11403047_501556653332293_5789500593118031795_n

11403047_501556653332293_5789500593118031795_n

(በዳንኤል አማረ ©ኢትዮጤና)
ለበለጠ የጤና መረጃ ይህን ገጽ ላይክ ያድርጉ www.facebook.com/EthioTena

በፊንጢጣ አካባቢ የሚገኙ የደም ቧንቧዎች ሲያብጡ የሚፈጠር በሽታ ነው ይህ ችግር ከፍተኛ ክመም እና ስቃይ አለው ነገር ግን የከፋ ህመም ደረጃ ላይ አያደርስም፡፡
በፊንጢጣ ውስጥ የሚገኙ የደም ቧንቧዎች ሲያብጡ ውስጣዊ ኪንታሮት ይፈጠራል ወይም በፊንጢጣ ቀዳዳዎች አካባቢ ሲያብጡ ደግሞ ውጫዊ ኪንታሮት ይፈጠራል፡፡ ሁለቱም አይነት ኪንታሮቶች በተመሳሳይ ጊዜ በአንድ ሰው ላይ ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡
በዳሌና ፊንጢጣ አካባቢ ያሉ የደም ቧንቧዎች ውጥረት ሲበዛባቸው ኪንታሮት ይፈጠራል፡፡ በፊንጢጣ ውስጥ የሚገኙ ጡንቻዎች በደም ይሞላሉ ይህም የአንጀትና ሆድ ዕቃ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር ያመቻል፡፡ ሽንት ቤት ውስጥ ለረጂም ጊዜ ተቀምጠን በምንቆይበት ጊዜ የውጥረት መጨመር በፊንጢጣ ጡንቻዎች ውስጥ ያሉትን የደም ቧንቧዎች እንዲያብጡና እንዲለጠጡ ያደርጋቸዋል ይህም ኪንታሮት እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡

*የኪንታሮት መነሻ ምክንያቶች
ኪንታሮት በአብዛኛው የሚከሰተው በዳሌና ፊንጢጣ አካባቢ የሚገኙ የደም ስሮች ላይ ጫና ሲጨምርባቸው ይፈጠራል፡፡ ግፊት በሚጨምርበት ጊዜ ደም ወደ ስሮቻችን ይገፋና እንዲያብጡ ያደርጋቸዋል፡፡ እነዚህ ያበጡ ስሮቻችን በአካባቢ የሚገኙ ጡንቻዎቻችንን ይለጥጧቸውና ኪንታሮት እንዲፈጠር ያደርጋሉ፡፡

የሚከተሉት ልምዶች የደም ግፊትን በፊንጢጣ አካባቢ በመጨመር ኪንታሮት እንዲፈጠር ያደርጋሉ፦

• ሽንት ቤት ስንቀመጥ በጣም ማማጥና መቻኮል
• ቀጣይነት ያለው ተቅማጥ ወይም የሆድ ድርቀት
• ከመጠን ያለፈ ውፍረት በተለይ በሆድና ዳሌ አካባቢ
የደም ስሮቻችንን ግፊት በመጨመር ለኪንታሮት ያጋልጠናል፡፡
• እርግዝና እና ወሊድ
በእርግዝና ወቅት የሆርሞኖች ለውጥ ስለሚኖር ወደ ዳሌና አካባቢው የደም ዝውውር እንዲጨምር ያደርገዋል፡፡ በወሊድ ጊዜ ህፃኑን ገፍቶ ለማውጣት/ሲያምጡ በፊንጢጣ አካባቢ ውጥረት(Pressure) እንዲጨምር ስለሚያደርገው ለኪንታሮት ሊያጋልጣቸው ይችላል፡፡
• የተለያዩ በሽታዎች
ለረጂም ጊዜ የቆየ የልብ እና ጉበት በሽታ ደምን በከርስና ዳሌ አካባቢ ስለሚገፉት የደም ቧንቧዎች እንዲያብጡ ያደርጋቸዋል፡፡

*የኪንታሮት ምልክቶች
• በአንጀት ጡንቻዎች እንቅስቃሴ ጊዜ ህመም የሌለው ደም ይኖራል፡፡ ፈካ ያለ ቀይ ደም በሶፍት ላይ ይታያል፡፡
• በፊንጢጣ አካባቢ የማሳከክ እና የማቃጠል ስሜት
• ህመም ወይም ምቾት ማጣት
• በፊንጢጣ አካባቢ ማበጥ
• በፊንጢጣ አካባቢ እባጭ መኖር፡፡ እባጩ ህመም ይኖረዋል፡፡

