የ40 /60 ፈተና – በአርኪቴክት ዮሐንስ መኮንን

40-60 Buildings in Addis Ababa

40-60 Buildings in Addis Ababa

አዲስ አበባ ከተማን ሰንገው ከያዝዋት ችግሮች መካከል የመኖሪያ ቤት ችግርን የሚስተካከለው ያለ አይመስለኝም፡፡ ዜጎች ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ገቢያቸውን ለቤት ኪራይ ስለሚያውሉ ቀጣይነት ያለው ሃብት መፍጠሪያ አቅም ነስቷቸዋል፡፡ የኽም ኑሮአችንን በመከራ የተሞላ አድርጎብናል፡፡ ይኽንን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት መንግስት የቤቶች ግንባታ ፕሮገራም መንደፉ የሚያስመሰግነው ቢሆንም ወደ መሬት ያወረደበት መንገድ ግን አነጋጋሪ ሆኖ የሚቀጥል ይመስለኛል፡፡

ከነኚህ ፕሮግራሞች አንዱ የሆነው በተለምዶ 40/60 በመባል የሚታወቀው የቤቶች ግንባታ በመሠረታዊ የዲዛይን ስህተቶች የተሞላ እና ስህተቶቹን ለማረም የተኬደበት መንገድም ሌላ ተጨማሪ ስህተት የፈጠረ ይመስለኛል፡፡ ለመሆኑ ስህተቶቹ ምንድናቸው?

1) ፕሮግራሙ እና የተሠሩት ቤቶች አይተዋወቁም፡፡ ዜጎች ‹‹ታገኙታላችሁ›› በተባሉት አጠቃላይ የወለል ስፋት መሠረት በባንክ መቆጠብ መጀመራቸው ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ በጥድፊያ እንዲገነቡ የተደረጉት አፓርታማዎች ግንባታቸው ከተጋመሰ በኋላ የወለል ስፋታቸው የተዛነፈ መሆኑ በመታወቁ እንደምንም ተብቃቅተው መንግስት ከዜጎች ጋር በተፈራረረመው ውል መሰረት እንዲስተካከሉ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ (በአጭሩ ለማስረዳት ጃኬት ለማሰፋት ለተዋዋለ ደንበኛ ካፖርት ከሠፉ በኋላ ስህተቱን ለማረም ካፖርቱን በመቆራረጥ ሌሎች ጃኬቶች ለማውጣት እንደመሞከር ያለ ነው፡፡ከካፖርት ጃኬት ይወጣ ይሆናል፡፡ ግን የተጨማደደ እና የተጣበበ መሆኑን መቀበል ይኖርብናል፡፡ በ40/60 እየሆነ ያለውም ይኼው ነው፡፡)
2) የአደጋ ጊዜ ማለጫ የላቸውም፡፡ ግንባታቸው ከተጋመሰ በኋላ የታወቀውን የአደጋ ጊዜ ማመለጫ ደረጃ ቀድሞ ባልታሰበበት ሁኔታ ‹‹እንደምንም ብላችሁ አንድ ጥግ ፈልጉለት›› በማለት ለመፍታት መሞከር መፍትሔውን ሰንካላ ማድረጉ አይቀሬ ነው፡፡
3) የቆሻሻ ማስወገጃ ሊኖራቸው ይገባ ነበር፡፡ 12 ፎቅ ተገንብቶ ነዋሪዎች የሚያስወግዱትን ደረቅ ቆሻሻ በፌስታል ቋጥረው እንዲወርዱ ማሰብ ተገቢ አይደለም፡፡ በቀላሉ የቆሻሻ ማንሸራተቻ (Trash shooter) ማሰብ ይገባ ነበር፡፡ 
4) ለሁሉም በሽታ አንድ ክትባት! እንኳንስ ህንጻ ዛፍ እንኳን ሲተከል ከቦታ ቦታ የተለያየ እና ተስማሚ ዓይነት ይመረጣል፡፡ አሁን የሚሠሩት አፓርታማዎች ግን ለሁሉም የንፋስና የፀሐይ አቅጣጫዎች፣ ለአፈር እና ለድንጋይ ዓይነቶች እንዴት አንድ ዲዛይን ይሠራል? ይህን ያህል ጥድፊያስ ም ለማትረፍ ነው?
5) ንድፉ አያምርም፡፡ ይህን የመሰለ ከፍተኛ በጀት እና ጉልበት የሚፈስበት ብሔራዊ ዕቅድ በቂ የባለሙያዎች ክርክር እና ጥናት ሳይደረግበት በጥድፊያ በተሞላ ውሳኔ ወደ ተግባር መገባት አልነበረበትም፡፡ ሲሆን ሲሆን ከፍተኛ አማካሪዎች የተሳተፉበት የዲዛይን ውድድር ተደርጎ የተሻለው ሊመረጥ ይገባ ነበር !

