የአስም በሽታ

Asthma

(በዳንኤል አማረ ©ኢትዮጤና)

አስም የአየር ቧንቧዎች በሽታ ሲሆን የአተነፋፈስ ስርዓትን በማዛባት ለመተንፈስ አዳጋች ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ የአየር መተላለፊያ ቧንቧዎችን እንዲቆጡ በማድረግ ወደ ሳንባ ኦክስጂን የሚወስዱ ቧንቧዎችን እንዲጠቡ ያደርጋል፡፡ ይህም እንደ ሳል፣ ሲተነፍሱ ድምጽ ማዉጣት፣ የትንፋሽ ማጠር፣ የደረት መወጠር እና የመሳሰሉት የአስም በሽታ ምልክቶች ያስከትላል፡፡ ከባድ የአስም በሽታ ለመንቀሳቀስ እና ለማውራት እስከመቸገር ያደርሳል፡፡ የአስም በሽታ ጥሩ የሚባል ህክምና ቢኖሩትም አደገኛና ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው በሽታ መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ ነገር ግን በትክክል ህክምናውን በመከታተል ጤናማ ሆኖ መኖር ይቻላል፡፡

የአስም በሽታ የተለያዩ 3 ገጽታዎች አሉት እነሱም፦
1. የአየር ቧንቧ መዝጋት በጤናማ የአተነፋፈስ ስርዓት የአየር ቧንቧዎችን የከበቡት ጡንቻዎች ዘና ይላሉ ይህም የአየር ቧንቧ ያለምንም መጨናነቅ እንዲንቀሳቀስ ያደርገዋል፡፡ ነገር ግን የአስም በሽታ ያለባቸው ሰዎች አለርጂ፣ ጉንፋንና የአካባቢያችን ሁኔታዎች የአየር ቧንቧዎችን የከበቡትን ጡንቻዎች እንዲጠብቁ ያደርጋቸዋል ከዚያም አየር በትክክል እንዳይተላለፍ ያደርገዋል፡፡ ወደ ውስጥ የሚገባውን አየር ሲያንስ ሰውየው የትንፋሽ እጥረት ያጋጥመዋል በጣም በጠበቡት የአየር ቧንቧዎች የሚወጣው አየር ትንፋሻችን ድምጽ እንዲኖረው ያደርገዋል፡፡
2. የቧንቧዎች መቆጣት አስም ያለባቸው ሰዎች የመተንፈሻ ቧንቧዎቻቸው ያብጡና ቀይ ይሆናሉ፡፡ ይህ የቧንቧዎች መቆጣት ከብዙ ጊዜ ቆይታዎች በኃላ በአስም ምክንያት ለሳንባ መጎዳት ከፍተኛ አስተዋጽዎ ያደርጋል፡፡ ይህን የቧንቧዎች መቆጣትን ማከም የአስም በሽታን ለመቆጣጠር ከፍተኛ አስተዋጽዎ ያደርጋል፡፡
3. የአየር ቧንቧዎች ማሳከክ/መቆጣት በአስም በሽታ የተያዙ ሰዎች የአየር ቧንቧ ከመጠን በላይ ቁጡና ቶሎ ምላሽ የሚሰጡ ናቸው፡፡ እነዚህ የአየር ቧንቧዎች በጣም በትንሽ ሽታ ለምሳሌ የአበባ ዱቄት፣ የእንሰሳት ሽታ አቧራና የመሳሰሉት በቀላሉ እንዲቆጡና እንዲጠቡ ያደርጋቸዋል፡፡

አስም በአዋቂ ሰዎች ላይ
የአስም በሽታ በማንኛውም የእድሜ ክልል ላይ ሊከሰት ይችላል፡፡ እድሜያቸው ከ40 ዓመት በታች የሆኑ ሰዎች ላይ የተለመደ ነው፡፡ በአስም የተያዘ የቤተሰብ አባል ያለው ሰው በአስም የመያዝ እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ አለርጂክ እና አስም አብረው የመከሰት እድል አላቸው፡፡ አስም ማንኛውንም ሰው በማንኛውም ጊዜ ሊይዝ ይችላል ስለዚህ የአስም ምልክቶች ከታዩ በአፋጣኝ የህክምና እርዳታ ያግኙ፡፡

አሰም በህፃናት ላይ
አስም ህፃናትን በብዛት ይይዛል በአሜሪካ ከሚገኙ 10 ህፃናት አንዱ በአሰም በሽታ ይያዛሉ፡፡ የአሰም ምልክቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ በአንድ ህፃን ላይ ሊለያይ ይችላል፡፡ ልናስተውላቸው የሚገቡ የአስም ምልክቶች እነሆ፦
° በተደጋጋሚ መሳል፦ በሚጫወቱበት፣ በሚስቁበትና ማታ ላይ ያስላቸዋል፡፡ በአስም በሽታ ጊዜ ሳል ብቸኛ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡
° በጨዋታ ጊዜ የአቅም ማነስ ወይም በጨዋታ ጊዜ ትንፋሽ ለመሰብሰብ መቆም
° ቶሎ ቶሎ መተንፈስ
° የደረት መታፈን
° አየር ሲያስወጡ እና ሲያስገቡ ለየት ያለ ድምጽ መኖር
° የትንፋሽ መጨመርና መቀነስ ወይም የተዘበራረቀ አተነፋፈስ
° የትንፋሽ ማጠር
° የአንገትና ደረት ጡንቻዎች መጠንከር
° የድካም ስሜት

