ጌታነህ ከበደ ፕሪቶሪያን ተቀላቀለ

45159a49-c124-4efb-b29c-d2c2fc0e5a27

ሐምሌ 23፣2007

የኢትዮጵያው የፊት መስመር ተጨዋች ጌታነህ ከበደ ቢድቪስትን ለቆ ሌላኛውን የደቡብ አፍሪካ ክለብ ፕሪቶሪያ ዩንቨርስቲን ተቀላቅሏል፡፡

ጌታነህ ፕሪቶሪያን የተቀላቀለው በውሰት እንደሆነ ቢገለጽም ለምን ያህል ጊዜ እንደሆነ በግልጽ አልተቀመጠም፡፡

ጌታነህ ባለፈው ዓመት በቢድቪስት 10 ጨዋታዎችን አድርጎ 2 ጎሎችን ከመረብ አሳርፏል፡፡

ለዚህ ክለብ በመፈረሜ በጣም ደስተኛ ነኝ፣ ጠንካራ ቡድን ነው፤ በክለቡ ጥሩ ጊዜ እንደማሳልፍ ተስፋ አለኝ ፤ ቦታየንም ለማስጠበቅ ጠንክሬ እስራለሁ ሲል ከፊርማው በኋላ ጌታነህ አስታያይቱን ሰጥቷል፡፡

የፕሪቶሪያ አሰልጣኝ ማሶላ በበኩላቸው ጌታነህ በቢድቪስት የመጀመሪያ የውድድር ዓመት ጥሩ ነበር፤ ከዚያ በኋላ የመሰለፍ ዕድል በክለቡ አልተሰጠውም፤ እኛ በሌሎች ክለቦች ዕድል ሳይሰጣቸው የቀሩ ተጨዋቾችን አምጥተን ተሳክቶላቸው አይተናል፤ እሱም በፊት መስመራችን የምንፈልገው ዓይነት ተጨዋች ነው። በፍጥነት ተዋህዶ ለቡድናችን ጥራት እንደሚጨምርለት ይሰማኛል ብለዋል፡፡

ጌታነህ አዲስ የፈረመበት ክለብ ባለፈው የውድድር ዘመን በሊጉ ከሚወዳደሩ 16 ክለቦች 13ኛ ሆኖ ማጠናቀቅ ችሏል፡፡ የለቀቀው ቪድቪትስ ክለብ ደግሞ 3ኛ ሆኖ ነው የጨረሰው ፡፡

ምንጭ፡-የፕሪቶሪያ ዩንቨርስቲ

 

3 thoughts on “ጌታነህ ከበደ ፕሪቶሪያን ተቀላቀለ

Leave a Reply

Your email address will not be published.