ዜና ካላባር…ደጉ ላይሰለፍ ይችላል! ኬሺ 4ት ሀገራት…ጆን ኦቢ ሚኬል…ታዳጊ ዋንጫ

ደጉ ደበበ በጉደት ምክንያት የዛሬን ጨዋታ የመግባቱ ነገር አጠራጣሪ መሆኑን አሰልጣኝ ሰዉነት ቢሻዉ ተናግረዋል፤.በሱ ምትክ ሳላሀዲን ባርጌቾ እንደሚገባ ታዉቅዋል፤ቢያድግልኝ ልያሥ ሌላዉ በቦታዉ መሰለፍ የሚችል ተጫዋች ነዉ!!ደጉ የቦትስዋና ጨዋታ የአሰልጣኙ ማስተማሪያ ወድቆበት ባለቀ ሰአት በጉዳት መዉጣቱ ይታወሳል፤ ካላባር ከእንቅልፍ እየነቃች ነዉ፤ጋዜጦች በጨዋታዉ ዙሪያ ብዙ አስተያየቶችን እያስነበቡ ነዉ፤አንዱ ጋዜጣ ስለኬሺ እንዲህ ብሎአል፤ኬሺ የብዙ ናይጄሪያዉያን ጀግና ነዉ፤የአፍሪካ ዋንጫን በልትዋል፤አሁን ደግሞ ለአለም ዋንጫ እናልፋለን…ነገር ግን አሰልጣኛችን ደሞዝ የለዉም…ኬሺ 4ት የአፍሪካ ሀገራት ብሂራዊ ቡድኖች የአሰልጥነን ጥሪ እንዳቀረቡለት ተናግርዋል፤ነገር ግን ለሀገሬ ያለኝ ፍቅር በገንዘብ የሚለካ አይደለም፤ያም ቢሆን ለተጫዋቾቹ የሚሰጠዉ ቦነስ ማነስ ናይጄሪያን ከሚያክል ቡድን አይጠበቅም ብልዋል፤ጋና ለግብጹ ጨዋታ 15ሺ ዶላር ግብጻዉያኑ ደግሞ 25ሺ ዶላር ቃል ተገብቶላቸዋል እኛስ አንዴት 5ሺ ብቻ እንባላላን፤የአህጉሩን ዋንጫ በልቶ በቦነስ የሚከራከር ቡድን የእኛ ብቻ ነዉ..ኬሺ አስተያየቱን ሰጥትዋል፤ ጀን ኦቢ ሚኬል የዛሬን ጨዋታ በቀላሉ እንደሚያሽንፉ ቡድናቸዉ በጣም ጠንካራ እንደሆነ ተናግርዋል፤”ሚኬል ማሳጅ ተደረገ ”የሚል የዜና ርአስ አይቼ ገርሞኛል፤እያንዳንድዋን ትንሽ ክስተት ለአንባቢ ለማሳወቅ የሚያደርጉት ጥረት ገርሞኛል፤ የታዳጊ ቡድኑ የአለም ዋንጫን አግኝትዋል፤ዛሬ በስታድየምም ተገኝቶ አቀባበል ይደረግለታል፤እቅዱ ዋናዉ ካሸነፈ በሁዋላ አብሮ ለመጨፈር ነዉ፤ጨዋታዉ አሁን 8 ሰአታት ገደማ ብቻ ቀርቶታል፤ ዋልያዉ አሁን ለቁርስ እየተነሳ ነዉ፤ከዛ በሁዋላ ያሉትን አዳዲስ ነገሮችና አሰላለፍ ይዘን ከች እንላላን!!

5 thoughts on “ዜና ካላባር…ደጉ ላይሰለፍ ይችላል! ኬሺ 4ት ሀገራት…ጆን ኦቢ ሚኬል…ታዳጊ ዋንጫ

  1. I am glad that Degu will not play. I think he is not up to the level of the other team members. Saladin is a better defender that Degu at this moment. I also wish – Umoud Owedkery will not even be at the bench – I don’t actually know why he is in the team at all.

    GO Ethio GO!

Leave a Reply

Your email address will not be published.