የኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ቡድን ድሬደዋ ላይ የሱዳን አቻውን ያስተናግዳል

Eth U23

አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ ጨዋታው በድሬዳዋ መደረጉን አልወደዱትም አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ ጨዋታው በድሬዳዋ መደረጉን አልወደዱትም

በእኛ የጊዜ አቆጣጠር ከመጪው ነሐሴ 29፣ 2007 እስከ መስከረም 9፣ 2008 (በፈረንጆች የጊዜ አቆጣጠር ከሴፕቴምበር 4 እስከ 19፣ 2015) በኮንጎ ብራዛቪል አስተናጋጅነት በሚካሄደው 11ኛው የመላው አፍሪካ ጨዋታ ላይ ከሚካተቱት ውድድሮች አንዱ በሆነው የእግር ኳስ ፉክክር ላይ ተሳታፊ ለመሆን የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ (ከ23 ዓመት በታች) ቡድን ዕሁድ የካቲት 15/2007 በ10፡00 ሰዓት ድሬዳዋ ላይ ከሱዳን አቻው የማጣሪያ ግጥሚያውን ያደርጋል፡፡ የዛሬ 50 ዓመት ዘንድሮ ውድድሩን በምታዘጋጀው ኮንጎ ብራዛቪል መካሄድ የጀመረው የመላው አፍሪካ ጨዋታ ተወዳጁን እግር ኳስ እና የእኛውን አትሌቲክስ ጨምሮ ከ20 የበለጡ ስፖርታዊ ውድድሮች የሚደረጉበት፣ በየአራት ዓመቱ የሚካሄድ፣ በፖሊቲካዊ ጉዳዮች ምክንያት ከማትሳተፈው ሞሮኮ በቀር ሁሉንም የአፍሪካ ሀገራት የሚያሳትፍ፣ የኦሊምፒክን ፅንሰ-ሀሳብ መሰረት አድርጎ በአፍሪካ ብሔራዊ የኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር አዘጋጅነት በዓለም-አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ይሁንታ የሚካሄድ ታላቅ አህጉራዊ ውድድር ነው፡፡ የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ልክ እንደ ታላቁ ኦሊምፒክ ሁሉ በአንዳንድ ውድድሮች (እንደ አትሌቲክስ ባሉ) ሚኒማ ማሟላት የሚችሉ ተወዳዳሪዎችን ያለማጣሪያ የሚያሳትፍ ሲሆን እንደ እግር ኳስ ባሉ ውድድሮች ግን ማጣሪያውን ማለፍ የሚችሉ ሀገራት ቡድኖችን ብቻ ያሳትፋል፡፡

በዚህ መሰረት ለዘንድሮው ውድድር ለማለፍ ካለፈው ውድድር አሸናፊዋ ጋና፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ካሜሩን እና ሴኔጋል በቀር አብዛኞቹ ሀገራት ሁለት፣ ሁለት የማጣሪያ ደርሶ መልስ ፍልሚያዎች ማድረግ ሲጠበቅባቸው ከላይ የተጠቀሱት አራቱ ሀገራት የመጀመሪያውን ዙር አልፈው የዚህን ዙር አሸናፊዎች እንዲጠብቁ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያም በታሪኳ በውድድሩ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ (በወንዶቹ ውድድር) ለመሳተፍ በምታደርገው ጥረት በማጣሪያ የደርሶ መልስ ፍልሚያ ከጎረቤት ሱዳን ጋር እንድትጫወት ተደልድላለች፡፡ ኢንተርናሽናል ጨዋታዎችን በማስተናገዱ ረገድ ለረጅም ግዜ አንድ ለእናቱ ሆኖ የቆየው የአዲስ አበባ ስታድየም ከአስር ቀን በኋላ ለሚጀመረውና ኢትዮጵያ ለምታስተናግደው 12ኛው የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በእድሳት ላይ የሚገኝ በመሆኑ ፌዴሬሽኑ አማራጭ ስታድየሞችን ማስመዘግብ ግድ ብሎታል፡፡ አጋጣሚውም ለባሕር ዳር እና ድሬዳዋ ስታድየሞች ኢንተርናሽናል ውድድሮችን  ለማስተናገድ የመመዝገብ ዕድልን የፈጠረ ሲሆን የድሬዳዋ ስታድየም ከ13 ዓመት በኋላ በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል የሚደረገውን ኢንተርናሽናል የማጣሪያ ጨዋታ ለማስተናገድ ዝግጁ ሆኖ እየተጠባበቀ ይገኛል፡፡
Sudan U23
በአሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ የሚመራው የኢትዮጵያ ቡድን ላለፉት ሶስት ሳምንታት ዝግጅቱን ሲያከናውን የቆየ ሲሆን አንድ የአቋም መለኪያ ጨዋታ ብቻ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውድድር አሸናፊው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር አድርጎ በራምኬል ሎክ፣ ዳዋ ሆጤሳ፣ ሄኖክ ፍሰሀ እና አማኑኤል መገርሳ ጎሎች 5ለ2 አሸንፏል፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በፊት አሰልጣኝ ባሬቶ 45 የሚደርሱ ተጨዋቾችን ወደ ቡድኑ ሲጠሩ አሰልጣኙ ለእረፍት ከሀገር ውጪ በመቆየታቸው፣ ከዚህ መነሻ የፕሪምየር ሊጉን ውድድሮች በበቂ ሁኔታ ካለመመልከታቸው እና የተወሰኑ ተጨዋቾችን የመረጡባቸውን የብሔራዊ ሊግ ክለቦች ጨዋታዎች ፈፅሞ ካለማየታቸው አንጻር ምርጫው ብዙ ክርክር አስነስቶ ነበር፡፡ ከምርጫው ጀርባ የክለብ አሰልጣኞች እና የስፖርት ጋዜጠኞች ሳይቀሩ በጥቆማ መሳተፋቸውም ሲወራ ሰንብቷል፡፡ ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ከተጨዋቾቹ በተጨማሪ የዋናውን ብሔራዊ ቡድን ምክትሎቻቸውን የቅዱስ ጊዮርጊሱን ፋሲል ተካልኝ እና የደደቢቱን ዳንኤል ፀሀዬንም አብረዋቸው እንዲሰሩ አድርገዋል፡፡ ከደደቢት የተመረጡትን ተጫዋቾች ከሲሸልስ መልስ በጉዞ መስተጓጎል ምክንያት ማግኘት ያልቻለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዓርብ ረፋድ ላይ የመጨረሻ ተመራጭ የሆኑትን 20 ተጫዋቾች ይዞ ወደ ድሬዳዋ አቅንቷል፡፡ ጨዋታውን የሚመሩት ኬኒያዊያን አርቢትሮች እና ጂቡቲያዊው የጨዋታ ኮሚሽነርም እንዲሁ ድሬዳዋ ገብተዋል፡፡

