የፍትህ ሚኒስቴር የአቶ ተማም አባቡልጉን የጥብቅና ፍቃድ ለ1 አመት ከሰባት ወር አገደ

Temam Ababulgu

Temam Ababulgu

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 2 ፣ 2007 (ኤፍ ቢ ሲ) የፍትህ ሚኒስቴር በጥብቅና ሙያ የሚተዳደሩት አቶ ተማም አባቡልጉ አባዲኮን ከስነ ምግባር ጋር በተያያዘ ለ1 አመት ከሰባት ወር የጥብቅና ፍቃዳቸውን አገደ።

ከፍትህ ሚኒስቴር የወጣው ደብዳቤ እንደሚያሳየው የፈደራል የጠበቆችና የዲሲፕሊን ጉባኤ በግለሰቡ ላይ የቀረቡ የስነ ምግባር ክፍተት ጥቆማዎችን ሲመረምር ቆይቷል።

በዚህ መሰረት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አዋጅ ቁጥር 192/92 አንቀፅ 24(3ለ 2) መሰረት በማድረግ አቶ ተማምን ከሰኔ ወር 2007 ጀምሮ ለ1 አመት ከሰባት ወር የጥብቅና ፍቃዳቸውን አድጓል።

የእግድ ደብዳቤው ለሚመለከታቸው አካላት መገለፁ ከሚኒስቴሩ የወጣው ደብዳቤ ያመለክታል።

Source: FBC

1 thought on “የፍትህ ሚኒስቴር የአቶ ተማም አባቡልጉን የጥብቅና ፍቃድ ለ1 አመት ከሰባት ወር አገደ

Leave a Reply

Your email address will not be published.