ደካማዉ እግር ኳሳችን ከፖለቲካ ስርአታችን ያለዉ ርቀት

ethiopia-football-vs-ethiopian-politics

በአዱኛ ሂርፓ

ርቀት አንድ ፡ – የተጫዋች ምርጫ
ሃገርን ወክለዉ ሜዳ ላይ የሚጫወቱ ተጫዋቾቻችንን ስናይ ከእኛ የተሻሉ እንደሆኑ እናምናለን ፡፡ ምናልባት ቅር ቢለን ሁለት ወይም ሦስት ተጫዋቾች ለጊዜው ስላልተመረጡ ይሆናል፤ በሂደቱም ለመመረጥ የተጫዋቾቹ ድርሻ ለቦታቸው ያላቸው በቃት ብቻ እንደሆነ ልብ ይሏል፡፡ በፓለቲካችን ሜዳ መቼ ይሆን በስራ ብቃት ፣ በሀቀኝነት፣ በህዝብ አገልጋይነት ከሁላችን የተሻሉትን የምንመርጥበት ስርአት የሚኖረን?

ርቀት ሁለት፡ – ታዳጊ ተኮር ስራ
በት/ቤት እና በጥቂቱም ቢሆን ለታዳጊዎች የተዘረጋው ፕሮጀክት ይብዛም ይነስም ለእግር ኳሳችን አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ለነገዉ ፓለቲካችን ማማር አርቀን አሰበን ልጆቻችን ልብ ዉሰጥ በተግባር እና በቃል ከሙስና እና ከዘረኝነት የጸዳ ክብር ለሰዉ መሰጠትን ፡ፍቅር እና ይቅርታን እንዲሁም ለፍትህ መቆምን የምንዘራ ቤተሰቦች ምን ያህሎች ነን?

ርቀት ሶስት፡ – የሚዲያ ነጻነት
ለእግር ኳሱ ያለው የሚዲያ ሽፋን ሂሱና ትንተናው የኳስ አፍቃሪው ስሜቱን የሚገልጽበት መንገድ ያስቀናል፡፡ ይሄ ነጻነት በፓለቲካችን ውስጥ ሽታውም የለም፡፡ ክፍተቱን የሚያሳዩ በምዕራቡ ዓለም አጠራር “watch dogs” እየከሰሙ ታማኝ ደጋፊዎች “Lap dogs”እያበቡ የሚሄዱበት ስርዐት የት ያደርሰናል? አንድ ተክል ለማደግ ጸሃይ ውሃ እና ዓየር እንደሚያስፈልገው ዘላቂ እድገትና ልማን ያለግልጽነት፣ ተጠያቂነትና ኃላፊነት መጠበቅ የዋህነት ነው፡፡
እንግዲህ የፖለቲካችንን ስርአት በብዙ ርቀት የሚመራዉ እግር ኳሳችን በአለም አቀፍ መድረክ ሲለካ እንዲህ ከተፈተነ ፓለቲካችን በማያከራክር መለኪያ ቢለካ ዉጤታችን የቱጋ ይሆን?

በዚህ አዲስ አመት እንደወትሮው መልካም እንዲሆን መመኘታችን የሚጠበቅ ነው፡፡ነገር ግን ከምኞት ባሸገር በጎ ዘመን እንዲወለድ ካልተፈጠሩ ቀኖቻችን ጀርባ የተለወጠ አስተሳሰብ ያስፈልጋል፡፡ ቢላ ቢላን እንዲስለው በመቻቻል፣ በመደማመጥ ፣ በመከባበር የሆነ ዉይይት ትልቅ ስፍራ ሊሰጠዉ ይገባል ፡፡ እግዚአብሄር ምድራችንን እዉነት እና ምህረት የሚተቃቀፉበት ጽድቅ እና ፍትህ የሚስማሙበት ያድርግልን ፡፡መልካም አዲስ ዓመት !

1 thought on “ደካማዉ እግር ኳሳችን ከፖለቲካ ስርአታችን ያለዉ ርቀት

Leave a Reply

Your email address will not be published.