፡እናም በካፍ የአልቢትር ኮሚቴ ግምገማ በአምላክ በጨዋታዉ እንከን ያለበት ነገር እንዳልሰራና ጥሩ ዳኝነት እንዳሳየ ተነግርዋል፡፡ስለዚህም በዉድድሩ 2ተኛ ጨዋታ እንዲዳኝ እድሉ ተሰጥቶታል፡፡

እሮብ ከሚደረጉት የምድብ 2ት ወሳኝ ጨዋታዎች መሀል ዲሞክራቲክ ኮንጎ እና ብሩንዲን ጨዋታ እንዲዳኝ ተመርጥዋል፡፡በቻን ዉድድር 17 መሀል ዳኞች ተመርጠዉ ነበር፡፡ከነዚህ መሀል 2ተኛ ጨዋታ የማጫወት እድል ያገኙት 6ብቻ ናቸዉ፡፡ኢትዮጲያዊዉ በአምላክም ከነዚህ መሀል ሁንዋል፡፡ብሩንዲ እና ኮንጎ የሚያረጉት ጨዋታ ደግሞ የሞት ሽረት ነዉ፡፡ብሩንዲም ኮንጎም 4ት እኩል ነጥብ አላቸዉ፡፡ጋቦን 3ነጥብ ይዣ ምንም ከሌላት ሞሪታኒያ ጋር ትጫወታለች፡፡ስለዚህ ኮንጎ እና ብሩንዲ ካልተሸናነፉ አደጋ ላይ ይወድቃሉ፡፡

እንዲህ አይነት ወሳኝ ጨዋታ እንዲመሩ የተመረጡት 4 ዳኞች ብቻ ናቸዉ፡፡በአምላክም ከዚህ አንዱ ሁንዋል፡፡በጨዋታዉ ጥሩ መዳኘት ከቻለ ዋልያዉ ያላለፈዉን የምድብ ማጣሪያ በአምላክ ያልፈዋል ማለት ነዉ፡፡

ከመጀመሪያዉ ጨዋታ በኋላ የካፍ ፕሬዝዳነት ኢሳ ሀያቱ ዜግነቱን በመጠየቕ አድናቆታቸዉን ችረዉታል፡፡የካፍ ምክትል ፕሬዝዳንትም ከኢትዮጲያዉ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳነት ጁነዲን ባሻ ጋር ባደረጉት ቆይታም በዳኛዉ ብቃት ደስተኛ መሆናቸዉን ነግረዋቸዋል፡፡ለፊፋ አለም ዋንጫ 3ት ፍሪካዊ ዳኞች እንዲመሩ አስቀድሞ መመረጣቸዉ ይታወሳል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.