ጩኸት ቅሚያ…

 

ከአንባቢ የተላከልን

ከ6 አመት በፊት ሪያል ማድሪድ እና አል-ናስር ክለብ ተጫወቱ፤ስታድየሙ ንጉስ ፉአድ ስታድየም ነበር፤ሪያድ ሳኡዲ አረቢያ ዉስጥ መሆኑ ነዉ ጨዋታዉ……70ሺ ሰዉ ስታድየሙን የሞላዉ በጊዜ ነበር፤30ሺ የሚሆኑቱ ደግሞ ትኬት አጥተዉ ስታድየሙ አከባቢ ተስፋ ሳይቆርጡ ይጠባበቃሉ፤ይህ ሁሉ ሳኡዲያዊ ሊያየዉ የጓጓለት ጨዋታ የአንደ ተጫዋች ሽኝት ነበር፤የግብ አይምሬዉ የአረቡ አለም ፔሌ ማጅድ አብዱላህ ነበር፤የሚገርመዉ ደግሞ ካቆመ ከ 10አመት በሁዋላ ነዉ ስንብቱ…ይህ የሳኡዲ ኮከብ ግብ አግቢ መገኛ ጅዳ አልያም ሪያድ አይደለችም፤ጎረቤት ካርቱም እንጂ…አባትና እናቱ ለተሻለ ኖሮ ፍለጋ ነበር ማጂድ ከተወለደ በሁዋላ ይዘዉት ወደ ሳኡዲ ያመሩት …እናም ዉለታዉን ለመክፈል 100ሺ ሰዉ በስታድየም ታጨቀ! የሳኡዲን እግር ኳስ ታሪክ ለመረመረ አብዘኞቹ ኮከብ ተጫዋቾች የተፈጥሮ ክህሎት ባለቤቶች መነሻ ምስራቅ አፍሪካ ነች፤እንደአትሌቲክሱ ተገዝተዉ አይደለም፤ኢትዮጲያም ከፍተኛ ድርሻ አላት፤ ለኑሮ ብለዉ ከመጡ በሁዋላ ዉድ የሆነዉን ዜግነት ለችሎታቸዉ ሲባል ይሰጣቸዋል፤እናም ሳኡዲን በእግር ኳሱ አለም ያገናሉ..በተለይ በእስያ አህጉር ሳኡዲ ያላትን የበላይነት ያስከበሩት በነዚህ ተጫዋቾች ነዉ!! እስኪ የሪያድ መንገድ ላይ ስለ መሀመድ ኑር ጠይቁ..የአረቡ አለም እንቁ የነበረዉ ተጫዋች ከኢትዮጲያዊ ቤተሰቦች የተገኘ ነዉ፤ምናልባትም በኳስ ችሎታዉ ባይመረጥ ኑሮ አሁን በግፍ እየታሰሩ ካሉት መሀል ይካተት ነበር፤ ሪዳ ቱከር ሁነኛ ተከላካይ ነዉ፤በ2002 እና 2006 የአለም ዋንጫ ሳኡዲን ወክሎ ተጫዉትዋል፤ከሰሜን ኢትዮጲያ ወደ መዲና ከሄዱ ቤተሰቦች የተገኘ ሰዉ ስለመሆኑ ሀበሻ በኩራት ያወራለታል፤አሁን በሪያድ ስታድየም ተገኝታችሁ ሀዛዚ የሚል ስም ብታነሱ ሁሉም ጆሮዉ ቁሞ ያዳምጣቸሁዋል፤ይህ ተጫዋቸች ንስሩ በመባል ይታወቃል…ክለቡ አል ሸባብ ነዉ፤እሱና ታላቅ ወንድሙ ኢብራሂም ሀዛዚ ኢትዮጲያዊ ደም አላቸዉ፤ሳኡዲን በዜግነት እና ትዉልድ አንጂ በዘር ሀረጋቸዉ አያቅዋትም…በአንድ ወቅት ከብሂራዊ ቡደኑ 8 የሚሆኑ ተጫዋቾች ኢትዮጲያዊና ኤርትራዊ ደም ያላቸዉ ነበሩ!! ብቻ ምን አለፋችሁ..አኢትዮጲያ ብሎም አፍሪካ ለሳኡዲ ብሂራዊ ቡድን ቁልፍ ሚና ተጫዉተዋል፤ለባንዲራዋ መላቅ ትልቁን ድርሻ ተወጥተዋል፤አሁን ግን የሚሰማዉ እና የሚታየዉ ነገር እጅጉን አሳዛኝ ነዉ፤ለሀገሪቱ ዉለታ የዋሉት ሰዎች ወንድሞችና እህቶች ላይ የደረሰዉ ነገር ያሳዝናል፤ስም ያለዉ ተጫዋች ከምእራብ አፍሪካ አልያም ከምስራቅ የመጣ ነዉ..አሁን ግን ከእነዚህ ሀገራት የመጡ ሰዎች እንደእንስሳ ይጋዛሉ፤I love Ethiopia የሚለዉን አርማ አንገቱ ላይ ያጠለቀዉ ኢትዮጰያዊ በደህናዉ ጊዜ በካታንጋ አልያም ሚስማር ተራ ና ዳፍ ትራክ ድጋፉን ሲሰጥ ነበር የመንስለዉ…በዛ መልኩ ህይወቱን አጥቶ በስለቱ ልበሱ ሲቀደድ ማየት ግን ያማል፤ አሁን በካላባር ኢትዮያን የሚወክሉት ተጫዋቾም የዚህ ትዉልድ አባልነታቸዉ ጥርጥር የለዉም፤ለዛዉም ትዉልዱን አንድ ያደረጉ መነጋገሪያዎች ናቸዉ፤ደጋፊዎቹ ወደ ካላባር ቢያመሩም ልባቸዉ ግን እነዛ ወገኖቻቸዉ ጋር ነዉ፤ሁሉም በአንድ ነገር ይስማማሉ…አለም የኢትዮያዊያንን እሮሮ ሊሰማ ሊያዳምጥ ለታሪክ ሊያሥቀር ይገባዋል፤በቅድሚያ ነገርየዉን ማቆም ከዛም ዜጋዉን ማክበር…በዚህ ሰአት ከብሂራዊ ቡድኑ ልቆ ለዚህ አርአያ ሊሆን የሚችል የትም አይገኝም…ካላባር ለሳኡዲ ማስታወሻ አንድ ነገር ይጠበቅባታል፤ዉለታ የረሱትን ለማስታወስ…!!!የተቀማነዉን ጩሀት በአለም ህዝብ አይንና ጆሮ ለማስመለስ ደጋፊዎችና ተጫዋቾች ቁልፉን ይዘዋል!!ጩኸታችንን አስመልሱልን–ሳኡዲ ትጣራለች!

Leave a Reply

Your email address will not be published.