ግብፅ ለህዳሴው ግድብ ቦንድ መግዛት እፈልጋለሁ አለች

 

Written by አለማየሁ አንበሴ

በአባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለውን የታላቁን ህዳሴ ግድብ በመቃወም ግንባታውን ለማደናቀፍ የተለያዩ ዘመቻዎችን እያካሄደች ያለችው ግብፅ፤ ግድቡ ሁለቱን ሃገራት የጋራ የሚጠቅም ከሆነ ቦንድ በመግዛት በገንዘብ ለመደገፍ እንደምትፈልግ የሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማስታወቃቸውን የዜና ምንጮች ገለፁ፡፡
በቤልጅየም ብራሰልስ እየተካሄደ ባለው የአፍረካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት የጋራ ጉባኤ ላይ ለመካፈል የተጓዙት የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ነቢል ፋህሚ  የህዳሴ ግድብን ለማስቆም ከፍተኛ ዘመቻ ሲያካሂዱ ሰንብተዋል፡፡ ሮያል ኢንስቲትዪት ፎር ኢንተርናሽናል ሪሌሽን በተባለው ተቋም ሃሙስ እለት ባደረጉት ንግግርንና፣ ሃገራቸው የህዳሴውን ግድብ ግንባታ በገንዘብ ለመደገፍ ማቀዷን አስታውቀው ግድቡ ተሰርቶ ሲጠናቀቅ ግድቡን የማስተዳደር ስልጠን ከሁለቱ ሃገራት በተውጣጣ ኮሚቴ ስር መሆን አለበት፡፡
ቀደም ሲል የህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያና የግብፅ የጋር ፕሮጀክትነት እንዲሆን ተመሳሳይ ጥያቄ መቅረቡ የሚታወስ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ መንግስት ግን ጉዳዩ ከሉአላዊነት ጋር የተያያዘ መሆኑን በማመልከት ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል፡፡  ግድቡን የጋራ ለማድረግ በሚሆንበት ጉዳይ ላይ አበክራ እንደምትሰራ የተናገሩት ነቢል ፋህሚ፤ ከግድቡ ጋር በተያያዘ የግብፅን ጥቅም የሚቀናቀን ጉዳይ ላይ ግን ትዕግስት እንደሌላት ተናግረዋል፡፡ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በጉባኤው ላይ ከአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ ካትሪን ጋር የመከሩ ሲሆን በጉባኤው ላይም የግድቡ ጉዳይ መነጋገሪያ እንደሆነ ኃላፊዋን መጠየቃቸው ተጠቁሟል፡፡ የህዳሴው ግድብ የመሰረት ድንጋይ የተጣለበት 3ኛ አመት መከበሩን በተመለከተ የግብፅ የሚዲያ ተቋማት በርካታ ዘገባዎች ሲያቀርቡ የሰነበቱ ሲሆን፤ የተለያየ አቋም አስተጋብተዋል፡፡ ግድቡ ሁለቱንም ሃገራት እንደሚጠቅም መሆኑ የሚገልፅ ዘገባ ያሰራጩ የሚዲያ ተቋማት እንዳሉዋሉ፤ ሌሎች ደግሞ ግብፅ ጥቅሟን ለማስከበር በተለይም በ1902 እ.ኤ.አ ሚኒልክ ፈርመውበታል የተባለውን ስምምነት በመጥቀስ በአለማቀፉ ፍ/ቤት ክስ እንድታቀርብ እየመከሩ ነው፡፡
የግብፅ ምሁራንና ባለስልጣናት በተደጋጋሚ የግድቡ መገንባት ማንኛውም 95 በመቶ ውሃ ፍላጎቷን ከናይል በምታገኘው ሃገራቸው ላይ የውሃ መጠኑን በ20 በመቶ በመቀነስ ጉዳት ያመያል ሲሉ እየተከራከሩ ሲሆን አንዳንድ የኢንጅነሪንግ እውቀት ያላቸው ምሁራኖቿ ግን ከዚህ በተቃራኒው ግድቡ ዓመቱን ሙሉ የውሃ ፍሰት ሳይቀንስ እንዲዘልቅ ይረዳል ሲሉ መከራከሪያ ሲያቀርቡ ተደምጧል፡፡ ግንባታው ከተጀመረ 3 ዓመት የሆነው የታላቁ ህዳሴ ግድብ 32 በመቶ ስራው የተጠናቀቀ ሲሆን ለግድቡ ግንባታ 11.5 ቢሊዮን ብር ከህብረተሰቡ ቃል የተገባ ሲሆን አጠቃላይ ወጪው 80 ቢሊዮን ብር እንደሆነ ተመልክቷል፡፡

