የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ5ኛውን ሀገር አቀፍ አጠቃላይ ምርጫ ጊዜያዊ ውጤት ይፋ አደረገ።

Election Board Announces Prelimnary Results

Election Board Announces Prelimnary Results

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ5ኛውን ሀገር አቀፍ አጠቃላይ ምርጫ ጊዜያዊ ውጤት ይፋ አደረገ። በዚህም መሰረት አዲስ አበባ ላይ ከ23 መቀመጫዎች ኢህአዴግ 23ቱንም መቀመጫዎች አግኝቷል።

ከትግራይ ክልል ቦርዱ ከደረሱት የ31 መቀመጫዎች ውጤት ህውሃት/ኢህአዴግ 31 መቀመጫዎችን፣ ከአማራ ክልል ከደረሱት የ107 መቀመጫዎች ውጤት ብአዴን/ኢህአዴግ 107 መቀመጫዎች፣ ከኦሮሚያ ክልል ቦርዱ ከደረሱት የ150 መቀመጫዎች ውጤት ኦህዴድ/ኢህአዴግ 150 መቀመጫዎችን፣ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ቦርዱ ከደረሱት የ16 መቀመጫዎች ውጤት ኢሶዴፓ 16 መቀመጫዎችን፣ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከደረሱት የሰባት መቀመጫዎች ውጤት ሰባቱንም ቤጉዴፓ አግኝተዋል።

ከደቡብ ክልል ከደረሱት የ95 መቀመጫዎች ውጤት ዴኢህዴን/ኢህአዴግ 95 መቀመጫዎች፣  በጋምቤላ ክልል ጋህዴፓ ከሶስት መቀመጫዎች ሶስቱንም፣ በሀረሪ ክልል ሀብሊ ከ2 መቀመጫዎች አንዱን ሲያገኝ አንዱን ኦህዴድ/ኢህአዴግ፣ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከሁለቱ መቀመጫዎች አንዱን ኦህዴድ/ኢህአዴግ ቀሪውን ሶህዴፓ አግኝተዋል።

ከአፋር ክልል ከደረሰው የስድስት መቀመጫዎች ውጤት አብዴፓ ስድስቱንም መቀመጫ አግኝቷል።

በኢትዮጵያ ህገ መንግስት መሰረት መንግስት ለመመስረት አንድ ፓርቲ 274 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎችን ማግኘት የሚገባው ሲሆን፥ ቦርዱ  ዛሬ ባወጣው ጊዜያዊ ውጤት መሰረት ኢህአዴግ 408 መቀመጫዎችን አግኝቷል።

Election_2007_Result_1

Election_2007_Result_2

Source: FBC

4 thoughts on “የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ5ኛውን ሀገር አቀፍ አጠቃላይ ምርጫ ጊዜያዊ ውጤት ይፋ አደረገ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.