ብዙም ለዉጥ አይኖረንም…ዋልያዉ የመጨረሻ ልምምዱን ሰርትዋል!!!ፋሲካ እና ፋዲጋ???ደጋፊዎች ማስጠንቀቂያ…ትትት በዛብን!!!

IMG_1238[1]

4አሰት ላይ ነዉ ልምምዱ የተጀመረዉ–መሀል ገብ ከዛም በግማሽ ሜዳ ጨዋታ–ቤስቱ ብዙም ለዉጥ እንደማይደረግበት አሰልጣኝ ሰዉነት ተናግረዉ ነበር፡፡ዛሬም ቤስቱ ቡድን ላይ የ2ት ተጫዋቾች ቅያሪ ብቻ ነዉ የነበረዉ፡-ፋዲጋ እና ፋሲካ ነበሩ የገቡት፡-ዋልያዉ ትሬኒንግ ላይ እንደሌላ ቡድን ቤስትና ቤንቹ መለየት ከባድ ሁንዋል፡፡ከሊቢያ በፊት ደጉ–አበባዉ እና ስዩም በቤንቹ ላይ ነበር የሰሩት–የጨዋታዉ ቀን ቤስት ገቡ፡፡ነገም ምን ሊሆን እንደሚቸል አይታወቅም፡፡ለመገመት ያህል ግን አዳዲስ ገቢዎች ሊሆኑ የሚችሉት ፋዲጋ እና ፋሲካ ናቸዉ –መነሻዉ የዛሬ ትሬኒንግ ነዉ!!

በጉዳት በኩል ሁሉም ተጫዋቾች ጤነኛ ናቸዉ፡፡የሊቢያዉ ጨዋታ ሽንፈት የቡድኑን መንፈስ ቀይሮታል፡፡በተለይ ጣቶች በተጫዋቾች ላይ መቀሰራቸዉ ተጫዋቾቹን አሳዝንዋል፡፡ማንም ቢገባ ስህተት ሊሰራ ይችላል ነገር ግን አንድ ስህተት ላለመስራት ሁሉም ሲጠነቀቅ ቡድኑ እንደሚጎዳ ተጫዋቾቹ ይገልጻሉ፡፡ለሊቢያዉ ጨዋታ ሽንፈት ሀላፊነቱ በተጫዋቾቸ ላይ መላከክ እንደሌለበት ብዙዎቹ ያምናሉ፡፡እንደቡድን ደካማ መሆናችን እዉነት ነዉ፡፡ግለሰቦች ተነጥለዉ ክፉኛ መዘለፋቸዉ ግን ማንንም አይጠቅምም፡፡ነገ እነሱን ተክተዉ የሚገቡትም ይህንን ትችት ፈርተዉ ቡድኑን መጥቀም የሚችሉትን ያህል ሳይጠቅሙ ይወጣሉ የሚለዉ ሀሳብ የብዙዎችን ተጫዋቾች ያሳመነ ነዉ፡፡እናም ጥሩ ነገር የሰራንበት ጊዜም ሊታወስ ይገባል፡፡ትችቱ ከዉድድሩ በኋላ ቢቆይ እና የቀሩንን ጨዋታዎች በደንብ ብንዘጋጅባቸዉ ጥሩ ነዉ ባዮች ናቸዉ የዋልያዉ ተጫዋቾች!!

ካፍ በዋልያዉ ደጋፊዎች ላይ ማስጠንቀቂያ ልክዋል፡፡በሊቢያዉ ጨዋታ ላይ የእርስ በእርስ ድብድብ ነበር፡፡ደጋፊዎቻችሁ ተጣልተዉ በጥብጠዋል፡፡ይህ ነገር ከተደገመ በፌዴሬሽኑ ላይ ቅጣት እጥላለሁ ብልዋል፡፡ባለፈዉ የአፍሪካ ዋንጫ በተመመሳሳይ 5ሺ ዶላር ዋልያዉ መቀጣቱ ይታወሳል፡፡በዛሬዉ የፕሪማች ስብሰባ ላይ የፌዴሬሽኑ ተወካዮች በጉዳዩ ላይ ተቃዉሞዋቸዉን እንደሚያሰሙ ተናግረዋል፡፡ምክንያቱም የኢትዮያዊ ደጋፊ ለመሆኑ የተደባደበዉ ምንም ማረጋገጫ የለም፡፡ዋልያዉን የሚደግፉ ብዙ ደቡብ አፍሪካዊያንም አሉ ባይ ነዉ ፌዴሬሽኑ፡-ለነገሩ ነገ እምብዛም የዋልያዉ ደጋፊ ይገኛል ተብሎ አይጠበቅም፡፡

 

10 thoughts on “ብዙም ለዉጥ አይኖረንም…ዋልያዉ የመጨረሻ ልምምዱን ሰርትዋል!!!ፋሲካ እና ፋዲጋ???ደጋፊዎች ማስጠንቀቂያ…ትትት በዛብን!!!

  1. hey man….every body should be responsible for his/her own feelings. I dont care about what they feel. I’ll tell it like it is. They are not babies. They should perform well other wise they will be blamed and fired. That’s the fact of life for all of us. They better learn it too.

  2. SEWUNET he religated trans and neyala how he becomes national team coch ? HE MUST LEAVE AND TEACH BIOLOGY THAT HE CAN ?

  3. U better care for players feeling and it is a big responsibility we have to stand beside waliya n give them moral support!

  4. U better care for players feeling and it is a big responsibility we have to stand beside waliya n give them moral support!

  5. why are the players offended ? are they cry babies or what ? we don’t care if their feelings are ‘hurt’. This is their job and they should do it well. We all do our job well or we lose money or get fired. If they want the recognition, money and respect that comes with the game , they should learnt to accept blame, work harder, make NO mistakes or try their best not to make silly mistakes and be creative. We can not treat them like babies. If they don’t give us the football we want, there is plenty of great European football to watch.

  6. said you have unresolved issue with sewunet …please calm down and try to report rationally. Not impressed!!!!!!!!!!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.