ደጉ እና አይናለም አይገቡም!!ቀዳሚዉ ለዉጥ የአስተሳሰብ ወይስ የግለሰብ????

IMG_4302

 

ዛሬ ዋልያዉ ከኮንጎ ይጫወታል፡፡ሰአቱ ደግሞ በሊቢያዉ ሰአት ነዉ፡፡3ሰአት በኢትዮጲያ አቆጣጠር ነዉ፡፡ተጫዋቾቹ ትላንት ማምሻዉን ወደ ከተማ ወጣ ብለዉ አየር ያግኙ ተብሎ ወደ አንድ ሞል ተወሰዱ፡፡እናም ሻይ ቡና ብለዉ ተመለሱ፡፡እግራቸዉ ብሎምፎንቴን ከገባ ጀምሮ ክልምምድ ቦታ እና ስታድየም በስተቀር የትም ረግጦ አያቅም ነበር፡፡

ዛሬ የአሰላለፍ ለዉጥ እንደሚኖር የተረጋገጠ ጭምጬ (ጭምጭምታ) አለ፡፡አይናለም እና ደጉ በሳላሀዲን እና ቢያድግልኝ ተቀይረዉ ይገባሉ፡፡በዳዊት ፍቃዱ ቦታ መሳይ የተደራቢ አጥቂ ሁኖ ይገባል እንደ-ጭምጬዉ—አሁን ጥያቄዉ ለምን እነ ደጉ ወጡ ለምን እን ሳላሀዲን ገቡ አይደለም፡፡

ለተፈጠረ ስህተት እና ለተወሰደ ብልጫ ግለሰብን ተጠያቂ አድርጎ በሌላ ግለሰብ መቀየር ችግሩን እንደማይቀርፍ የአፍሪካ ዋንጫ ተሞክሮ በቂ ነዉ፡፡የቡርኪና ፋሶ ቀን 4ት ቅያሪዎቸ ተደረጉ፡፡ቡድኑ በ10 ተጫዋች 4-0 ተሸነፈ፡፡በቀጣዩም ጨዋታ ስህተቱን በግለሰብ ቅየሪ ለመቀየር ተሞክሮ ቡድኑ ከመሸነፍ አልዳነም፡፡ባለፉት 12 ወራት ዋልያዉ ከናይጄሪያ ጋር ያደረጋቸዉን 4ት ጨዋታዎች ስናይ በ3ቱ ሪጎሬ ተገኝትዋል፡፡4 ፔናልቲ ያስገኙት 3ት የተለያዩ ሰዎች ናቸዉ፡፡እየተቀያየሩ የገቡት ተጫዋቾ ለአንድ አይነት ስህተት ከተጋለጡ እነሱን ከስህተት የሚያድናቸዉ የጨዋተዉን አስተሳሰብ መቀየር ያሥፈልጋል፡፡

ዋልያዉ ተጋጣሚዉን ለመብለጥ የያዘዉን ነገር መመርመር አለበት፡፡በረኛዉ ኳስ እንዲጀምር እንደሚፈልጉ አሰልጣኙ ተናግረዋል፡፡በተከላካዮቹ እና በረኛዉ ግን የሚግባቡበት ስልጠና እንዳልተሰጠ ሜዳ ላይ ያየነዉ ነገር ማሳያ ነዉ፡፡አማካዩ ክፍል በአጭር ርቀት ኳሶችን መቀባበል ከጠበበ ቦታ ስፔስ አስከፍቶ መዉጣት እና ተጋጣሚ ክልል ላይ በብዛት ሁኖ ማጥቃት ችግር አለበት፡፡እነዚህን ነገሮች ሰዉ በሰዉ በመቀየር መፍታት አስቸጋሪ ነዉ፡፡

በቅድሚያ ዋልያዉ ምን አይነት አጨዋወት ቢከተል ተጋጣሚዎችን በልጦ ማሸነፍ ይችላል የሚለዉ መቅደም ይኖርበታል፡፡ከዛ ወዲህ ሰዎችን ሳይሆን እንቅስቃሴዉን ተመስርቶ ቅያሪ ማድረግ ይቻላል፡፡

