የሚያሳፍር ይዘዝብህ!!

dsc_2604

 

መስከረም 12፣ 2007 | በደመቀ ከበደ

አስቸኳይ ፕሮጀክት ለማስረከብ ዛሬ ቀጠሮ አለብኝና በጠዋት ነው የተነሳሁት፡፡ ከሲኤምሲ መገናኛ እና ከመገናኛ – ብሔራዊ – ሜክሲኮ በሚጭኑ ሁለት ታክሲዎች ነው ቢሮዬ የምደርሰው፡፡

ከሲኤምሲ መገናኛ ባለው ጉዞዬ አንድ ወዳጅ ታክሲ ውስጥ አጋጠመኝና የወዳጅነቴን ከፈልኩ፡፡ ደረስን አመስግኖኝ ወረደ – ወረድኩ፡፡

ሁለተኛውን ታክሲ ያዝኩ – ከመገናኛ ብሔራዊ ሜክሲኮ የሚያደርሰኝን፡፡
ሰው በጠዋቱ ነቅሶ ወጥቷልና እስከ አፍ ጢሟ ጫነን፡፡
ከጥቂት ጉዞ በኋላ ረዳቱ ሂሳብ መቀበል ጀመረ፡፡
ሁሉም እያወጣ ከፈለ፡፡

አገር ሰላም ብዬ እጄን ወደ ኪሴ ሰሰድኩ፡፡
ጠላታችሁ ክው ይበልና እንደ ግንቦት ዋልካ መሬት ሰውነቴ ከላይ እስከታች ተሰነጣጠቀ፡፡
ቀኝ ኪሴን ፈተሸኩ – ብሮቼ የሉም፡፡
ግራውንም አየሁት – የሉም፡፡
የጃኬቴንም በረበርኩ – ፈፅሞ!

እንደዚህ ዓይነት ‹‹ቅሌት ወይ ውርደት ይሉት ነገር›› ሲያጋጥመኝ የመጀመሪያ ነውና ደንግጫለሁ፡፡

በግንባሬ የተንቸፈቸፈውን ላቤን በግራ እጄ እያባበስኩ ረዳቱን ‹‹ስንደርስ ልክፈል…›› አልኩት፡፡
‹‹ከኪሱ አውጥቶ ለመክፈል ባይመቸው ነው ›› በሚል ይመስላል ሌሎቹን ወደማስከፈከሉ ሄደ፡፡

ስልኬስ??
ቀኝ ኪሴ ገባሁ – እሱም የለም፡፡ አመዴ ቡን አለ፡፡

ዋሌቴስ ??
ወደ ኋላ ኪሴ ገባሁ – አለ፡፡

አፍታ ቆይቼ በተረጋጋ መንፈስ ሳስተውል ግራ እጄ ላይ አለ – ስልኬ፡፡ እፎይ አልኩ፡፡
ግን ብሮቼስ!
ጥሎብኝ ብዙ ብርም ቢሆን በዋሌት መያዝ አልወድም – በቃ ያለኝን ሁሉ በቀኝ ኪሴ ነው የምይዘው፡፡

ካሳንቺስ ስንደርስ ‹‹ወራጆች ወረዱ››፡፡
ለሶስት ተቀምጠንበት ከነበረው ወንበር አንድ ሰው ተቀነሰ፡፡
‹‹አሁን ለማውጣት ይመችሃል ክፈል›› አለኝ – ረዳቱ፡፡

አፌ ተያያዘ፡፡
‹‹እ… እ›› እያልኩ እንደገና ወደኪሴ ገባሁ፡፡
አፍጥጦ ያየኛል፡፡
‹‹በቃ ስንደርስ ኤ ቲ ኤም ሸበሌ ሆቴል ጋር አውጥቼ እሰጥሃለሁ፡፡ ብሮቼ ወይ ከኪሴ ስልኬን ሳወጣ ወድቀዋል ወይ ሌባ ሰርቆኛል፡፡›› አልኩት፡፡
‹‹ባክህ ክፈል – ይሄ የተበላበት ስልት ነው…›› አለኝ በማጓጠጥ፡፡
‹‹ፕሊስ ተረዳኝ – የምሬን ነው፡፡›› መለማመጥን የመሰለ አስጠሊታ ነገር በምድር የለም፡፡
‹‹ሰውዬ ትከፍል እንደሁ ክፈል – ታዲያ ገንዘብ ሳጥይዝ ዘው ብለህ ለምን ገባህ..›› ጮኸ፡፡

የተሳፋሪው ሁሉ ዓይን እኔ ላይ አፈጠጠ፡፡
ይሄኔ ‹‹አንዴ በቦክስ በለው.. ሌባ!!›› የሚሉት መሰለኝ – በሆዳቸው፡፡
እኔ ደግሞ ያኔ በደህናው ቀን ‹‹መልስ የለኝም፤ ዝርዝር የለኝም እያሉ ረዳቶች ሁሉ ሳይመልሱ የተውኩሏቸውን በተለያዬ ቀን የከፈልኳቸውን ብሮች እያሰብኩ ‹‹እርም ቁራጭ ሳንቲም ብተውላችሁ›› እያልኩ ነበር፡፡
‹‹ሰውዬ….!!›› አለ – የታክሲዋ ሁለመና በሚበታትን ድምፅ፡፡

ልሳን አጣሁ – ሽምቅቅ አልኩ፡፡
‹‹አቦ ተወኛ ወጣት አይደለህ – ወይ እመነኝ ወይ ተወኝ!!›› አልኩት፡፡
ተሳፋሪው ሁሉ አፍጥጦ ከማየት በቀር የተነፈሰ አለመኖሩ አበገነኝ፡፡ ሾፌሩም አንዳች ቃል አልወጣውም፡፡

