የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በአውሮፕላን ማጣት ምክንያት ብዙ ሰዓታትን በያውንዴ የአውሮፕላን ማረፊያ ለመቀመጥ ተገዷል

Team Ethiopia - Youth Women

ባለፈው እሁድ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ያውንዴ ላይ ከካሜሮን አቻው ጋር 0 ለ 0 የተለያየው የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በአውሮፕላን ማጣት ምክንያት ብዙ ሰዓታትን በያውንዴ የአውሮፕላን ማረፊያ ለመቀመጥ ተገዷል፡፡

ዛሬ ማምሻውን ከያውንዴ – ዱዋላ በረራ የሚያገኝ ከሆነ ቡድኑ ነገ አዲስ አበባ የሚገባ ይሆናል፡፡

ቡድኑ ለዚህ ችግር የተጋለጠው ከካሜሮን ያውንዴ – ዱዋላ የሚደረገው በረራ በመሰረዙ ነው፡፡

በዚህ ምክንያትም ቡድኑ ያለምንም ምግብ እና መጠጥ ለ9 ሰዓታት በአውሮፕላን ማረፊያው ለመቀመጥ ተገዷል፡፡ በአጠቃላይ ደግሞ ከአንድ ቀን በላይ በአስቸጋሪ ሁኔታ በካሜሮን ቆይቷል፡፡

የበረራው መሰረዝ ከታወቀ በኋላ ቡድኑ ወደ ሆቴል ተመልሶ ዕረፍት ማድረጉ ተገልጿል፡፡

ቡድኑ በአየር ማረፊያ ለማደር ሲገደድ የካሜሮን እግር ኳስ ፌደሬሽን ምንም ድጋፍ አለማድረጉ ተጠቁሟል፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ እስካሁኑ ሰዓት ድረስ በያውንዴ አውሮፕላን ማረፊያ በረራ እየተጠባበቀ ይገኛል፡፡

ምንጭ፡- የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን

Leave a Reply

Your email address will not be published.