“ግብ እናገባለን–ጋናን ለማሸነፍ እንጥራለን” የቀድሞ ኮከብ ግብ አግቢ ቢያድግልኝ ኤልያስ

IMG_3581

በኮንጎ ጨዋታ የተከላካይ ክፍሉን ከሳላሀዲን ባርጌቾ በጥሩ ሁኔታ መርተዉታል፡፡በዋልያዉ ጉዞ በተለይ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ሁነኛ ሚና ከተጫወቱ መሀል ቢያድግልኝ ኤልያሥ አንዱ ነዉ፡፡ተጫዋቹ ያልተጫወበት ቦታ በረኝነት ብቻ ነዉ፡፡በ2002 አርባምንጭ ዳሸን ሲጫወት በአማካይ እና አጥቂነት ቡድኑን አገልግልዋል፡፡ሲዳማ ቡናን ወደ ፕሪሚየር ሊግ ካመጡት ተጫዋቾች አንዱ ነዉ፡፡በብሂራዊ ሊግ ዉድድር ኮከብ ግብ አግቢነት እየተፎካከረ ነበር፡፡11 ግቦች ነበሩት፡፡ለጥቂት ነዉ በመጨረሻዎቹ ጨዋታዎች የተበለጠዉ…

ስዩም አባተ ተጫዋቹን አይቶ ለቡና መልምሎት አናግሮት ነበር፡፡ያኔ የዳሸን አጥቂ ነበር፡፡እናም ነገሮች እያለቁ እያለ ስዩምና ቡና ተጣሉ፡፡ቢያድግልኝም ሲዳማ ቡና ገባ፡፡አሁን የጊዮርጊስ ተጫዋች ነዉ፡፡ወጣቱ ተከላካይ አሁን በብሂራዊ ቡድኑ ብዙ ልምድ እያገኘን ነዉ ከአሁን በኋላ ባሉት ዉድድሮች አጨዋወታችንን ካስተካከልን በርግጠኝነት የሚፈትነን ቡድን አይኖርም የሚል እምነት አለዉ፡፡ስለዛሬዉ ጨዋታም እንዲህ ብሎኛል፡፡

“እኛ ከተጫወትን ማንም አይከብደንም፡፡ተጋጣሚዎቻችንን በኳስ መብለጥ ከቻልን እናሸንፋለን፡፡ለዚህ ደግሞ የኛ ተከላካዮች ሚና ወሳኝ ነዉ፡፡ወደ ፊት እየሄድን በተጋጣሚዎቻችን ላይ ሜዳዉን አጥበን ብዙ ሆነን ወደ ጎል መድረስ አለብን፡፡ጋናን ለማሸነፍ እንገባለን፡፡እስካሁን ነጥብም ጎልም የለንም፡፡ስለዚህ ግብ ማስቆጠርም ነጥብ ማግኘትም አለብን፡፡ይህ የሀገር ጉዳይ ነዉ፡፡ለክብራችን ኢትዮጲያ በእግር ኳስዋ ስምዋ በደንብ እንዲጠራ ጋናን አሸንፈን ከዉድድሩ ማስወጣት አለብን፡፡የተከፋዉ ደጋፊያችንንም በዚህ መካስ አለብን” ይላል፡፡

ቢያድግልኝ ኤልያሥ በቀኝ በመሀል ተከላካይነት–በአማካይነት ከዛም በአጥቂነት ተሰልፍዋል፡፡”ከሁሉም ቦታ ይልቅ መሀል ላይ ብጫወት ደስ ይለኛል፡-አምኖ የሚያሰልፈኝ አሰልጣኝ ባገኝ በደንብ እንደምጠቅም እርግጠኛ ነኝ” ብሎኛል፡፡

በባህሪያቸዉ ዝምተኛ ከሆኑ ተጫዋቾች መሀል ቢያድግልኝ ይጠቀሳል፡፡በጊዮርጊስ ቤትም ምሳሌ ነዉ፡፡የክለቡ መደበኛ ልምምድ 4ሰአት ከመድረሱ በፊት በጠዋት 11 ሰአት ተነስቶ በግሉ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ያደርጋል፡፡ከዛ ወደ መደበኛዉ ትሬኒንግ ይሄዳል፡፡ከእንቅልፍ እረፍት መልስ አሁንም መደበሪያዉ ስፖርት ነዉ፡፡ጨዋታ ኖረ አልኖረ ተሰላፊ ሆነ አልሆነ ተጫዋቹ ሁሌም ከእንቅስቃሴ አይርቅም፡፡”ከልጅነቴ ጀምሬ ጫና ያለዉ ትሬኒንግ ነዉ የለመድኩት ፡-ላዛም ነዉ ካለስፖርት መዋል የማለችለዉ”ይላል፡፡

ቢያድገልኝ ኤልያሥ ዛሬ ከሳላሀዲን -አሉላ እና አበባዉ ጋር ተከላካይ ክፍሉን እንደሚመራ ይጠበቃል፡፡

1 thought on ““ግብ እናገባለን–ጋናን ለማሸነፍ እንጥራለን” የቀድሞ ኮከብ ግብ አግቢ ቢያድግልኝ ኤልያስ

Leave a Reply

Your email address will not be published.