ዘመቻ ካላባር….የጉዞ ማስታወሻ

 

አብረዉኝ የነበሩት 14ት ሰዎች በዚህ ርእስ የሚስማሙ ይመስለኛል፤ከጀርመን ይህንን ጨዋታ ለማየት የመጣ ሰዉ እዚህ ቡድን ዉስጥ ይገኛል፤የሀገር እግር ኳስ ፍቅሩ በጣም ይገርማል፤የአየር መንገዱ ካፕቴንም ከኛ ጋር ናቸዉ..ሰይፉ ፋንታሁን በኢቢኤስ ሳይሆን በካላባር ነዉ የምታገኙት፣ታደለ አሰፋ የኢትዮጲፒካ ሊንኮቹ ዮናስ እና ብርሀኔ…ወደ ደቡብ አፍሪካ በመኪና ከተጓዙት መሀልም አንድ ሰዉ ይገኛል፣፣፣የፊደል ሬስቶራንቱ ባለቤት ኤፍሬምም ከአጠገቤ ነዉ፤16ት ምግቦችን ይዞ ነዉ የመጣዉ..በስልክ የታዛቸዉን…የ15 ሰዎች ጉዞ ወደ ካላበር መሆኑ ነዉ!! ከአዲስ አበባ ኢኑጉ 5 ሰአተ የፈጀ በረራ ተደረገ..ከኢኑጉ በባስ ወደ ካላባር የ3ት ሰአት መንገድ መሆኑ ነበር የተነገረን..እናም ባስ ተከራየን.እያንዳንዱ ተሳፋሪ 40ዶላር አዋጥቶ 600 ዶላር ከፍለን መንገድ ጀመርን፤ተወካያችን ሚልዮን ይባላል.ድንገት የሚወስደን ሹፌር ስልክ ተደወለለትና…በቃ መመለሴ ነዉ ገንዘብ እንዳልከፈላችሁ ነግረዉኛል አለን፤በሰዉ ሀገር የመብት ማስከበር ክርክሩ እዚህ ላይ ተጀመረ፤ሚልዮን አልቻለም፣በጣም ተናድዋል..በዛ ሙቀት የመጣነዉን ያህል ልንመለስ ነዉ..በዛ ላይ ብሩን የከፈለዉ እሱ ነዉ…ፖሊሶች ሲያይ መኪናዉን አቁም ብሎ በጣም ጮሀ..ሹፌሩ በድንጋጤ አቆመ..ፖሊሶቹ እስኪመጡ ሚልዮን የማይለዉ ነገር የለም፤እዚህ ኢምባሲ አለን..አታጭበረብሩንም…ብራችንን መልስ…ብቻ የሹፌሩን ሸሚዝ ጨምድዶ ይዞ አለቅም አለ..ፖሊሶቹ መጡ፤በደንብ የታጠቁ ናቸዉ፤ጉዳዩን ማስረዳት ጀመርን..ትንሽ ቆዩና የራሳቸዉን ነገር ማማቻቸት ጀመሩ…አብረዉን ወደ መነሻ ቦታችን ተመለሱ፤ከዚህ ካላበር ድረስ ለዛዉም ናይጄሪያ ዉስጥ እንዴት ብተደፍሩ ነዉ ብቻቸሁን የምትሄዱት አሉ…. እናም ፖሊስ በ200 ዶላር ተከራይተን ጉዞ ወደ ካላባር…3ሰአት ይፈጃል የተበላዉ መንገድ ከ6ሰአት በላይ ወሰደ..መሀል ላይ የረሀቡ ሁኔታ ጫፍ ደረሰ… እናም ቀስ በቀስ ድምጹ ከፍ ያለ ዘፈን መሰማት ጀመረ፤ከወደ ሁዋላ “የቴዲ ዶሮ ይበላ” የሚለዉ ድምጽ አስተጋባ…የምግቡ ባለቤቶች ካላባር ነዉ ያሉት..