ዳኛዉ አሸነፈን! ሰዉነት ቢሻዉ

 

ወደ ናይጄሪያዊዉ ጋዜጠኛ ዞሩ..ሰዉነት በጨዋታዉ ዉጤት በጣም ተበሳጭተዋል፤ኬሺን እንኳን ደስ አለህ ካሉት በሁዋላ ለተጠየቁት ጥያቄ የሰጡት መልስ ይህንን ይናገራል፤ ጋዜጠኛዉን መልሰዉ ጠየቁት…who won the match?እሱም Nigeria አለ፤ሰዉነትም መለሱ፤The refree won the match!! ዳኛዉ ፔናልቲ ከለከለን፤እንደገና ያልተገባ ሪጎሬ ሰጠብን፤ከዛም በላይ ደግሞ ቅጣት ምት የኛ ተጫዋቾች እያዘጉ እያለ አስመታብንና ገባብን!!እኔ በዳኛዉ ቦታ ብሆን ቅጣት ምቱን አስደግም ነበር ብለዋል፤ የኛ ቡድን በፕሮፌሽናሎች አልተገነባም፤የሀገር ዉስጥ ናቸዉ አብዛኞቹ…ደግሞም የናንተ ተጫዋቾች ልምደ አላቸዉ..በምንም አልበለጣችሁንም፤ይህ የኛ ቡድን ከትንሽ ጊዙ በሁዋላ ትልቅ ደረጃ ይደርሳል ብለዋል፤ በጨዋታዉ አስራት ጉዳት ደርሶበታል፤በሽንፈቱ ተጫዋቾቹ ላይ ከፍተኛ ንዴት ይስተዋላል፤አረንጓዴ ንስሮቹ ዝናቡ ካባራ በሁዋላ በስታድየሙ ብዙ ጨፍረዉ ነዉ የወጡት…..ጅቡቲ ላይ የተጀመረዉ የብራዚል ጉዞም ካላባር ላይ ተገትዋል፤

6 thoughts on “ዳኛዉ አሸነፈን! ሰዉነት ቢሻዉ

  1. በእርግጥ እንደጨወታችን ውጤቱ ኣይገባንም ቢሆንም ግን ኳስ ነውና በካ ሌላ የኛ ቀን ይመጣል። Bravo Walya

Leave a Reply

Your email address will not be published.