የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ጥር ላይ በቀድሞ ቦታው ሊቆም ነው

ታህሳስ 14፣ 2008

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ግንባታን ለማከናወን ሲባል በጊዜያዊነት ከቦታው ተነስቶ  ብሔራዊ ሙዚየም የነበረው የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ጥር 29 ቀን 2008 ዓ.ም ቀድሞ ከነበረበት ቦታ እንደሚቆም የቅርስና ጥናት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት በክብር ወደ ነበረበት ቦታ ለማስቀመጥ የሚያስችል ግንባታ መጀመሩን አስታውቋል፡፡

ሐውልቱ በቦታው ሲመለስ የሚቆምበት አደባባይ የሐውልቱን ክብርና ታሪክ በሚገልጽ መልኩ እንዲሆን ኮሚቴ ተቋቋሞ ሲሰራ ቆይቷል፡፡

የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ደስታ የሐውልቱ ይዘት ሳይቀየር እሴቶች ተጨምረውበት ወደ ቦታው እንደሚመለስ ገልፀዋል፡፡

የባቡሩ ንዝረት በሐውልቱ ላይ ጉዳት እንደማያስከትልም የባለሙያዎች ጥናት ማረጋገጡን ተናግረዋል፡፡

ሐውልቱ ወደበታው ሲመለስ ቀድሞ ከነበረበት አቀማመጥ በተለየ መልኩ ውበቱ እንዲጎላ እና አደጋ እንዳይደርስበት ጥንቃቄ ተደርጓል ብለዋል፡፡

የሐውልቱን መቀመጫ ግንባታ የሚያከናውነው የአሰር ኮንስትራክሽን ተወካይ ግንባታውን በዲዛይኑ መሰረት በማከናወን በተቀመጠለት ጊዜ እንደሚያስረክብ ገልፀዋል፡፡

ሪፖርተር:-ጌቱ  ላቀው

ምንጭ፦ EBC

Leave a Reply

Your email address will not be published.