[የግል ምልከታ] የዘረኝነት ሀሳብ ጽዳት ዘመቻ ወቅታዊ ነዉ

Addis Ababa Steet Cleaning - 3

ከአዲስ ካሳሁን

“ጡ- ጡ- ጡ- ጡ- ጡ – ጡ -ጡ -ጠ- የከተማ ፅዳት የአዲስ አበባ ጽዳት” አሉ ጋሸ አበራ ሞላና ወዳጆቹ በአንድ ወቀት አዲስ አባባን ከቆሻሻ ለመታደግ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በአንድ ወቅት የሊቢያዉ ፕሬዘዳንት የነበሩት መሐምድ ጋዳፊ የአፍሪካ ህብረትን ወደ ሊቢያ ከተማ እንዲዛወር በጀመሩት እንቅስቃሴ “በዚች በቆሸሸች ከተማ እፍሪካ ህብረት እንዴት ይቀመጣል ስለዚህ ጽ/ቤቱ ሊቢያ ይሁን” ብለዉ ሃሳብ ሲያቀርቡ ኢተዮጵያን ለ 20 ዓመት ያህል የመሯት አቶ መለስ ዜናዊ “ከተማችንንስ እናፀዳታለን የማይፀዳዉ ግን ቆሻሻ ጭንቅላት ነዉ” ብለዉ ጥሩ መልስ ሰጥተዉልን ነበር፡፡ ሁለቱም ዛሬ በሂወት የሉም፡፡ ለዝች አጭር ህይወት መጥፎ ማሰብ ምን ይሰራል?

ታዲያ ዛሬ ልክ እንደ ጋሸ አበራ ሞላ የጽዳት ዘመቻ ሁሉ ጡ- ጡ- ጡ- ጡ- ጡ- ጡ- ጡ- ጡ የዘረኝነት ሀሳብ ጽዳት ዘመቻ ቢባል ወቅታዊና ትክክል ነዉ፡፡ ፌስቡክ መጠቀም ከ ጀመርኩ ዓመታት አልፈዋል፡፡ በነዚህ ጊዚያቶች ከፌስቡክ በዙ የሚባሉ ቁመነገሮችን አግኝቻለሁ፡፡ በዘመናዊ ቴክኖሎጅ ኢንፎረማሽን ማግኘት ነገሮችን ፈጣን ከማደረጉ በተጨማሪ እሩቅ ለሩቅ ያሉተን ሰዎች በአንድ መደረክ ላይ ያገናኛል፡፡ ግን በሌላ በኩል ፌስቡክና የተለያዩ ማህበራዊ ድህረ ገፆች በአንዳንድ ሰዎች በአሉታዊ መልኩ የሚጠቀሙባቸዉና እሾክ የሚዘሩባቸዉ ትላልቅ መሬቶች ሆነዋል ቢባል የተጋነነ አይደለም፡፡ ስልችት እሰከሚል ድረስ እና ማየትና ማንብብ እስከሚያሰጠላ ድረስ በነዚሀ አዉድማዎች ላይ ለትዉልድ የማይጠቅሙ የነገር አንክርዳዶች ይወቃሉ ይደቆሳሉ፡፡

በአብዛኛዉ እነዚህን ድህረ ገጾች የሚጠቀመዉ ህብረተሰብ “የተማረ“ የሚባል ነዉ፡ ግን ከተማረ የማይጠበቅ ለሃገር እና ለህዝብ አንድነት የማይጠቅም የዘረኝነት እና ጎጠኝነት ወሬ አናፋሹ እሱ እራሱ የተማረ ተብዬው ሲሆን ከመረበሽም በላይ ትልቅ የጭንቅላት ኪሳራና ዝገት መሆኑ ግልፅ ነዉ፡፡ ዛሬ በዘመነ ግሎባላይዜሽን ስለ ቀበሌ እና ጎጥ እያወሩና ጡሩንባ እየነፉ ሰላም የነበረዉን እና የሚፋቀረዉን ህዝብ ሆድና ጀርባ እንዲሆኑ ማደርግ ምናልባት ጠለቅ አድርጎ ቢታስብ ሰይጣናዊ ክፍ ሰራ ነዉ፡፡ ጭንቅላት ያለዉና ቆሞ የሚሄድ ሰዉ በዘር እና በቋንቋ አለያይቶ ምስኪኑን ህዝብ ምንም ወደ ማያዉቀዉ የዘረኝነት ጭለማ ዉስጥ ጎትቶ ማሰገባት ትልቅ የታሪክ ኪሳራም ነዉ፡፡