የአስም በሽታ መነሻና የሚያባብሱት ነገሮች
የአስም በሽተኞች የአየር ቧንቧ በአካባቢያችን ለሚገኙ ብዙ ነገሮች በቶሎ መሰማት እና ቁጡ እንዲሆን ያደርጉታል፡፡ ከነዚህ ነገሮች ጋር ንክኪ ሲኖረን የአስም በሽታ ምልክቶች እንዲጀምሩ ወይም እንዲባባስ ያደርጋቸዋል፡፡ የሚከተሉት የአስም በሽታ መነሻ ናቸው የሳይነስ፣ ጉንፋንና ፍሉ ኢንፌክሽኖች የአበባ ዱቄት(ፖለን)፣ ሻጋታ፣ የቤት እንሰሳት ሽታና አቧራ ነገሮች ጠንካራ ሽታ ያላቸው ሽቶዎች፣ የማጽጃ ፈሳሾች ሽታና የተበከለ አየር የሲጋራ ጭስ/ሲጋራ ማጨስ አንዳንድ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች የአየር ሁኔታ፦ የሚቀት ሁኔታ መቀያየር፣ እርጥበታማ አየር፣ ቀዝቃዛ አየር ጭንቀት፣ ሳቅ ወይም ለቅሶ፣ ዉጥረት የተለያዩ መድሃኒቶች(አስፕሪን)

የአስም በሽታ መከላከያዎች
° የኢንፉሌንዛ እና ኒሞኒያ ክትባት መዉሰድ ክትባቶች በጊዜ መውሰድ ለአስም በሽታ መነሻ ሊሆኑ የሚችሉትን ኢንፉሌንዛ እና ኒሞኒያ መከላከል ይችላል
° ለአስም በሽታ የሚያጋልጡ ነገሮችን ለይቶ ማወቅና ማስወገድ ከቤት ውጪ የሚገኙ እንደ አበባ ድቄት ፣ ቀዝቃዛ አየርና የአየር ብክለት የመሳሰሉት የአስም በሽታ ሊያስለሱ ስለሚችል ከነዚህ ነገሮች መራቅ ተገቢ ነው፡፡
° የአተነፋፈስ ሁኔታን መከታተል የአስም በሽታ ምልክቶች የሆኑትን ሳል፣ የትንፋሽ እጥረትና የመሳሰሉት ማስተዋልና ህክምና ማድረግ ተገቢ ነው፡፡
° ቶሎ(በጊዜ) መታከም በቶሎ እርምጃ የምንወስድ ከሆነ በሽታን ስር ሳይሰድ መቆጣጠር እንችላለን፡፡
° መድሃኒቶችን በታዘዙልን መሰረት መዉሰድ/መጠቀም

የአስም ህክምና
የአስም በሽታን መከላከያ መንገዶችን መጠቀምና ለረጂም ጊዜ መቆጣጠር በአስም በሽታ እንዳንጠቃ ቁልፍ ነገሮች ናቸው፡፡ የአስም በሽታ ህክምና እና የመነሻ ምክንያቶችን ማወቅ እነዚህ መነሻዎችን ለማቆም እርምጃ መውሰድ እና በየቀኑ የምንወስዳቸው የአስም መድሃኒቶች ውጤታማ ለመሆናቸው ትንፋሻችንን መከታተልን ያጠቃልላል፡፡ ትክክለኛውን የአስም መድሃኒት ለመጀመር የሚከተሉትን ነገሮች ማጤን ተገቢ ነው፡፡ እነሱም፦
° የበሽተኛው እድሜ
° የበሽታው መነሻ ምክንያቶች
° በሽተኛው ላይ የሚታዩበት ምልክቶች የአስም በሽታን በቀላሉ ለመቆጣጠር ወሳኝ ድርሻ አላቸው፡፡

መልካም ጤንነት!!! ለበለጠ የጤና መረጃ ይህን ገጽ ላይክ ያድርጉትwww.facebook.com/EthioTena – See more at: http://www.ethiotena.net/wordpress/?p=61#sthash.VCZkzMU5.dpuf

– See more at: http://www.ethiotena.net/wordpress/#sthash.8TraPzim.dpuf

3 thoughts on “የአስም በሽታ

  1. It’s a great awarness ….tnx….but i wish to know the difference b/n ‘Asim’ n ‘Saynes’….

Leave a Reply

Your email address will not be published.