እነ ቴዲ አፍሮ መሆናቸዉ ነዉ፤እዚህ ያለነዉ ደሞ በረሀብ ልንሞት ነዉ፤በዚህ መሀል ምግቡን ከሆቴሉ አሰርቶ ያመጣዉ ኤፍሬም አጣብቂኝ ዉስጥ ገባ… ትንሽ ቆይቶ በፆም ምግቦች ተጀመረ…ሰሀን የለም፤እጅ መታጠቢያ ዉሀ የለም፤አንድ ኮስተር ባስ ዉስጥ 15 የተራቡ ኢትዮያዊያን ደጋፊዎች እነሱን ያጀቡ ሁለት ፖሊሶች ሹፌሩና ረዳቱ ብቻ ናቸዉ ያሉት….ላስቲክ ጊዚያዊ ሰሀን ሆነ..እናም የካፕቴኑ ለክፉ ቀን የተቀመ ምግበ ከተበላ በሁዋላ ሌላዉ ላይም ተፈረደበት፣፣፣ አሁን ረሀቡ ትንሽ ጋብ ብልዋል፤ቀጣዩ ደግሞ ዉሀ ነዉ፤መንገዳችን በጣም ከመርዘሙም በላይ አስፈሪ ጫካዎችን እያለፍን ነዉ የምንሀደዉ፤የሹፌሩ አነዳድ ደግሞ አይምሬ ነዉ፤በዛ ጠባብ ኮረኮንቻማ መንገድ መኪኖችን ሲደርብ አይን የለዉም፤የመንገዱን ርዝመት ያየዉ ሰይፉ ፋንታሁን…Wel come to Cameroun የሚለዉን ስታዩ ንገሩኝ ብሎ አስፈግዋል፤አታካቹ መንገድ መሀል አንዲት አመዳማ የገጠር ቀበሌ ነገር ላይ መኪናዉ ቆመ፤እናም ከትንሽዬ ሱቅ አጠገብ ካለዉ ትልቅ በርሜል ቆሻሻ ዉሀ እያወጣን እጃችንን ታጠብን…12.30 ካላበር ይገባል የተባለዉ ባስ ከምሽቱ 3 ሰአት ገደማ ካላባርን አሳየን..የናፍቆትዋን ሀገር ሙቀትም ገና ከመግባታችን በሆቴሉ ዉስጥ የነበሩት ነገሩን፤ ዛሬ የቁርጥ ቀን ነዉ፤ትላንት የመጡት ደጋፊዎቹ እዚህ ካሉት ጋር በመሆን በስታድየም ቡድኑን ለማበረታታት ተነጋግረዋል፤ለተጎሳቀሉት ዜጎችም ማስታወሻ የሚሆን ነገር ለማድረግም ተነጋግረዋል፤ ከጀርመን የመጣዉ ደጋፊ 14 አመት እዛዉ ኑርዋል፤የካዛንቺስ ሰፈር ሰዉ ነበር፤እናም ያለኝ ነገር ከአእምሮዮ አልጠፋ ብሎ አስቸግሮኛል፤ “እኔ እዚህ መምጣቴ ሀገሬን በመዉደዴ ነዉ፤የጊዮርጊስ ዳገፊ ነኝ፤ቱኒዚያ ድረስ ሂጄ ተጫዋቾቹን ደግፌያለሁ…አንዳንድ ጊዜ የሀገሬን ኳስ ለማየት ሁሉም መንገድ ሲዘጋብኝ አንድ ነገር አደርጋለሁ..ምንም ለኳስ ግድ የሌለዉ ወንድሜ ጋር ሀገር ቤት ስካይፕ እደዉላለሁ..እናም ካሜራዉን ወደ ቲቪዉ ያደርግልኛል፤በሀገር ዉስጥ ብቻ የሚተላለፈዉን ጨዋታ በዚህ መንገድ አየዋለሁ…እናም እባካችሁ ሁሌም የብሂራዊ ቡድኑ ጨዋታ ይተላለፍልን” የካላበር 2ተኛ ቀን ቆይታ የጡዘቱ ዋና አካል ነዉ፤አሁን ለጨዋታዉ 4 ሰአታት ብቻ ይቀራሉ፤

13 thoughts on “ዘመቻ ካላባር….የጉዞ ማስታወሻ

Leave a Reply

Your email address will not be published.