3ተኛዉ የአፍሪካ ዋንጫ 52ተኛ አመት በሀዘን ይታወሳል!!!!…ጀግኖቹን የማይዘክር እግር ኳስ…”ክብር ተነፍገናል”ሉቻኖ ቫሳሎ

luciano 1

ልክ የዛሬ 52 አመት በትላንትናዉ ቀን…እሁድ ጥር 11-1954 የኢትዮጲያ እግር ኳስ የምንግዜም ትልቁ ቀን ነበር፡፡የያኔዉ ጥቁር አንበሳ ግብጽን አሸንፎ ለአንዴና እስካሁን ለመጨረሻ ጊዜ የአፍሪካን ዋንጫ የወሰደበት ቀን ነበር፡፡4ት ቡድኖች በተሳተፉበት ዋንጫ አዲስ አበባ ላይ 1ሳምንት በፈጀ ዉድድር የዣን ዘመኑ ትዉልድ የአፍሪካን ዋንጫ ካነሳ ትላንት 52ተኛ አመት አስቆጥርዋል፡፡

እነዚህ 52ት አመታት በእግር ኳስ የሀዘን አመታት ናቸዉ፡፡ለአፍሪካ ዋንጫ ከ4ተኛዉ ጀምሮ ያለፉት ቡድኖች ጥሩ ዉጤት ሳያመጡ ዋንጫዉንም ሳይደግሙ ቀሩ፡፡ይባስ ብሎ ከ52 አመታት 31ዱ ከተሳትፎም የተራቀባቸዉ አመታት ሆኑ፡፡ደቡብ አፍሪካ ላይ ከ32 አመታት በኋላ ያለፈዉና ጎሮ ወሸባ የተባለለት ቡድንም የተለመደዉን ዉጤት ይዞ ተመለሰ፡፡አሁንም በአመቱ የኢትዮጲያ እግር ኳስ ተከታታይን ልብ የሚሰብር ዉጤት ላይ ተገኝትዋል፡፡እናም 52ተኛ አመቱ በከፍተኛ የዉጤት ማጣት ሀዘን ዉስጥ ይታወሳል፡፡

የታሪካዊዉ ትዉልድ አባላትም ክብር ተነፍጎናል ይላሉ፡፡በህይወት ያሉት በጣት የሚቆጠሩ ናቸዉ፡፡ኢትዮጲያ ዉስጥ የሚገኘዉ የያኔዉ ተከላካይ አዋድ መሀመድ “የዕድሜ ልክ ስታድየም መግቢያችንን እንኳን ተቀምተናል፡፡ታሪክ በሰራንበት ስታድየም ጨዋታ ለመታደም ሌሊቱን ሙሉ መሰለፍ አለብን፡፡ሌላዉን ነገር ትተዉ እንኳን ይቺን ማድረግ ሲያቅታቸዉ ማየት ያሳቅቃል”ይላል፡፡

ብቸኛዉ የአፍሪካ ዋንጫ ያነሳዉ አምበል ሉቻኖ ቫሳሎም ከሚኖርበት ሮም ጣሊያን “እኛ ታሪክ ብንሰራም ተጥለናል፡፡ማንም በእግር ኳሱ በሰራነዉ ስራ ሊያስታዉሰን አልቻለም ”ባይ ነዉ፡፡ወንድሙ ኢታሎ ኤርትራ ይገኛል፡፡ግብጽ ላይ አንድ ግብ ያሥቆጠረዉ እና የዉደድሩ ኮከብ ግብ አግቢ መንግስቱ ወርቁ ህይወቱ ካለፈ ወዲህ ስለሱ የተሰማዉ ጥቂት ነዉ፡፡ኢትዮጲያ መቼ ነዉ የአፍሪካን ዋንጫ የበላችዉ ተብሎ የዚህ ትዉልድ አባላት ቢጠየቁ በርግጠኝነት ደቡብ አፍሪካ ላይ ሊሉ ይችላሉ፡-ምክንያቱም የድሮዉን ከአሁኑ ያገናኘ ድልድይ የለምና፡-

የኢትዮጲያ ብሂራዊ ቡድን የአፍሪካን ዋንጫ ባነሳበት 52ተኛ አመት ቀን የሀገሪቱ ትልቁ መነጋገሪያ በኤፍ.ኤሞች ተዳምቆ የሚተላለፈዉ የማንቸስተር እና ቼልሲ ጨዋታ ነበር፡፡ቲቪ እና ሬድዮ–ፕሬሱ ና ድረ-ገጹ የሰጡት ትኩረት በርግጥም ታሪካዊያኑ ለምን አንዳልታወሱ ማስረጃ ይሆናል፡፡

 

1 thought on “3ተኛዉ የአፍሪካ ዋንጫ 52ተኛ አመት በሀዘን ይታወሳል!!!!…ጀግኖቹን የማይዘክር እግር ኳስ…”ክብር ተነፍገናል”ሉቻኖ ቫሳሎ

Leave a Reply

Your email address will not be published.