አንዲት ወጣት ሴት ..
‹‹አንተ ምን ሆነሃል – አምስት ብር ከኪስህ ወድቆ አያውቅም እንዴ በፈጣሪ – እየነገረህ አይደል ያጋጠመውን – ይሄው እኔ እከፍልለታለሁ፡፡›› አለችና ወረወረችለት፡፡
ለቀም አድርጎ አጉተመተመና ዝም አለ፡፡

መናገሪያየን ሁሉ ነው የቆለፈብኝ – የከፈለችልኝን ልጅ እንኳን የማመስገን ድፍረት አጣሁ፡፡

አይደረስ የለም ደረስን – ለወትሮው ብሄራዊ አካባቢ ነበር የምወርደው – ታክሲ መጨረሻው ድረስ ‹‹ሽምቅቅ ብዬ›› ሄድኩ፡፡ ወረድን፡፡
ስወርድ…
ሾፌሩ ብር አወጣና ‹‹ሶሪ እንዲህ ያጋጥማል – ቀጣይ ታክሲ መሳፈሪያ ስለማይኖርህ እንካ ›› ብሎ ዘረጋልኝ፡፡
አሁንማ ሸበሌ አወጣለሁ – ግን አመሰግናለሁ፡፡

እንደወረድን የከፈለችልኝን ልጅ ፈለኳት – የለችም ሄዳለች፡፡
ብሮዬ እንደገባሁ ይሄን ፃፍኩ፡፡
አንቺ የማላውቅሽ የማታውቂኝ ወጣት ‹‹አመሰግንሻለሁ!!››

 

17 thoughts on “የሚያሳፍር ይዘዝብህ!!

  1. Betam yemeyasdeset derset yemsmesel nger new nger gen yahya nger yeewnet yemhone new ena sewoch banchkakein teru new ena antein gen kahuin ahuin metawe beya segahu eko anteletolo mfethewen wedehuwala akoyeto yemtsffe ewketo alehena berretan endzhe kewenett gar yalu Derammawochin metsafe Albhe beyaa emakerhulhu. Lejetowanem teberkey elalehu leweyalawem andandya entezazen enjie malet deferet ayedelemena hulum sew leba ayedlemna merarat albhe elalhu.bye

  2. Enen betam yegeremegn Ye leju Tsihuf chilota ye ewunet betam des yilal . Keziya beterefe , Tininish santimochen iyelekakemu yemiyaskerut ye taksi redatochachenen tazebkuachew

  3. በጣም የሚገርም አጋጣሚ ነው ለማንኛውም ብሮችህን ስታስቀምጥ ለወደፍቱ ባሉህ ኪሶች ከፋፍለህ የማስቀመጥ ልምድ ይኑርህ.

  4. በጣም ይገርማል ልጅቷ እግዛብሄር ይባርካት ሌሎችም የተቸገረን መርዳት በእግዛብሄር ዘንድ ዋጋ አለውና ቸል አትበሉ

  5. DEAR READERS,WHOEVER CAN HELP ME TO GET BACK TO MY OWN CITY IN FRANCE, i’LL BE GREATFUL,AND BLESS YOU ALL.BECAUSE ANYPERSON CONTACT ME WITH AWRONG REASON i ALREADY GAVE MY FULL DOCMENT TO THE gOVERMENATALLY LAW MAKERS WHICH BY THE WAY LATE ME TO STAY FOR AT LEAST 3YEARS THAT i GOT THIS MESSAGE FROM WESTSIDE OF eTHIOPIA,WHEN i VISIT MY GREATGRANNIES LAND wELEGA aRJO pROVIDENCE SO,i TRIED TO COMMUNICATE WHY i SHOULD STAY LIFE CAN’T BE REPEATED BAD MEMORY TO ME AND OTHERS WHO REALLY WANTS TO CHANGE IN THE NAME OF gOD aLMIGHTY PAS,RELIGIOUS WAR ONLY i NEED TO FREE LIKE HE FREES ME,THERE,BUT REMEMBER BOYS CAN NOT UNDERSTAND GIRLS PERSONALL PROBLEM.

  6. Sewoche ebakachu andu wendmachu endi sisakeke zeme belachu mayetu agebabe ayedelem pls Ethiopianweyane enredada agatamiwe Hulachenenem bezure selemidersen. (betame azgnalew) teru temrete newe

  7. በጣም የሚያሳዝነኝ ነገር ቢኖር እነዚ የሰዉ ንብረት የሚዘርፉ ሌቦች ጉዳይ ነዉ የሚገርመዉ ነገር ደግሞ ማንም ይሄን ጉዳይ አይቶ እዳላየ የማለፉ ነገር አንዳንዴ ሰዉ በሀገሩ እንደ ልቡ መሆን የማይችልበት ስልክ አዉጥተን እንኳን ማናገር የማይቻልበት ሀገር ታክሲ ተራወች በተለይ ሰወች በብዛት የሚገበያዩበት ቦታዎች ችግሩ የከፋ ነዉ ሁሉም የየበኩሉን ካልተወጣ ይሄ ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ የማይቀር ነዉ

  8. for next time ask your neighbor before you argue with this rude co-drivers, i paid many times for such incidents even though i never faced such case, most of the “weyalas” are very fast to start a fight, i dont know what is wrong with them

Leave a Reply

Your email address will not be published.