ጋና ከዋልያ—“ኳስ በኛ ጊዜ ቀረ???”—ቅድመ ጨዋታ !!

IMG_0042

ግዬን ሆቴል በሉት ሸበሌ በሉት ሌላ ቦታ ስለ እግር ኳስ ጥናት ተደረገ ሲባል ኳስ በኛ ጊዜ ቀረ የምትለዉ አባባል ከትልልቆቹ አጥኚዎቸ አፍ አትጠፋም፡፡ለዚህ ማስረጃቸዉ ደግሞ የያኔዉ የጋና ጋዜጣ የጻፈዉ ጽሁፍ ነዉ፡፡”የኢትዮጲያ ቡድን እንደብራዚል ይጫወታል፡፡የኳስ ከህሎታቸዉ ልዩ ነዉ፡-የአፍሪካ ብራዚል ልንላቸዉ እንችላለን”የሚለዉ የጋዜጣዉ ጽሁፍ ሁሌም እነዛ ጥናቶች ላይ ይቀርባል፡፡እስኪ ጉዳዩን ነካ ነካ እናድርገዉ!!

3ተኛዉን የአፍሪካ ዋንጫ የበላዉ የያኔዉ ዋልያ ለ4ተኛዉ ወደ ጋና ያመራል፡፡6ት ቡድኖች ነበሩ የተሳተፉት፡-ከየምድቡ አንደኛ የወጡት ለፍጻሜ ያልፋሉ፡፡ዋልያዉ ጋና እና ቱኒዚያ አንድ ምድብ ነበሩ፡፡ጋና በመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮያን 2-0 አሸነፈች፡፡ከቱኒዚያ ጋር ደግሞ 1-1 ወጡ፡፡ስለዚህ የመጨረሻዉ ጨዋታ ለጋና ወሳኝ ነዉ፡፡ዋልያዉ መዉደቁን አረጋግጦ ነዉ ቱኒዚያን የሚገጥመዉ፡-እናም ቲኒዚያን እንዲያሸንፍ መላዉ የጋና ህዝብ ይፈልጋል፡፡ጋናዎች ቡድኑን በሁሉም መንገድ መለመን ጀመሩ፡፡እባካችሁ ባዘጋጀነዉ የአፍሪካ ዋንጫ እንዳንወጣ ቱኒዚያን አሸንፉልን ልመናዉ ቀጠለ፡፡

አክራ እንደደረሱ የዋልያ ተጫዋቾች ከፍተኛ እንግልት ደርሶባቸዉ ነበር፡፡ያረፉበት ሆቴል ደግሞ የመጨረሻ የደከመ ሆቴል ነዉ፡፡እናም ለበቀል ተነሳስተዋል፡፡እንዲህ ያበገናቸዉን ሀገር ቡድን ለመጣል፡፡ነገር ግን ጋናዎች የማለፍ ተስፋቸዉ በዋልያዉ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ካወቁ ጀምሮ አንክብካቤዉን አጦፉት…መንግስቱ ወርቁ የወቅቱን ሁኔታ ከwww.librogk.com ጋር በነበረዉ ቆይታ እንዲህ ያስታዉሳል!!

የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ደግሞ በጋና በመሸነፋቸዉ ለቱኒዚያ መልቀቅ ፈልገዋል፡፡እኛም ምን እናውቃለን ተናደናል፣ ተዳክመናል ለካ እነርሱ ገና ከሜዳ ሳንወጣ በፊት ከነበርንበት ከአስቃቂው ሆቴል እቃችንን በሙሉ አውጥተው ከተማ ውስጥ ትልቁ ዘመናዊ ሆቴል አስገብተውታል፡፡

መንግሥቱ፡- ቱኒዚያን እንደናሸንፍላቸው ነዋ፡፡ ቱኒዚያን እኛ 3ለ0 ከረታን ጋና ወድቆ ቱኒዚያ ያልፋል፡፡ እኛ ደግሞ 7 ነው የምንለቀው ብለን ዛትን፡፡ ያኔ ጋናዎች ፈሩን፡፡ ሆቴል እንደደረስን መድሀኒቱ፣ ሐኪሙ፣ ኦራንጁ በቃ ቤተመንግስት የገባን መሰለ፡፡

ሊብሮ እንደዚህ ሆኖ ስታገኙ ምን አላችሁ?

