ክሊሜንቴ አጭበረበረን!!??

IMG_1108[1]

ሽሜዉ ደንግጥዋል፡፡ለምን እነደሆነ በኋላ ነዉ የገባኝ….ከጨዋታ በኋላ የመጀመሪያዉን  ጥያቄ የማቅረብ  እድል ተሰጠኝ…”የዋልያዉ ደካማ ጎን ምን ነበር እንዴት አሸነፋችሁት አልኩት”???፡–ተተረጎመለት–“አረ በጭራሽ ዋልያዉ የምድቡ በጣም ጠንካራ ቡድን ነዉ፡፡”አለኝ፡-ሴትየዋ የጥያቄዎች አስተናባሪ ናት፡፡”ጥያቄህ ተመለሰለህ ?”አለችኝ..አይ በሌላ መንገድ ልጠይቀዉ አልኩዋት…ዋልያዉን ለማሸነፍ የተጠቀማችሁበት ታክቲክ ምንድነዉ??አሁንም ጮሌዉ አስተርጓሚ ፈጥኖ አደረሰ፡፡ ስፔናዊዉ ቀጠሉ..”ምንም ደካማ ጎን የላቸዉም፡ድክመታቸዉ እንደኛ አይነት በጣም ጠንካራ ቡድን መግጠማቸዉ ነዉ” አሉን፡፡ሁሉም ጋዜጠኛ ተገረመ፡-እኚህ ሰዉ የቀድሞዉ የሊቢያ መሪ ወይሥ አሰልጣኝ….

ሌሎች ጥያቔዎችም ቀጠሉ፡፡ሰዉየዉ የማይገኛኙ መልሶቸን ያስቀምጣሉ፡፤የካፍኦንላይኑ ኬኔዲ ግን ፈተናቸዉ፡፡”ዋልያዉን የምድቡ ጠንካራ ቡድን ካሉ በቃ ጋና እና ኮንጎን አሸንፈዉ እንዳለፉ እንቁጠረዉ አላቸዉ??”–አሁን ደጋግመዉ አሰቡበትና..”አይ ዋልያዉ ምድቡ ዉስጥ ካሉት ጠንካራ ቡድኖች አንዱ ነዉ ማለቴ ነዉ” አሉ፡፡አልሸሹ እንትን አሉ ማለት ነዉ!!

ጋዜጣዊ መግለጫዉ አለቀና አስተርጓሚዉን በግላጭ አገኘሁት፡-እንዴት ነዉ ነገሩ አልኩት፡-በደንብ ገብቶታል፡፡”አይ ቡድናችሁ እኮ ታክቲኩ ጥሩ አደለም እንጂ አሪፍ ነዉ” አለኝ፡፡እንዴት የምድቡ ጠንካራ አሉት ስለዉ ግን እዉነታዉን በወዳጅነት መንፈስ መለሰልኝ—“በፍጹም እናንተን ለማሸነፍ አላሰብንም ነበር፡፡2ተኛዉ ጎል ሲገባ ሽማግሌ(እሱ የሚጠራዉ በዚህ ስሙ ነዉ) በጣም ደንግጥዋል፡፡ለማመንም ጊዜ ወስድዋል፡፡እናም ብዙ ነገር ቢያወራ አትፍረድበት” አለኝ፡፡

“እኛ ከጦርነት የመጣን ሰዎች ነን፡፡እሱ ደግሞ ስራ ያልነበረዉ ሰዉ ነዉ፡፡እስከምንግባባ ድረስ መታገስ ነዉ–ድሉን ከፍ ለማድረግ ተጋጣሚዉን ማዋደድ አለበት” አለኝ!!!እኔ የቲቪዉ ባልደረባዬ መኳንንት እና የካፉ ኬኔዲ ተያይተን ተሳሳቅን!!አስተርጓሚዉን 90 ደቂቃ ሙሉ እየተነሳ ሲንቆራጠጥ ያያችሁት ነዉ!

ለማንኛዉም ስፔንን ለ2ት አለም ዋንጫና እና 1 አዉሮፓ ዋንጫ ከመራት ክሊሜንቴ ጋር ፎቶ ተነሳን፡፡በቻን ዉድድር ስላልተጠየቁት የሚያወሩ አሰልጣኞች መበራከት እየተገረምኩ!!! ክሊሜንቴ እድለኛ ይሁኑ እዉነተኛ ከጋና ጋር ይለይላቸዋል!!

 

18 thoughts on “ክሊሜንቴ አጭበረበረን!!??