የኪንታሮት ክመም ምልክቶች እንደሚገኝበት ቦታ ይወሰናል፡፡ ውስጣዊ ኪንታሮት በፊንጢጣ ውስጥ ይገኛል ማየትም ሆነ መዳሰስ አንችልም ስለዚህ ምቾታችንን አይነሱትም ነገር ግን በምንፀዳዳበት ጊዜ ህመምና ማንጣጣት ይኖራቸዋል፡፡
ውጫዊ ኪንታሮት በፊንጢጣዎ አካባቢ በሚገኝ ቆዳ ላይ ይገኛል፡፡ በሚያንጣጣን/በሚያቃጥለን ጊዜ የማሳከክ ወይም የመድማት ሁኔታ ይኖራል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደም ውጫዊ ኪንታሮትን በመግፋት የደም መርጋት እንዲፈጠር ያደርጋል ይህም ከፍተኛ ህመም፣ ማበጥና ማቃጠል ይኖረዋል፡፡

የኪንታሮት ህክምና
አብዛኛዎቹን የኪንታሮቶች ህመሞች የምግብ ለውጥ በማድረግ በቀላሉ ማስተካከል ይቻላል፡፡ ያለብን የኪንታሮት መጠን በጣም ትልቅ ካልሆነ እና ህመም ህመም ካልኖራቸው ምንም ዓይነት ቀዶ ጥገና ወይም ሌሎች ህክምናዎች ላያስፈልጉት ይችላሉ፡፡

ኪንታሮትን ለማከም ከቀዶ ጥገና ውጪ የሚደረጉ ህክምናዎች የማለስለሻ ህክምናዎች ሲሆኑወደ ኪንታሮት የሚሄደውን ደም በመቀነስ እንዲጨማደድና እንዲደርቅ ያደርጋቸዋል፡፡ ይህ የተጨማደደው ቦታ ሌሎች አዳዲስ ኪንታሮቶች እንዳይወጡ ያግዛል/ይከላከላል፡፡
በአብዛኛው ኪንታሮቶችን በቀዶ ጥገና ማስወገድ ግድ የሚሆነው ኪንታሮቱ ትልቅና ውስጣዊ ሲሆን ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ማለስለሻና ቀዶ ጥገና በማቀናጀት ህክምና ይደረጋል፡፡

*የኪንታሮት መከላከያ መንገዶች
• የመፀዳዳት ወይም ሽንት ቤት የመቀመጥ ስሜት ሲሰማዎት ቶሎ ወደ ሽንት ቤት ይሂዱ፡፡
• ሲፀዳዱ ዓይነ ምድርዎን ለማስወገድ/ለማስወጣት ማማጥ የለብንም ተፈጥሮ በለገሰችን መንገድ በራሱ ጊዜ እንዲወገድ ይተውት፡፡
• ሽንት ቤት ተቀምጠው በፍጹም ጋዜጣ ወይም ሌላ ነገር አያንብቡ፡፡
• ለረጂም ጊዜ መቀመጥ ወይም መቆም የለብንም፡፡
• የሚቻል ከሆነ ከባድ ነገሮችን በተደጋጋሚ አያንሱ፡፡ የሚያነሱ ከሆነ ደግሞ ትንፋሽዎን ሳያምቁ በሚያነሱበት ጊዜ ወደ ውጪ ይተንፍሱ፡፡
• ነፍሰጡር(እርጉዝ) ከሆኑ በዳሌዎ አካባቢ ያለውን የደም ፍሰት ውጥረት ለመቀነስ በጐንዎ ይተኙ፡፡
• የሆድ ድርቀትን ይከላከሉ
• በየዕለቱ የሚመገቡት ምግብ ዉስጥ ፍራፍሬ፣ አትክልቶችና ጥራጥሬዎችን ይጨምሩ/ያካትቱ እነዚህ ምግቦች ከፍተኛ የሆነ ፋይበር አላቸው፡፡
• በቂ የሆነ ውሃ ይጠጡ
• በየቀኑ እንቅስቃሴ ያድርጉ፦ መካከለኛ የሆነ ቢያንስ ለ2 ½ ሠዓት እንቅስቃሴ ያድርጉ፡፡
• በእንክብል መልክ የተዘጋጁ ለምሳሌ፦ ሲትሩሴል(Citrucel) ወይም ሜታሙሲል(Metamucil) አስፈላጊ ከሆነ በየቀኑ ይውሰዱ፡፡

መልካም ጤንነት!!

ለበለጠ የጤና መረጃ ይህን ገጽ ላይክ ያድርጉ www.facebook.com/EthioTena

9 thoughts on “ኪንታሮት

  1. I like it and I found that u guys brought good issues with solutions.so keep it up

  2. It is very important information I like it because I am on of the victim this and have got the necessary and essential information.
    Keep in touch

Leave a Reply

Your email address will not be published.