መንግሥቱ፡- እንደደረስን ይህንን ስናውቅ የእነርሱን ሐኪሞችና ሰራተኞች  ጋር መደባደብ ጀመርን፡፡ ያን ያህል ጊዜ በድላችሁን እንዴት አሁን ትመጣላችሁ ብለን ተጣላን፡፡ እኛ ተመካክረን 7 እንለቃለን ብለን ወስነናል፡፡ በኋላ ጋሽ ይድነቃቸው ሁኔታችንን አይቶ ጠረጠረና ሰብስቦ ‹‹ ስሙ ልጆች እንደዚህ ልታደርጉ እንደሆነ ገብቶኛ፡፡ በእርግጥ ችግር ደርሶባችኋል ግን ይህ እየተለመደ መጥቷል፡፡ አንደኛ ነገር አሁን ብትለቁ ጋናና ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ዋንጫ ሲገናኙ የመጀመሪያቸው ነው፡፡ ገና ብዙ የአፍሪካ ዋንጫ አለ፡፡ ለቱኒዚያ ብትለቁ ይህ ቲም ሁሌም እንደዚህ ነው ተብሎ ታሪካችንን ታበላሻላችሁ፡፡ ሁለተኛ ነገር ደግሞ እናንተ አብዳችኋል ወይስ ጤነኛ ናችሁ? አሁን አራት እና አምስት ብትለቁ በየት በኩል ልትወጡ ነው?›› አለ፡፡ ትዝ ሲለን ለካ ሰው ሀገር ነው ያለነው ሁኔታው አስፈራን፡፡ ግን ጨዋታው እስኪደርስ ድረስ እያስፈራራን ብዙ ተጠቀመን፡፡ ቱኒዚያን 4ለ2 አሸነፍን እኔ 2 አገባሁ ጨዋታው ከአለቀ በኋላ ህዝቡ ሜዳውን አጥለቀለቀው እያንዳንዳችን ለ40ና ለ50 እየሆኑ እየተሸከሙን ይጨፍሩ ነበር፡፡ ምክንያቱም ጋና ለዋንጫ አለፈ፡፡ በየጋዜጣው ናሽናል ሄሮ እየተባልን ፎቶአችን ወጣ፡፡ እኔም ተሸክመውኝ ሲጨፍሩ ይህን ለቀን ቢሆን ኖሮ ለ40ና ለ50 ሆነው እንደዚሁ ይቦጫጭቁን ነበር ብዬ አሰብኩ፡፡ ከዛ ማታ ቤተመንግስት ተጠርተን ፕሬዘዳንቱ ባለበት ተጋበዝን፡፡ በጣም አመሰገኑን ስለደረሰውም በደል ይቅርታ ጠየቁን፡፡

ይህ ቡድን ለጋና በሰራዉ ዉለታ የሀገር ጀግና ተብሎ በጋናዎች ተወደሰ፡፡አሁንም በጥናቶች ላይ ኳስ በኛ ግዜ ቀረ የሚያሥብል ታሪክም አስገኝትዋል፡፡በነገራችን ላይ የኢትዮጰያ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ከሀገር ዉጭ ያሸነፈዉ ጨዋታ አንድ ነዉ፡፡ያም ቱኒዚያን ለጋና ብለ ባሸነፈበት ጨዋታ፡-አስገራሚዉ ነገር ጋና ፍጻሜ ደርሶ ዋንጫ በላ፡፡5ተኛዉንም ደገመ፡፡ከዛ 3ተኛ ጊዜ በልቲ ሊያሥቀር አዲስአበባ ለ6ተኛዉ የአፍሪካ ዋንጫ መጣ፡፡ጋና በአዲስ አበባ ለፍጻሜ ደረሰ፡፡ህልሙ ተጨናግፎበት ከኢትዮያ ተመለሰ፡፡በኮንጎ 1-0 ተሸነፈ!!

ዋልያዉ ከጋና ጋር በአፍሪካ ዋንጫ  ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኘዉ በዚህ ጨዋታ ነበር፡፡አሁን ደግሞ በዚህ ትዉልድ ለ2ተኛ ግዜ ይገናኛል፡፡ዛሬም በተመሳሳይ አጋጣሚ ዋልያዉ ከጋና ጋር ይጫወታል፡፡ጋና ለማለፍ ዋልያን ማሸነፍ አለበት፡፡ዋልያዉ ደግሞ ለክብር ይጫወታል፡፡ካሸነፈ በአፍሪካ ዋንጫ ከሜዳዉ ዉጪ በማሸነፍ ከ50 አመት በኋላ ታሪክ ይደግማል ማለት ነዉ፡፡ኳስ በኛ ጊዜ ቀረም ማለት ይችል ይሆናል፡፡

 

2 thoughts on “ጋና ከዋልያ—“ኳስ በኛ ጊዜ ቀረ???”—ቅድመ ጨዋታ !!

  1. One thing I like from team Ethiopia is such kinds of articles by someone who is in contact with the team like the journalists… bu am frustrated with the lack of professionalism within the team…so I agree with begna gize kere still because whether we like it or not that team has won and brought pride in its own day. Lot more to work to build. I hope we will improve one day…

Leave a Reply

Your email address will not be published.