ምንጭ፦ አዲስ አድማስ

16 thoughts on “ግብፅ ለህዳሴው ግድብ ቦንድ መግዛት እፈልጋለሁ አለች

 1. May 15, 1902 –Treaty between Great Britain and Ethiopia
  The 1902 agreement was the most controversial treaty in the colonial history
  concerning the Nile because both parties ascribe different meanings to the treaty’s
  provisions. The primary aim of this treaty was to delineate borders between Ethiopia and
  the Sudan. Again only the Article III relates to the use of Nile water. The English version
  reads: “His Majesty the Emperor Menilik II, King of Kings of Ethiopia, engages himself
  towards the Government of His Britannic Majesty not to construct or allow to be
  constructed any work across the Blue Nile, Lake Tana, or the Sobat, which would arrest
  the flow of their waters except in agreement with his Britannic Majesty’s Government
  and the Government of Sudan (“Transboundary Water”).” Ethiopia claimed that in ! 24
  Amharic the meaning indicates that the obstruction or blockage of the river was
  forbidden but the use was the water was not (“Mekonnen”). They also claim never to
  have ratified the document (“Transboundary Water”).”
  This agreement was the first to engender disputes that threatened the socio-political
  and economic dynamics of the region as well as future efforts toward cooperation.
  Sudan had created a dominant role for itself in the region and was, for the first time,
  supported by Egypt who issued threats of military retaliation. It is also possible that this
  treaty exacerbated famine already caused by Ethiopia’s poor agricultural policies
  (“Mekonnen”). Today, however, the treaty holds little meaning. Once Sudan gained its
  independence Ethiopia and other parties were quick to indicate that, since Britain no
  longer rules the Sudan, this agreement was no longer valid.

 2. ምን ላድርግ…እውነት ነው ሙት ቢወቀስ ስህተቱን አያርምም ሁኖም ተመሳሳይ ስህተት የሚሰሩ አሁንም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከግብፅ ጎን ቆመው የዚህን ግድብ መሰራት የሚቃወሙ በማየቴ ነው…ታሪክን የማንሳት አንዱ ፋይዳ ያ ነው…ስህተቱ በድጋሚ እንዳይሰራ…እሳቸውም አንዴ ሥጋና ነፍሳቸው ተዋህዶ መሃላችን ቢቆሙ ይህን ነው ሊመሰክሩ የሚችሉት…

 3. ቦንድ ለመግዛት መፈለጋቸው ጥሩ ሁኖ ሳለ ግድቡን የማስተዳደር ስልጥን መጠየቃቸው ግን ችግር አለው፡፡

 4. ጥቂት እንዳንተ/ቺ ዓይነት አስተዋዮች ላይ ነው የዚች ሃገር ህልውና የተንጠለጠለው….ያልበሰበሰ የለም፡ በስድብ እና አሽሙር ያልቆሸሸም እንዲሁ… ጥቂቶችን ግን እቺ ሃገር አታጣም…ከመጸለይ ውጪ ምን ምርጫ አለን?

 5. Habesha, Thank you for your CHEWA anegager. Minilik is my king and part of the history It brings me here. What I mentioned is the fact, When we talk about history it is only to abandon and take care of future evil deeds. I raise the issue caz it is mentioned in the article. No other leader should did the same while negotiating on our pride. But he did. That is why Egyptians get this as a legal input…Minilik did it wrong.

 6. አንድ ተረት አለ ሰውየው የምትችለውን ምታ ቢባል ሚስቱን ሊደበድብ ወደ ቤቱ ገባ፡፡ አሁን ሀገራችን የምትፈልግብን ነገር ቢኖር በአንድ ላይ ቆመን የጀመርነውን መፈጸም ንው…..ወዳጅ…ንትርክ የግብፅ ደጋፊ ያስመስላቿል…….ማውራት ስለቻላችሁ…ብቻ አታውሩ….እንደ ዜጋ…መደፈርን ..መጥላትና ለ ኢትዮጵያ መወገን ..ሌላውን (ሚስት መደብደቡን)…ትተን…ጠላትን ለመቋቋም እንስራ ተባረኩ

 7. my friend, we are living in 21 century,a century that believes in reason. Therefore,think reasonably,talk reasonably and finally you will be accepted as the 21 century men. Unless you will be accepted as animal. First of all, this country is governed not only by TPLF but also other brotherhood parties of the other brother nations. Therefore, how could you say TPLF sells the ethiopian people to Arabs? you know TPLF worries about this country as much as possible better than you. and do not forget TPLF means the Tigrian people and you are throwing bad words for these brave people even in history. This people gives their blood in history for any foreign enemies and internal enemies that are not good for the ethiopian people.

 8. @ADANE – Please you have to read more first before you tried to blame him (Minilik), he is an intelligent and a king became before the time! OK!! any way you are here and talking as you are free from any one is the one which he gave you!! Read More on EThiopian History!! Ade!!

 9. What the hell are you talking about. Read the article well. It is Minilik who sell (better to say submitted), our pride. Better to be logical sir/madam…See what you called bitches are doing, they don’t give the issue put on a table…they are working hard. Let us say a spade a spade!! Give your hate a clue.

 10. የምኒሊክ መዘዝ እችን አገር ሊለቃት አልቻለም…የአርትራ መገንጠል፤ በኦሮሞ እና ደቡቦች ላይ የተፈጸመ ግፍ ቁስል፡ የጅቡቲ መሸጥ አሁን ደሞ በወቅቱ የግብጽ ቀኝ ገዢዋ እንግሊዝ ጋር ለትውልድ ጠባሳ የሚሆን አሳፋሪ የተንበርካኪነት ውል ፈርመው ሊላ ጣታ አመጡብን…እኚ ሰውዬ በእውነት ለዚህች ሃገር ምንድነው የሰሩላት…ከትውልድ ትውልድ ከሚተላለፍ ነቀርሳቸው በስተቀር!!!

 11. TPLF you bitches you sell our lands, you sell our people to Arebs, you sell your ass and now you left with one thing that you can sell and that is Nile go a head and sell it woyanetbeduspy adergu betfelgu

Leave a Reply

Your email address will not be published.