አትሌት እታፈራሁ ተመስገን አበረታ እፆች በመውሰዷ ለ12 አመታት ከውድድር ታገደች

Athlet Etaferahu Temesgen

የብሔራዊ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ (NADO) ዛሬ ሰኔ 13/2012 ዓ. ም ባሳወቀን መረጃ መሠረት አትሌት እታፈራሁ ተመስገን ወዳጆ እ.ኤ.አ october 20,2019 ዓ. ም. በካናዳ በተካሄደው የወተር ፍሮንት ማራቶን በግሏ በተካፈለችበት ወቅት በተወሰደው የደምና ሽንት ናሙና የተከለከሉ 2 ንጥረ ነገሮችን (ኢፒኦ እና ቴስቴስትሮን – EPO and Testestrone) መጠቀሟ በመረጋገጡ እና በተጨማሪም ይሄንን ጥፋት ለመሸፋፈን ሃሰተኛ የህክምና ማስረጃ በማቅረብ ለፈፀመችው 3 ተደራራቢ ጥፋቶች እ.ኤ.አ ከNovember 20,2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ November 20, 2031 ዓ. ም. ድረስ ለ12 አመት የሚቆይ ከማንኛውም የአትሌቲክስ ውድድሮች እገዳ አስተላልፎባታል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም እየተከተለ ካለው የንፁህ አትሌቲክስ መርህ መሠረት፣ እርምጃውን የሚደግፍ መሆኑን እየገለፀ፣ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከእንዲህ አይነት የህግ ጥሰትና አንገት አስደፊ ተግባር ራሳቸውን እንዲጠብቁና ወደ እንደዚህ አይነት ድርጊት ሊገፋፉ ከሚችሉ ግለሰቦችና ሁኔታዎች እንዲርቁ ጥብቅ መልእክቱን ያስተላልፋል።

ምንጭ: የኢአፌ