ብዙ የሌላ ሀገር ዜጎች ፌስቡክ ጋደኞች ይኖሩናል፡ ግን እነዚህ ሰዎች ይህንን ድህረ ገጽ የሚጠቀሙበት በአብዛኛዉ ለ አዎንታዊ ነገር ነዉ፡፡ ምናልባት ሀገራቸዉ ዉስጥ ጎሳና የተለያዩ ቋንቋ ተናገሪ ህዘብ ባለመኖራቸዉ አይመስለኝም ግን ይህ ነገር ለነሱ ከሀገር ተሻግሮ ትልቅ የመነጋገሪያ ነጥብ ሰላልሆነ ነዉ፡፡ በተቃራኒዉ ወደ እኛዉ ሀገር ተጠቃሚ ስንመጣ በዙ በጣም በዙ የዘረኝነት አካዉንት፤ፔጅ እና ግሩፖች ተከፍተዋል፡፡ አንድነትን የማይታያቸዉና ማባላት ስራቸዉ የሆነ የዘረኝነት መርዝ ተፊዎች በኛ ሀገር ነዉ ሽርጉድ የሚሉት፡፡

ግን አሁን ስንት የሚወራና የሚሰራ ነገር እያለ፡ ከሰዉነት ደረጃ ወረድ ብለን ከብሄራዊነት ይልቅ ሰለ ቅርነጫፎቹ ብሄር እያወሩ እኔ የእገሌ ጎራ ልጅ ነኝ ምናምን እያልን መቀባጠሩ ምን ይጠቅማል? ደግሞ በእንደዚህ አይነት እንቅስቃሴ የትኛዉ ሀገር ነዉ ያደገዉ? ገና በልተን ሳንጠግብ ስለ ጥቃቅን ነገሮች ስናወራ ሆዳችን ይሞላ ይሆን? ብዙ ለሀገርና ለወገን የሚጠቅም ነገር መስራት እየተቻለ በጥቃቅን ነገሮች ላይ ትኩረታችንን ሰጥተን በዚህ በ21ኛዉ ክፍለ ዘመን የዘቀጠ ሃሳብ ይዞ መራመድ ጨለምትኝነትአባ ጠባብነት ይመስለኛል፡፡

ስራቸዉ፤ ግባቸዉ ፤ እንዲሁም መተደዳሪያቸዉ ይህ ጭፍናዊ የማለያየት ፕሮፖጋንዳ የሆነ ግለሰቦች መኖራቸዉ የማይካድ ሃቅ ቢሆንም፡ የሚያሳዝነዉ ግን ጥራዝ ነጠቅ እና በ “አሉ፤ አሉ” መንፈስ የነሱን ፍልስፍና አናፋሹ መብዛቱ ነዉ፡፡ አንዳንዶቹ በ ፖለቲካው ዓለም ኪሳራ ሲያጋጥማቸዉ ህዝብን ከህዝብ አባልቶ ቤተ መንግሰት ለመግባት የሚያደርጉት የዘረኝነት የማያዋጣ የጭለማ ሩጫ ነዉ፡፡ እነሱ ለጥቅማቸዉ ነዉ። አራጋቢዉ ምን ለማግኘት ነዉ?

ዘረኝነት በምድር ሆነ በሰማይ የሚያስጠይቅ ዲያብሎሳዊ አስተሳሰብ ነዉ፡፡ አንድ ሰዉ እኔ ከ እነ እገሌ ብሄር ልወለድ ብሎ ፈጽሞ የተወለደ የለም፡፡ ሰዉ በሰዉንቱ እንጂ በሚናገረዉ ቋንቋ እና ከየት መጣ ተብሎ መገልል የለበትም፡፡ ስለዚህ የፌስቡክ ብሄረተኞች መጀመሪያ እሰኪ በቀን 3 ጊዜ ሰለመብላት እንማከር ቀጥሎ ሌሎች ጎደሎቻችንን እንሙላ፡፡ በሰዉ ሃገር ላይ ወንድም እና እህቶች ህይወታቸዉ በመንግደ ላይ ሲረግፍ እያየን እኛ እዚሀ የትርኪምርኪ እሳት እናነዳለን፡፡ እናስብብት አንድነት እንጅ መለያየት አይጠቅመንም!!!
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

2 thoughts on “[የግል ምልከታ] የዘረኝነት ሀሳብ ጽዳት ዘመቻ ወቅታዊ ነዉ

  1. It is a nice look. Sometimes it is easy to indicate a problem rather than giving a solution. But what we deserve is the solution.

Leave a Reply

Your email address will not be published.