የግላኮማ በሽታ

glaucoma

glaucoma

(በዳንኤል አማረ ©ኢትዮጤና)

ለበለጠ የጤና መረጃ ይህን ገጽ ላይክ ያድርጉ www.facebook.com/EthioTena

ግለኮማ የአይንን ኦፕቲክ ነርቭ የሚጎዳ በሽታ ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የሚመጣ ችግር ነው፡፡ በአይን ውስጥ ከሚፈጠር ግፊት ጋር ይያያዛል፡፡ ግላኮማ በዘር የሚተላለፍ በሽታ ነው ነገር ግን ዕድሜዎ እስከሚገፋ ድረስ በሽታው ላይከሰት ይችላል፡፡

የአይን ውስጥ ግፊት መጨመር ኢንትራኦኩላር ፕሬዥር(Intraocular Pressure) ይባላል ምስልን ወደ አእምሮ የሚያስተላልፈውን ኦፕቲክ ነርቭ (Optic Nerve) ይጎዳል በአይን ውስጥ ግፊት መጨመር ምክንያት የኦፕቲክ ነርቭ ጉዳት የሚቀጥል ከሆነ ግላኮማ ቋሚ የሆነ የአይን መጥፋት ችግር ያስከትላል፡፡ ይህን ችግር በወቅቱ የማንታከመው ከሆነ ግላኮማ በጥቂት አመታት ውስጥ የአይን መታወር ያስከትላል፡፡

በግላኮማ የተያዙ ብዙ ሰዎች ምንም አይነት ምልክት ወይም ህመም በግፊት መጨመር ምክንያት አይታያባቸውም ስለዚህ በተወሰነ የጊዜ ልዩነት የአይን ሃኪም ጋር መሄድ አለብን ይህም በግላኮማ ምክንያት የአይን እይታችንን ሙሉ ለሙሉ ከማጣታችን በፊት ለመታከም ይረዳናል፡፡

በአይን ውስጥ ግፊት ለምን ይጨምራል?

ግላኮማ የአይንዎ ግፊት በሚጨምርበት ጊዜ ይፈጠራል ይህም የሚሆነው የአይን ፈሳሽ በፊት ለፊት የአይን ክፍል እንደልብ መዘዋወር ሲሳነው ነው፡፡ ይህ ፈሳሽ አኳስ ሁመር(Aqueous Humor) ይባላል ከአይን ውጪ በተገጣጠሙ የቱቦ መስመሮች ይፈሳል እነዚህ መስመሮች ከተዘጉ ፈሳሹ ይከማችና ግላኮማ ይፈጠራል፡፡ የዚህ መዘጋት ቀጥተኛ ምክንያት አይታወቅም ነገር ግን በዘር የተወረሰ እንደሚሆን ይገመታል፡፡

በግላኮማ የሚያዙት እነማን ናቸው?

ግላኮማ እድሜያቸው ከ40 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎችን በብዛት ያጠቃል፡፡ በተጨማሪም ወጣቶችን፣ ልጆችንና ህፃንት ላይ አልፎ አልፎ ይከሰታል፡፡ በአፍሪካ አሜሪካውያን ላይ ግላኮማ በተደጋጋሚና በልጅነታቸው የሚከሰት ሲሆን እይታቸውን የማታት እድላቸው በጣም ከፍተኛ ነው፡፡

የሚከተሉት በግላኮማ የመያዝ እድላችንን ይጨምራሉ፦

 • እድሜዎ ከ40 ዓመት በላይ ከሆነ
 • ከቤተሰብዎ መካከል በግላኮማ የተያዘ ካለ
 • ደካማ የሆነ እይታ ካለዎት
 • የስኳር በሽታ ካለብዎት
 • የስቴሮይድ(Steroid) መድሃኒቶች የሚወስድ ከሆነ፦ ፕሪዲኒሶን(Prednisone)
 • በአንድ ወይም ሁለት አይናችን ላይ ጉዳት ካጋጠምዎት

የግላኮማ በሽታ ምልክቶች

ለአብዛኛዎቹ ሰዎች የግላኮማ በሽታ በጣም ጥቂት ወይም ምንም አይነት ምልክት አይታይባቸውም፡፡ የመጀመሪያው የግላኮማ በሽታ ምልክት ዳር ወይም ጎን ላይ ያለን ነገር ለማየት አለመቻል ነው ይህም በሽታው እስከሚሰራጭ ድረስ አይታወቅም፡፡

የሚከተሉት ምልክቶች ካለብዎት በፍጥነት የህክምና እርዳታ ያግኙ፦

 • መብራት ስናይ ክብ ብርሃን ማየት
 • የእይታ መጋረድ/አለማየት
 • የአይን መቅላት
 • ጭጋግ የሚመስል አይን ላይ መታየት(በተለይ በህፃናት ላይ)
 • ማቅለሽለሽ ወይም ማስመለስ
 • የአይን ህመም
 • የእይታ መጥበብ

 