የእነኚህ ሁሉ ችግሮች ምንጮች ሁለት ናቸው፡፡ ጥድፊያ እና አነስተኛ ግምት ! መፍትሔው ከዚሁ ይመነጫል፡፡ ሰከን ብሎ ማሰብ እና ተገቢው ትኩረት! ሀሳቡ የፓርቲ ሳይሆን የመላእክት እንኳን ቢሆን አፈጻጸሙ ከተበላሸ ፈተናውን ወደቀ ማለት ነው ፡፡

 

Source: አርኪቴክት ዮሐንስ መኮንን

6 thoughts on “የ40 /60 ፈተና – በአርኪቴክት ዮሐንስ መኮንን

 1. Sir, It’s a good comment but imbalance perspective. Though your comments looks constructive,no alternative solution as an architect.You R also the one who is responsible as an Ethiopian.As to me the project should never be left to some groups. Anyways there was LDP & NHD discussion & evaluation at various levels.I can confirm this with tangible documents. The geotechnical activities have been made on the right truck, too. What ever it is, if u are an extrovert,logical,positive & …man
  ,you can discuss openly after detail professional elaboration given to you on your comment.

 2. ሃይ ብሮ ማነው የሳይዝ ችግር አለ ያለህ ; ለነገሩ አልፈርድብህም ያለመረጃ ስትዘባርቅ የመጀመሪያው ሰው አይደለህም ፡፡ግን አንድ ነገር ልንገርህ 2006 ምዝገባ ተካሄደ እንጂ ስራው የተጀመረው በ2005 ነው ፡፡አንተ እንዳልከው በጥድፊያ የሚካሄድ ነገር የለም ፡፡ለዛ ለዛ ማ ጸሃይ ሪል ስቴት ይቀድመናል ፡፡ተሳክቶ ከዛም በፊት ቢያልቅ መልካም ነበር፡፡ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ ዲዛይን ለማስተቸት መስቀል አደባባይ ህዝብ መጠራት አለበት እንዴ ለማንኛውም ጋሽ አርክቴክት ፖስት ያረግሺው የአፈር ምርመራ ስራ ፎቶ ነው እና http://www.aashde.gov.et ላይ አልቀው ለመተላለፍ የደረሱ ቤቶች ፎቶ ታገኛለህ፡፡ እሱን እያየህ ቡጨቃህን ቀጥል ፡፡አዋቂ መሆን እንጂ መምሰል አያዋጣም…. Tnx

 3. I was there in the beginning it looks like a construction hidden from Ethiopians
  the fault is not from the govt but from a person who took the responsibility as an agent
  and collect his colloquies and said go go go go go go and no one asks where, why, how, etc.

 4. well Architect yohaness, the critics that you have stated are quite right but very narrow & sound biased with regards to consideration to many situations at current time. i’m not justfying the mistakes like lack of fire escape stairs or garbage shoots….or the lack of debate by professionals but relative to building cultures of other privately owned buildings and in view of the grave housing issue we have, this are fairly good buildings…. and i dont think the concept of realistic finance make such sense to many architects… so i hope the second and third phase of this projects do learn a lot but i found your critic a little shallow.

 5. It is good view, but z ethiopian officials has no ear to listen such critics because whe u critisize they label u as opposing them not their ideas.

Leave a Reply

Your email address will not be published.