ጃሬ ይናገራል…”ከናይጄሪያ አጥቂዎች በላይ የኛ ተከላካዮች አስቸገሩኝ!!!”


“ስማቸዉን እየጠራ ይናገራል፤ማንጎ፤አህመድ ሙላት.ሰለሞን አንጀሎ…..እንዳሉ እኮ ተከላካዮች ነበሩ፤እናም ከአጠገቤ ራቅ ብለዉ አይጫወቱም፤ምክንያቱም የሚጫወቱ ተጫዋቾች የሉም፤ጥሩ ጥሩ ሚድ ፊልዶች አልነበሩም፤እኔ መድን ስጫወት እነ አብዲ እነ ተክሌ በቡድኑ ዉስጥ ሀይለኛ ሚድ ፊልዶች ነበሩ!!!”
ይህን የሚናገረዉ ይልማ ከበደ (ጃሬ) ነዉ፤በ1993ት ናይጄሪያ ጋር ስንጫወት 6ለ0 ስንሸነፍ 3ቱ ግብ የገባዉ እሱ ላይ ነዉ፤እኔ እራሴን ቀይሬ ነዉ የገባሁት ይላል ጃሬ..በረኛዉ ደሳለኝ ነበር፤3ት ገብቶበት ተጎዳ…ሳየዉ እኔም እሱን ማገዝ አለብኝ ብዮ ያለ መጋጫ ሜዳ ዉስጥ ገባሁ፤የሚገርመዉ ጋናዊዉ 4ተኛ ዳኛ ምንም አላለኝም…ከዛም 3ት ግቦችን አስተናገድኩ…ከኛ አጥቂዎች በላይ ያስቸገሩኝ የኛ ዲፌንሶች ነበሩ!!ይላል፤
አስቂኙ ገጠመኝ ደግሞ እንካችሁ….እየተጫወትን ያኪኒ መጣብኝ፤ሸፍኜዉ እሄዳለሁ ስል ገፈተረኝ…ከጎል ጀርባ ያሉ ጉድጉዋዶች አሉ፤የጠዘጋጁት ደጋፊዉ መጥቶ ሜዳ እንዳይገባ ነዉ፤ያኪኒ ነካ ያረገኝ እዛ ቱቦ ዉስጥ ገባሁ…አረ ኡ..ኡ.. አዉጡኝ አልኩኝ፤መንግስቱ መጥቶ ከቱቦዉ ዉስጥ አወጣኝ ….
ጃሬ የኢትዮጲያ ቡድን በካላባር ኳሱን ይዞ ከተጫወተ 2ለ1 አልያም 1ለ0 ያሸንፋል ብልዋል፤18 አመት ኳስን የተጫወተዉ በረኛን አሁን ማግኘት ከፈለጋችሁ ተክለ ሀይማኖት አከባቢ ጎማ ቤት ከፍቶ ታገኘታላችሁ!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.