በዋልያዉ 5ተኛ ቀን ልምምድ —ሁሉም ሰርተዋል!!”ልቡ ለታመመ–ምላሱን ለዋጠ ታጥቀን መጥተናል” ጠብታ አንቡላንስ ከብሎምፎንቴን

የብሎምፎንቴንን ቃጠሎ እንዴት እንደማስረዳችሁ አላቅም፡፡ሙቀት ሳይሆን አናት የሚበሳ ጻሀይ ነዉ ያለዉ–በእግር መዉጣት ከባድ ነዉ፡፡ናላ የሚያዞረዉ ጻሀይ እቅድዎን ያሰናክላል፡፡ዱባይ በስንት ጣእሙዋ..ሀሩሩ ራሱ ምግብ እኮ ነዉ፡፡

ዛሬ ዋልያዉ ለተሬኒንግ ቀጠሮ የነበረዉ በዚህ ቀዉጢ ሰአት ነበር፡፡10 ሰአት ላይ—ግን ባልተጠበቀ ሁነታ ዝናብ ዘንብዋል፡፡እናም በተሻለ አየር ነዉ ልምምድ የተደረገዉ፡-ሁሉም ጤነኛ ሁነዉ ሰርተዋል፡፡ወገቡ አከባቢ የተጎዳዉ ኤፍሬም አሻሞ ሳይቀር ሰርትዋል፡፡ስዩም ተስፋዬም አገግምዋል፡፡

በነገራችን ላይ በሊቢያዉ ጨዋታ ቀን አሰልጣኝ ሰዉነት ቱሳን መቀየሬ ስህተት ነበር ሲሉ አምነዋል፡፡ይህንን የተናገሩት ለተጫዋቾቹ ነዉ፡፡ትላንት በነበረዉ ልምምድ ላይ ነዉ–ቱሳን መቀየር አልነበረብኝም፡እሱ ሜዳዉ ዉስጥ መቆየት ነበረበት በሚል የተናገሩት,,

ዛሬ ልምምዱ በግማሽ ሜዳ ላይ እርስ በርስ ጨዋታ ነበር፡፡ለኮንጎ ጨዋታ እነማን እንደሚሰለፉ ፍንጭ ብዬ እንዳልነግራችሁ ባለፈዉም በቤንቹ ቡድን ላይ ተሰላፊ የነበሩት አበባዉ–ስዩም እና ደጉ በጨዋታዉ ላይ ተሰላፊ ነበሩ፡፡ምናልባት በአጥቂ ደረጃ 3ቱንም ዳዊት –ኡመድ እና ማናዬን አብረዉ ሊያሰልፉ ይችላለሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ዛሬ ጥዋት ከሰጡት መግለጫ ተነስቼ ነዉ ይህንን የምላቸሁ፡-

ክብረት በዋልያዉ አዲስ እንግዳ ነዉ፡፡መቸስ የአዲስ አበባ ስታድየም ታዳሚ ሁናችሁ የጠብታ አምቡላንስን ሳታርፉ አትቀሩም፡፡የጠብታ ስራ አስኪያጅ ነዉ፡፡ሙያዉ ደግሞ የቆመ ልብን ማስነሳት..ትንፋሽ እንዲቀጥል ማድረግ-ምላሱን የዋጠ ተጫዋች ወደ ቀልቡ እንዲመለስ ማድረግ ነዉ፡፡መሳሪያዉ 5ሺ ዶላር ያወጣል፡፡ካፍ ሜዳ ላይ የሚሞቱ ተጫዋቾች መብዛት ሲያሳስበዉ አነዚህን ባለሙያዎች መያዝ ግዴታ አድርጎታል፡፡ደግነቱ በዋልያዉ በኩል እስካሁን እንደዚህ አይነት እርዳታ ያስፈለገዉ የለም፡፡በባህላዊ መንገድ ባየዉ እና በሚያቀዉ አማካዩ ቱሳ የተጫዋቾች ነፍስ አትርፍዋል፡፡

ደደቢት ከመገር ሲጫወቱ ባደረገዉ የነፍስ አድን ስራም የ2002 የአመቱ የመልካም ስነ ምግባር ተሸላሚ ሁንዋል፡፡

ልምምድ ሜዳ ላይ

ይህንን መሳሪያ ያዩ ተጫዋቾች ከዚህ በፊት ባዩት ነገር ሲያወሩ የሀዋሳ ከነማዉ ወጌሻ ሁሉም ምላስ ላይ ገቡ፡፡ሰዉየዉ ሸምገል ያሉ ናቸዉ እናም አንድ ተጫዋቸ ምላሱን ዉጦ ተጫዋቾች እና ዳኛዉ ተደናግጠዉ ጨዋታዎ ቁምዋል፡፡እሳቸዉ በጉጉት ይጠበቃሉ፡፡እናም እየሮጡ ደረሱ—ከአሁን አሁን ሰዉየዉ የልጁን ምላስ በሚያቁት መንገድ መልሰዉ ትንፋሽ ይዘሩለታል ብለዉ ሁሉም እየጠበቁ  ነዉ፡፡ሰዉየዉ በቦታዉ ደረሱና ልጁን አዩት–ትንፋሽ የለዉም–ፀጥ ብልዋል፡፡እቃቸዉን ጥለዉ ኡ ኡአ ኡ ብለዉ ማበድ ጀመሩ፡፡ይህም አልበቃ ብልዋቸዉ እየተነሱ መፍረጥ ጀመሩ፡፡ሀዘን ላይ የነበሩት ተጫዋቾች በወጌሻዉ ድርጊት ሳቃቸዉን አፍነዉ እንደምንም የሚረዳዉ ሰዉ ተገኝቶ ልጁ ነፍሱን ዘራ፡፡ህይወት ያተርፋሉ የተባሉት ወጌሻ ህይወቱ ባላለፈዉ ተጫዋች ሙሾ አዉርደዉ ወደ ቦታቸዉ ተመለሱ፡፡

አሁን እነ ክብረት ይህ እንዳይደገም አዲሱን መሳሪያ ይዘዉ ብሎምፎንቴን ይገኛሉ፡፡ፎቶዉን ተመልከቱ!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.