ዘጠኝ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በአበረታች መድሃኒት ተጠርጥረው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው

Athletics Doping

Athletics Doping

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዘጠኝ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በአበረታች መድሃኒት ተጠርጥረው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን የኢትዮጵያ የፀረ አበረታች መድሃኒት ኤጀንሲ ገለፀ።

ከእነዚህም ውስጥ አምስቱ በተለያዩ ውድድሮች ውጤት ያስመዘገቡ ታዋቂ አትሌቶች መሆናቸውን ነው ኤጀንሲው ያስተዋቀው።

የኤጀንሲው ዋና ፀሃፊ አቶ ሰለሞን ማዕዛ ለአሶሼትድ ፕረስ እንደገለፁት፥ ኤጀንሲው ታዋቂ አትሌቶቹ የአበረታች መድሃኒት ተጠቀምዋል የሚል የቤተ ሙከራ ውጤት ከደረሰው በኋላ ምርመራ እያደረገ ነው።

የአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌደሬሽኖች ማህበር የቀሪዎቹን አራት አትሌቶች ማንነት ይፋ እንዲያደርግ መጠየቁንም አስታውቀዋል።

አቶ ሰለሞን እነዚህ አትሌቶች ተጠቅመውታል በሚል የተጠረጠሩትን የተከለከሉ አበረታች መድሃኒቶች አይነት ምርመራው እየተካሄደ በመሆኑ ይፋ አላደረጉም።

ኢትዮጵያ ከሩሲያ እና ኬንያ በመቀጠል በአበረታች መድሃኒት ወቀሳ እየቀረበባት የምትገኝ ሀገር ሆናለች።

ዘጠኙ አትሌቶች የፀረ አበረታች መድሃኒት መጠቀማቸው ከተረጋገጠ ሀገሪቱ በሪዮ ኦሎምፒክ ለማግኘት ያቀደችውን ውጤት ለማስመዝገብ ችግር ይፈጥርባታል ተብሏል።

ምንጭ:- ፋና

1 thought on “ዘጠኝ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በአበረታች መድሃኒት ተጠርጥረው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published.