ለዚህ ጨዋታ ከፍ ያለ ትኩረት ሰጥቶ ላለፉት ሁለት ወራት በኳታር ዶሀ ዝግጅቱን ሲያደርግ የሰነበተው የተጋጣሚው የሱዳን ቡድን ከግብፅ ክለቦች ጋርም የአቋም መለኪያ ጨዋታዎችን ያደረገ ሲሆን ሐሙስ ዕለት አዲስ አበባ እንደገባ በቀጥታ ወደድሬዳዋ አምርቷል፡፡ አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ በከተማዋ ባለው ከፍተኛ ሞቃታማ የአየር ፀባይ ምክንያት እና ተመሳሳይ የአየር ፀባይ ካለበት ስፍራ ለሚመጣው ተጋጣሚያቸው ምቹ ከመሆኑ አንፃር ግጥሚያው በድሬዳዋ የመደረጉን ጉዳይ እንዳልወደዱት፤ የእሳቸው ፍላጎት ሳይጠየቅ እና ከግምት ሳይገባ ውሳኔው ተግባራዊ መደረጉም እንዳላስደሰታቸው ሳይገልፁ አላለፉም፡፡

18 ሺህ ተመልካች የማስተናገድ አቅም ያለው የድሬዳዋ ስታድየም በአሁኑ ሰዓት በአብዛኛው የእግር ኳስ ውድድሮችን እያስተናገደ የሚገኝ ሲሆን በ1976 ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ስታስተናግድ ስድስት ጨዋታዎች፣ የሴካፋ ውድድር እንዲሁም በ1994 የኢትዮጵያ ወጣት ብሔራዊ ቡድን ከዛምቢያ ጋር ያደረጉትን ጨዋታዎች በማስተናገዱ ይታወሳል፡፡ የዚህ ጨዋታ የመልስ ግጥሚያ ከየካቲት 28-30 ባሉት ቀናት በአንዱ ይደረጋል፡፡

በኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ውስጥ በኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ውስጥ ተካተው ወደድሬዳዋ ያቀኑ ው ወደድሬዳዋ ያቀኑ ው ወደድሬዳዋ ያቀኑት 20 ተጫዋቾች፡-

ግብ ጠባቂዎች፡ ግብ ጠባቂዎች፡-
አሰግድ አክሊሉ (መብራት ኃይል)፣ ክብረአብ ዳዊት (ሐዋሳ ከነማ)

ተከላካዮች፡-
ሳላዲን ባርጌቾ (ቅ. ጊዮርጊስ)፣ አወት ገ/ሚካኤል (መብራት ኃይል)፣ ዘጋሪያስ ቱጂ (ቅ. ጊዮርጊስ)፣ አህመዲን ረሺድ (ኢትዮ. ቡና)፣ ቴዎድሮስ በቀለ (መከላከያ)

አማካዮች፡-
ምንተስኖት አዳነ (ቅ. ጊዮርጊስ)፣ አንዳርጋቸው ይላቅ (ቅ. ጊዮርጊስ)፣ ናትናኤል ዘለቀ (ቅ. ጊዮርጊስ)፣ ጋቶች ፓኖም (ኢትዮ. ቡና)፣ ሚካኤል በየነ (ኢትዮ. ቡና)፣ ሀይደር ሸረፋ (ደደቢት)፣ ሱራፌል ጌታቸው (ሙገር ሲሚንቶ)፣ እንዳለ ከበደ (ሲዳማ ቡና)

አጥቂዎች፡-
ዳዋ ሆቴሳ (ቅ. ጊዮርጊስ)፣ ኤፍሬም ቀሬ (ሙገር ሲሚንቶ)፣ ራምኬል ሎክ (መብራት ኃይል)፣ ምንይሉ ወንድሙ (መከላካያ)፣ አብዱራህማን ሙባረክ (አዲስ አበባ ከተማ)

1 thought on “የኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ቡድን ድሬደዋ ላይ የሱዳን አቻውን ያስተናግዳል

Leave a Reply

Your email address will not be published.