 1. Said is by far the best sport reporter ETV has gotten. He is a well informed and well rounded person. He put effort to dig up unheard histories from past and does his research before putting his reports out. He catches my attention when ever he put a report. Young man I admire your determination and passion for your work. Keep on doing the good work. Good Luck.

 2. @YewalyaDgf
  Finally someone who knows what they are talking about. Said does his research before putting his report together. He is by far the best sport reporter with a great passion ETV has got. some crappy peoples’ comment are just out of point. Gegema becha!

 3. deronem Kedeze aynet (anten malete newe) dedeb keze yanese aseyafe negre aytebekem.
  I bet you can’t do quarter of the report that Said does. I can see your illiterate when you bring the idea of terrorism in middle of soccer match report. dedeb, fara!

 4. @Death for GK.
  please leave your negatively and dark criticism at the door. Support your words with evidence , not emotion. who do you think you are to tag a name for others? I can smell your a hater from you dead words. Fara!

 5. ጎበዝ አናዳንድ መሻሻል በብሔራዊ ቡድናችን ላይ መታየቱ ማንም የማይክደው ሐቅ ሆኖ ሳለ፡፡ ከብሔራዊ ቡድናችን የምንጠብቀው ውጤት ግን ጤናማ አይመስለኝም፡፡ ውጤት በሞራል፣ በበጎ ፍላጎት እና ጉጉት ብቻ የሚመጣ አይደለም፡፡ ለዚህ ጤናማ ላለልሆነ ትክክለኛ አቅማችንን ያላገናዝበ ውጤት ናፍቆት (ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ) የሜዲያዎች ሚና ከፍተኛ ነው ባይ ነኝ፡፡ ብሔራዊ ቡደን የሚመረጠው ካሉት ክለቦች ነው፤ የክለቦቻችንን አቋምና ብቃት መካከለኛ ብቃት ካላቸው የአፍሪካ ክልቦች ጋር አንኳን ብናነጻጽረው በጣም የወረደ ነው፡፡ ወገን እረባካችሁ በእግዚአብሄር እርዳታ ብልጭ ድርግም በሚል ምንም ወጥ ያልሆነ ውጤት ላይ ከመኮፈስ ብዙ ይጠበቅብናልና ጠንክረን የክለቦቻችንን አቋምና አቅም መገንባት እና ከአቻ የአፍሪካ ክልቦች ጋር ተወዳዳሪ እነዲሆኑ በየክልሉ ሰፋ ያለ የ እግር ኳስ ፕሮጀክቶችን በመዘርጋት እና በመተግበር በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮና አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ እነዲችሉ በማድርግ ስራ ላይ እንረባረብ፡፡ ይህን ማድረግ ስንጀምር ያን ጊዜ ውጤት እንጠብቅ እንጂ ውጤት ዝም ብሎ ከሰማይ አይወርድምና ጉራችንን ትተን ሁሉም ሐላፊነቱን ቢወጣ ይሻላል ባይ ነኝ፡፡ ታዛቢው

 6. why should we give a crap about what a translator said, saied! Pessimistic journalism has killed the support Waliya receives. Its sad. With that being said, I still think swenet’s contract should be prolonged for at least two years, for he has done much more than to the revitalization of Ethiopian football than any “journalist” could have ever. 😀

 7. @ Said Kiyar koy gin neutral honehe le-mezegeb new yehedkewe or le-GK yalehin degafe lemasayet new ?

 8. bizu confidence selebeza new yeteshenefinew habeshnetachin gelonal b/c sewenet encuan yemibelaw alatawem menoriyam endezaw belual yih malet esekezi becha new life lela minabatu endemalet selehone……………..

 9. ተተኪ ያስፈለልገናል፣ በዚህ ደግሞ ፈደሬሽኑ አልስራም፣ ይሄ የረጅም ጊዜ ችግር ነው፤ አሁንም ይታሰብበት፡፡

 10. hulunem chewataweche bedel mewetat malet eko ashenafi weyme tenkara ayasebelem mikiniyatum eskahun ulunem chewata bedel yeteweta yelemna gen tenkara techawache ale

 11. Ive been reading Said’s articles for a while I always thought he was too critical about Sewnet Bishaw. Now I know Said Kiar is not stupid. You clearly read Clemente very well. That is what is missing from the Walya coaching team. They underestimate the opposition, they dont study them very well; they dont prepare for each game according to the style and formation of the opposition. And when things dont go well, they turn around and blame their players. They should learn a thing or two(*awctually a whole lot) from people like Clemente. They dont exaggerate their strength even after a win and they certainly dont underestimate any opposition even after beating them.

Leave a Reply

Your email address will not be published.