የግላኮማ በሽታ ምርመራ

የግላኮማን በሽታ ለመመርመር የአይን ሃኪም የእይታዎ ሁኔታን እና አይንዎን በተለጠጠ ፑፒልስ ምርመራ ያደርግልዎታል፡፡ የአይን ምርመራው ትኩረት የሚያደርገው በኦፕቲክ ነርቭ ዙሪያ ሲሆን በግላኮማ ህመም ጊዜ የተለየ መልክ አለው፡፡ በተጨማሪም የኦፕቲክ ነርቭ ፎቶግራፍ ምርመራውን ከማገዙም በላይ የኦፕቲክ ነርቭ የመልክ/እይታ ለውጦችን ለመከታተል ይረዳል፡፡ ሀኪሙ በተጨማሪም ቶኖሜትሪ(Tonometry) የተባለ ምርመራ የአይን ግፊትን ለመለካት ይሰራል፡፡

የግላኮማ በሽታ ህክምና

የግላኮማ በሽታ ምርመራ የአይን ጠብታ፣ ላሰር ሰርጀሪ ወይም ማይክሮ ሰርጀሪን ያጠቃልላል፡፡

የአይን ጠብታዎች፦ እነዚህ በአይን የፊት ክፍል ላይ የፈሳሽ መፈጠርን ይቀንሳል ወይም የፈሳሽ መውጣትን/መወገድን ይጨምራል፡፡ የግላኮማ የአይን ጠብታዎች የጎንዮሽ ጉዳቶች፦ አለርጂ፣ የአይን መቅላት፣ የአይን ማቃጠልና የእይታ መደብዘዝን ያጠቃልላል፡፡ አንዳንድ የግላኮማ መድሃኒቶች ልብና ሳንባን ሊያውኩ ይችላሉ፡፡

ላሰር ቀዶ ጥገና (Laser Surgery) ፦ ግላኮማን ለማከም የሚደረግ የላሰር ቀዶ ጥገና ከአይን ውስጥ ፈሳሽን ለማውጣት ወይም የፈሳሽ መታገድን ለማስወገድ ይደረጋል፡፡

ማይክሮ ቀዶ ጥገና (Microsurgery) ፦ ትራብኩሎክቶሚ በተባለ የቀዶ ጥገና መንገድ ሲሆን ፈሳሹን ለማስወገድ አዲስ የመፍሰሻ መስመር መፍጠር/መስራት ነው፡፡ በዚህም መንገድ በአይን ውስጥ የሚፈጠረውን ግፊት በማስወገድ ግላኮማን ያስወግዳል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ይህ ቀዶ ጥገና ላይሳካ ይችላል፡፡

የህፃናት/ውልደት ግላኮማ (Infant or Congenital Glaucoma) ፦ ይህ ማለት ሲወለዱ የግላኮማ በሽታ ተጠቂ ሆነው ይወለዳሉ፡፡ ይህ በሽታ የሚታከመው በመጀመሪያ በቀዶ ጥገና ነው ምክንያቱም የዚህ ችግር መነሻው የፍሳሽ መስመር ችግር ስለሆነ ነው፡፡

ግላኮማን መከላከል እንችላለን?

ግላኮማን መከላከል አንችልም ነገር ግን በጊዜ ከተመረመርንና ከታከምን በሽታውን መቆጣጠር እንችላለን፡፡

በግላኮማ የተያዙ በሽተኞች እጣ ፋንታ

በግላኮማ ምክንያት የሚከሰት የእይታ ማጣት የማይመለስና እንደገና ወደ እይታ መመለስ አይቻልም ስለዚህ በተሳካ ሁኔታ የአይን ግፊትን መቀነስ በግላኮማ ምክንያት የሚከሰትን እይታ ማጣትን ለመከላከል ይረዳል፡፡ ግላኮማ ያለባቸው አብዛኛዎቹ ሰዎች ህክምናቸውን በሚገባ ከተከታተሉና መደበኛ የአይን ምርመራ የሚያደርጉ ከሆነ የአይን እይታቸውን አያጡም፡፡

መልካም ጤንነት!!

ለበለጠ የጤና መረጃ ይህን ገጽ ላይክ ያድርጉ www.facebook.com/EthioTena

– See more at: http://www.ethiotena.net/wordpress

5 thoughts on “የግላኮማ በሽታ

 1. It is a very good information to me indeed, as I’m victim to this problem, moreover I’m now using a drug called Timolol 0.5%w/v and very recently advised to make microsurgery. Where do you think is a private clinic for making surgery in Addis, please, inform me via my e-mail address the address of the right hospital/clinic to this problem
  thank you
  Melese Negash

 2. ጥያቄ- በሽታው ከያዘኝ /ካወቅሁት 4 ዓመት ሁኖኛል ሁለት አይነት መድሀኒት እየተጠቀምሁነው የመድሀኒቱ አይነት 1ኛ ቲሞል-0.5 2ኛ ካርፒን 4% ሲሆን በየ 3ወሩ እታያለሁ ግፊቱ አንዲየ ይቀንሳል ሌላ ጊዜ ይጨምራል መድሀኔቱ በጣም አይኔን ያቃጥለኛልያሳከኛል አንዳንድ ጊዜ ሳይ በተለይ ብርሃን ሲበዛ አይኔ እንደመጭበርበር ይላልእርሰዎ ምን ይመክሩኛል ከምን ከምን ልቆጠብ መንግስት ሠራተኛ ነኝ የኮፒዩተር ባሞያ ስለዚህ ምን ላድርግ?

 3. ስለ ግላኮማ በሽታ የተሰጠው ማብራሪያ የማላቀውን እንደድናውቅ አድርጎኛል እኔም የዚህ በሽታ ተጠቂ ስለሆንኩ፡፡ እናመሰግናለን

Leave a Reply

Your email address will not be published.