የትግራይ ክልል ምክር ቤት አቶ አባይ ወልዱን በድጋሚ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ መረጠ

59a67c2de9545ea538b72805374aff96_XL

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የትግራይ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው አምስተኛ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር እና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር መረጠ።

በዚህም መሰረት አቶ አባይ ወልዱን ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ በድጋሚ ሲመርጥ፥ አምባሳደር ዶክተር አዲስዓለም ባሌማ ደግሞ በምክትል ርዕሰ መስተዳድርነት ተመርጠዋል ።

በተጨማሪም የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባኤ በመሆን ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ በድጋሚ የተመረጡ ሲሆን፥ ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ ሩፋኤል ሺፋረ ተመርጠዋል።

ምክር ቤቱ በጉባኤው የዞን መስተዳድሮች፣ የፈጻሚ አካላት፣ የምክር ቤቱ የቋሚ ኮሚቴዎች ሰብሳቢዎችና ምክትል ሰብሳቢዎች ሹመትንም አፅድቋል።

አቶ አባይ ወልዱ ቃለ መሃላ ከፈፀሙ በኋላ ባሰሙት ንግግር ህዝቡ የሰጣቸውን አደራ ለመወጣት እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።

በሚቀጥሉት አምስት አምታትም በህብረተስቡ ይነሱ የነበሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ጥረት እንደሚደረግም ነው ያመለከቱት።

በከተሞች የሚስተዋለው የኪራይ ስብሳቢነት የልማት ፀር በመሆኑ ልንታገለው ይገባል ያሉት አቶ አባይ፥ ህብረተስቡም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

በከተሞች ያለውን የቤት ችግር ለመቅረፍም ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ያማከለ የቤቶች ግንባታ እንደሚካሄድ ገልፀዋል።

በገጠርም የተለያዩ የልማት ስራዎችን በማከናወን የእርሻ ትራንስፎርሜሽን ይተገበራል ሲሉም ተናግረዋል።

በተጨማሪም ርዕሰ መስተዳደሩ ያቀረቡትን የክልሉን ካቢኒ አባላት ሹመትን ምክር ቤቱ አፅድቋል።

በዚህም መሰረት፦

1. ምክትል ርእሰ መስተዳድር እና የከተማ ልማት፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሀላፊ – አምባሳደር ዶክተር አዲስዓለም ባሌማ
2. የግብርና ቢሮ – ሃላፊ አቶ ኪሮስ ቢተው እና አቶ ሀይሌ አስፈሃ፣
3. የትምህርት ቢሮ ሃላፊ – አቶ ጎበዛይ ወልደአረጋይ፣
4. የጤና ቢሮ ሃላፊ – አቶ ሀጎስ ጎደፋይ፣
5. የፍትህ ቢሮ ሀላፊ – አቶ ልዑል ካህሳይ፣
6. የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ሃላፊ – ወይዘሮ አረጋሽ በየነ፣
7. የሴቶች ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ – ወይዘሮ ሙሉ ካህሳይ፣
8. የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቢሮ ሃላፊ – አቶ ጎይቶም ይብራህ፣
9. የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ – ዶክተር ገብረህይወት ገ/እግዚአብሄር፣
10. የፋይናንስ እና እቅድ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ – አቶ ብርሃነ ፅጋብ፣
11. የውሃ ሀብት ቢሮ ሃላፊ – አቶ ገብረመስቀል ታረቀ፣
12. የኮንስትራክሽን እና ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ – አቶ ተስፋዬ ገብረኪሮስ፣
13. የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ – አቶ ዳዊት ሃይለ፣
14. የገቢዎች ልማት ባለስልጣን ሀላፊ – ወይዘሮ ምህረት በየነ፣
15. የጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ተቋማት ቢሮ ሀላፊ – አቶ ጥላሁን ታረቀ፣
16. የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ – ወይዘሮ ኪሮስ ሀጎስ፣
17. የፀጥታ እና አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ – አቶ ሀዱሽ ዘነበ እና
18. የመንግስትና የህዝብ ግኑኝነት ቢሮ ሀላፊ – አቶ ገብረሚካኤል መለስ ሆነው ተሹመዋል።

እንዲሁም የምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ወይዘሮ ያላም ፀጋይ፣ የደቡብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተወልደብርሃን ተስፋዓለም፣ የሰሜናዊ ምእራብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማሙ ገብረእግዚአብሄር፣ የደቡባዊ ምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም እና የምዕራብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኢሳያስ ታደሰ ሆነው ተሰይመዋል።

የክልሉ ምክር ቤት ከዚህ በተጨማሪ በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ላይም ጥልቅ ውይይት ያደርጋል።

በመቐለ እየተካሄደ ያለው የምክር ቤቱ ጉባኤ ለቀጣይ ሶስት ቀናት ይቆያል።

በሙሉጌታ አፅበሃ

ምንጭ፦ ፋና

Leave a Reply

Your email address will not be published.