የኢትዮጵያና ሳዑዲ ዓረቢያ የሠራተኞች ቅጥር ስምምነት ሊፈራረሙ ነው

ነሐሴ 21፣ 2007
ኢትዮጵያና ሳዑዲ ዓረቢያ የኢትዮጵያውያን ሠራተኞችን መብት የሚያስጠብቀውን የሰራተኞች ቅጥር ስምምንት በመጪው መስከረም ሊፈርሙ ነው።
ስምምነቱ ሠራተኞች ክፍያቸውን በወቅቱ እንዲያገኙ፣ከማንኛውም ጥቃት እንዲጠበቁና በችግር ጊዜ ወደ አገራቸው የመመለስ ኃላፊነትን ያስቀምጣል።
በሳዑዲ ዓረቢያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጉዳይ አስፈፃሚ አቶ ተመስገን ዑመር ለኢዜአ እንዳሉት ስምምነቱ በሳዑዲ ዓረቢያ ተቀጥረው የሚሰሩ ኢትዮጵያውያንን የክፍያና የሥራ ሁኔታን የሚቀይር ነው።
የኢትዮጵያ መንግሥት ችግሩ እልባት እስኪያገኝ ድረስ ዜጎቹ ሥራ ፍለጋ ወደ ዓረብ አገራት የሚያደርጉትን ጉዞ ከጥቅምት 2006 ዓ.ም ጀምሮ አግዷል።
ምንጭ፦ ኢብኮ