17ኛው የአይ.ኤ.ኤ.ኤፍ የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ይጀመራል

Team Ethiopia

ኢትዮጵያ በአራት ሴቶች እና አምስት ወንድ አትሌቶች ትወከላለች   

ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ለቀጣዮቹ አራት ቀናት የእንግሊዟን በርሚንግሀም ከተማ የዓለም አትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪያን የትኩረት ማዕከል በሚያደርጋት 17ኛው የአይ.ኤ.ኤ.ኤፍ የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ሀገራችን ኢትዮጵያ በአራት ሴት እና አምስት ወንድ አትሌቶች ትወከላለች፡፡ በሴቶች በሶስት (800ሜ.፣ 1500ሜ. እና 3000ሜ.) በወንዶች በሁለት (1500ሜ. እና 3000ሜ.) የውድድር አይነቶች የምትሳተፈው ኢትዮጵያ በሴቶች 800ሜ. በሀብታም አለሙ፣ በሴቶች 1500ሜ. በገንዘቤ ዲባባ እና በዳዊት ስዩም፣ በሴቶች 3000ሜ. በገንዘቤ ዲባባ እና ፋንቱ ወርቁ፤ በወንዶች 1500ሜ. በሳሙኤል ተፈራ እና አማን ወጤ እንዲሁም በወንዶች 3000ሜ. በዮሚፍ ቀጄልቻ፣ ሀጎስ ገብረሕይወት እና ሰለሞን ባረጋ የምትወከል ሲሆን ሱፐር ኢንቴንዳንት ሁሴን ሼቦ እና ኮማንደር ቶሌራ ድንቃ ቡድኑን በአሰልጣኝነት ይመሩታል፡፡

ገንዘቤ ዲባባ እና ዮሚፍ ቀጄልቻ ከሁለት ዓመት በፊት በዩናይትድ ስቴትስ ፖርትላንድ በተከናወነው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ላይ በ3000ሜ. ያስመዘገቡትን የሻምፒዮንነት ክብር ለማስጠበቅ የሚፎካከሩ ሲሆን በፖርትላን የ1500ሜ. የብር ሜዳልያ አሸናፊ የነበረችው ዳዊት ስዩምም ዘንድሮ ለወርቅ ሜዳልያው ድል ከሀገሯ ልጅ ገንዘቤ ዲባባ እና ሌሎች ተሳታፊዎች ጋር ብርቱ ትንቅንቅ እንደምታደርግ ይጠበቃል፡፡ ገንዘቤ ዲባባ በሁለት ርቀቶች (በ1500ሜ. እና 3000ሜ.) ላይ የምትወዳደር ሲሆን በወንዶች 3000ሜ. ኢትዮጵያን የሚወክሉት ሶስቱ  አትሌቶች (ሀጎስ፣ ሰለሞን እና ዮሚፍ) በሚወዳደሩበት ርቀት በወቅቱ የዓለም የፈጣን ሰዓት ደረጃ ከአናት የተቀመጡ እንደመሆናቸው ሶስቱንም ሜዳልያዎች ለመውሰድ እንደሚፎካከሩ ይጠበቃል፡፡ በዚህ ውድድር ላይ አንድ ሀገር እንዲያሳትፍ የሚፈቀድለት ሁለት አትሌት ብቻ ሲሆን በወንዶች 3000ሜ. ኢትዮጵያ ሶስት አትሌቶችን የማሳተፍ ዕድሉን ያገኘችው ዮሚፍ ቀጄልቻ በዘንድሮው የአይ.ኤ.ኤ.ኤፍ የዓለም የቤት ውስጥ ውድድሮች ቱር በነጥብ የርቀቱ የአተቃላ አሸናፊ በመሆን የዋይልድ ካርድ ተጠቃሚነቱን ዕድል ለማግኘት በመብቃቱ ነው፡፡

በበርሚንግሀም ሀገራችንን ወክለው የሚሳተፉትን አትሌቶቻችንን ፉክክር ለመከታተል ለምትሹ ኢትዮጵያውያኑን አትሌቶች የሚወዳደሩበትን ፕሮግራም እነሆ (ሰዓት በኢትዮጵያ አቆጣጠር)፡-

Leave a Reply

Your email address will not be published.