“የሀይል ጨዋታ ቀንሱ“ ካሉሻ ቡዋልያ—የ5ት ሀገር ዳኞች የኮንጎና ዋልያን ጨዋታ ይመራሉ!!ተስፋዬ ገብረየሱስ ተመልሰዋል!!!ዋልያ አረንጓዴ ይለብሳል!!

IMG_0740[1]

የቻን ፕሪማች አሁንም ያለ ዳኞች ተካሂድዋል፡፡ዛሬ ቀትር ላይ በተደረገዉ የቅድመ-ጨዋታ ስብሰባ ኮሚሽነሩ እና የዳኞች ተቆጣጣሪዉ ብቻ ነበር የተገኙት–ዋናዎቹ ዳኞች አሁንም ኬፕታዉን ነዉ ያሉት ገና አልመጡም፡፡ዋና ዳኛ ከቡርኪና ፋሶ..ረዳቶች ኡጋንዳ ና ግብጽ ናቸዉ፡፡ኮሚሽነሩ ጋናዊ ነዉ፡፡

የዋልያ ደጋፊዎች ጉዳይ ከመነጋገሪያ ነጥቦች አንዱ ነበር፤እኛ የዉድድሩ አዘጋጅ አደለንም፡ደጋፊዎች በሰሩት ነገር መጠየቅ የለብንም በሚል ይግዛዉ ብዙአየሁ የፌዴሬሽኑ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ተከራክረዋል፡፡የምድብ 3ት ዉድድር አስተባባሪ ኬኒያዊዉ ሙሶንዮ ነዉ፡፡ዋናዉ ሀላፊ ደግሞ ካሉሻ ቡዋሊያ ነዉ፡፡እናም በነገሩ ላይ አበክረዉ ከተነጋገሩ በኋላ ፖሊስ በሚበጠብጡ ደጋፊዎች ላይ እርምጃ ስለሚወስድ እናዳትደናገጡ ብለዋል፡፡ደጋፊዎቻችን ከሩቅ ቦታ ነዉ የሚመጡት እናም በትእግስት ጨዋታዉን ያያሉ ስለዚህ የፀጥታ ሰዎች ትእግስት እንዲያደርጉ እንመክራለን ብለዋል ይግዛዉ!!

የሀይል አጨዋወት ቀንሱ በሚል ካሉሻ ተናግርዋል፡፡በመጀመሪያ ጨዋታ ላይ አንድ ቢጫ ተጫዋቻችሁ አይትዋል(አስራትን ነዉ) እናም በነገዉ ጨዋታ 2ተኛ ከደገመ የጋና ጨዋታ እንዳያመልጠዉ ይጠንቀቅ በሚል ካሉሻ ምክሩን ለግስዋል፡፡ይግዛዉ ብዙአየሁ እኔ በጉብዝናዬ ጊዜያት አንተን አጫዉቼህ ነበር ብለዉ ጨዋታዉን እና ቀኑን ሲጠቅሱ ተሰብሳቢዉ የግርምት ፈገግታዉን ለግስዋቸዋል፡፡

እናም ህጉን እናቃለን እንጠነቀቃለን ነዉ ነገርየዉ፡-በነገራችን ላይ ሰዉየዉ ከ1976 እስከ 1991 ድረስ ዳኛ ነበሩ፡፡የመጨረሻዉን 10 አመት በኢንተርናሽናልነት አሳልፈዋል፡፡አሁን በ2ት ቢጫ ምክንያት ስራቸዉን በለቀቁት አሸናፊ እጅጉ ቦታ የፌዴሬኑ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ሁነዋል፡፡

በእድሜ ምድባቸዉ የሚገኙት ተስፋዬ ገብረየሱስ የነገዉ ጨዋታ የዳኞች ተቆጣጣሪ ናቸዉ፡፡ሰዉየዉ አሁን የኤርትራን እግር ኳስ ይመራሉ፡፡ያኔ ያኔ ግን አዲስ አበባ ስታድየም የሚገኘዉን ፌዴሬሽን በፕሬዝዳንትነት መርተዋል፡፡ኢትዮጵያን ወክለዉ በአለም ዋንጫም አጫዉተዋል፡፡ያኔ ለይግዛዉ አለቃቸዉ ነበሩ፡፡አሁን ደግሞ በተለያዩ ሀገራት ተወካይነት ተገናኝተዋል፡፡ግን መከባበሩ እና ናፍቆቱ እንዳለ ነዉ፡፡ኤርትራን እንደገና ለማየት የሚጓጓ እና የወጣትነት እና ጎልማሳነት ከተማዉን ለመጎብኘት የሚሹ መንፈሶች ናቸዉ የተገናኙት…ለማንኛዉም ኮንጎ እና ዋልያ ሲጫወቱ ዋልያዉ የበቀደሙን አረንጓዴ መለያ ይለብሳል፡፡የካፍ አርማ ያለበት ቦታ በስተግራ መሆኑ ተገቢ እንዳልሆነ ተነግግሮዋቸዉ የካፍ አርማዉ ወደ ግራ እጅ ተቀይርዋል፡፡

1 thought on ““የሀይል ጨዋታ ቀንሱ“ ካሉሻ ቡዋልያ—የ5ት ሀገር ዳኞች የኮንጎና ዋልያን ጨዋታ ይመራሉ!!ተስፋዬ ገብረየሱስ ተመልሰዋል!!!ዋልያ አረንጓዴ ይለብሳል!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.