አሁን ግን ትላንት የተደረጉ ጥፋቶች ዛሬም ቢደገሙ አሁንም ሰዉን በሰዉ ከመቀየር በስተቀር ሌላ አማራጭ አልተቀመጠም፡፡እናም ተጫዋቹ ስህተት ላለመስራት ከሚጨነቅ ስለ እንቅስቃሴዉ ቢያሥብ ቡድኑ እድገት ይኖረዋል፡፡በአፍሪካ ዋንጫዉ በ3ት ጨዋታ 4በረኞችን ያሰለፈዉ ዋልያዉ ብቻ ነዉ፡፡4ቱም ስህተት ሰርተዋል አልያም ግብ ገብቶባቸዋል፡፡ነገር ግን ሁሉንም ለስህተት የዳረጋቸዉ የቡድኑ አጨዋወት አልታረመም፡፡ስለሆነም ሰዎችን በሰዎች ቀይሮ ስህተትን ለመቅረፍ ከመሞከር በፊት የጨዋታን እንቅስቃሴ ማጥናትና መቀየር ያስፈልጋል፡፡

የመጨረሻ አንድ ምሳሌ እንይ—የኮንጎ ቡድን በጉልበት እና ፍጥነት ጥሩ እንደሆኑ አሰልጣኝ ሰዉነት ተናግረዋል፡፡እናም እነሱን ለማቆም መላ አንፈልጋለን ሲሉም ተናገሩ፡፡አሁን ኮንጎን በፍጥነት እና ጉልበት ለማቆም ከተሞከረ ማንም ቢገባ አያቆማቸዉም፡፡መጀመሪያም የሚበልጡን በሱ ነዉና፡-ነገር ግን የነሱን ፍጥነት በዋልያዉ ኳስን መሰረት ያደረገ አጨዋወት ለማቀዝቀዝ ቢሞከር ቢያንስ ቢያንስ ብልጫዉ አይወሰድም፡፡ለዚሁ አጨዋወት የሚሆኑ ሰዎች ቢገቡም ይጠቕማሉ፡፡

ለማናኛዉም በጭምጬዉ መሰረት የዛሬ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል፡—-ጀማል…ሳላሀዲን..ቢያድግልኝ…ስዩም…አበባዉ…—አማካዮች…—-አዳነ አስራት ቱሳ እና ምንያህል..ከነሱ ፊት ፋሲካ አስፋዉ፣፣ከዛም ኡመድ ኡክሪ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡(ፎቶ -አይናለም የደጉን 2ቁጥር መለያ ለብሶ)

6 thoughts on “ደጉ እና አይናለም አይገቡም!!ቀዳሚዉ ለዉጥ የአስተሳሰብ ወይስ የግለሰብ????

  1. copy yehone astesaseb yeman copy endehone gemitu esti?bemejemeria waliya lemin 4 beregna tetekeme yemilewin manisat yegid neber kemawirat befit.engdih 4 yetebalut jemal,zerihun,sisay ena adis entsa nachew gin 4tum yegebubetin huneta sinay jemal bekey bemewitatu zerihun keburkina geba enam 4 goal silegebabet(hulum yesu chigir bayihonum) betam tichit silebezabet ke nigeria gar siay geba esum ende jemal bekey silewetana techawach kiyari silaleke adis beregna geba ahun tadiya ezih lay bemulu sinay yegidaj neger endehone manom megenzeb yichilale gin alamaw lela new.

    lelaw betam yemigermew ezih tsifu lay yetemitata asab ale esum ande< አሁን ጥያቄዉ ለምን እነ ደጉ ወጡ ለምን እን ሳላሀዲን ገቡ አይደለም;ስለሆነም ሰዎችን በሰዎች ቀይሮ ስህተትን ለመቅረፍ ከመሞከር በፊት የጨዋታን እንቅስቃሴ ማጥናትና መቀየር ያስፈልጋል;እነዚህን ነገሮች ሰዉ በሰዉ በመቀየር መፍታት አስቸጋሪ ነዉ eyale belela bekul degimo yila.yehe min malet new sew besew bekeyer kalihone mefithew yemin ለዚሁ አጨዋወት የሚሆኑ ሰዎች ቢገቡም ይጠቕማሉ malet new tadiya?kelay ለምን እነ ደጉ ወጡ ለምን እን ሳላሀዲን ገቡ አይደለም ketebale meliso leloch ሰዎች ቢገቡም ይጠቕማሉ malet min male yihon? esti bedenb asabun fetishut ebakachihu

  2. Saeid kiar Balege neh, siwr alama aleh “…በዳዊት ፍቃዱ ቦታ መሳይ የተደራቢ አጥቂ ሁኖ ይገባል…” dawit ezih wust min yseral? botawn man setew lesu? belibiyaw chewatas ye dawitn bota yeyazew man neber? Bemar liws merz endih new. Beafrica wancha “yeteserekew bota yimeles…etc” eyalk sitachberebir neber yasaznal. Beftnet rashn bitarm tiru new ante ebab…

Leave a Reply

Your email address will not be published.