ከድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን የተሰጠ መግለጫ

Diredawa Police Logo
 
በድሬደዋ አስተዳደር ቀበሌ 01 መልካ ጀብዱ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ መስከረም 21 ቀን 2011 አ.ም ምሽት ላይ በግለሰብ ላይ የደረሰን ጉዳት ወደ ብሄር ግጭት ተለውጦ ሁከትና ርብሻ የተከሰተ ሲሆን በዚህም 1ሰው በደረሰበት ድብደባና የስለት ጉዳት ህይወቱ ሲያልፍ ሌላ 1 ሰው በጥይት ተመቶ ህይወቱ አልፏል ሌላ አንድ ሰውም እግሩ በጥይት ቆስሎ በህክምና ላይ ይገኛል::
 
ፖሊስ ሁኔታውን በመቆጣጠር አካባቢውን ወደ ቀድሞ ሰላም ለመመለስ ከፌደሬል ፖሊስ ከመከላኪያና ሌሎች የፀጥታ ሀይሎች ጋር በመሆን ግጭቱን የማስቆምና የማረጋጋት ስራ እየሰራ ሲሆን 51 ተጠርጣሪዎችንም ይህ መግለጫ እስከ ተሰጠበት ግዜ ድረስ በቁጥጥር ስር አውሏል::
 
በመሆኑም ከዚህ በሃላ ግጭትና ሁከቶችን በመፍጠርና አለመረጋጋት እንዲኖር በማድረግ የግል ፍላጎትና ጥቅማቸውን ማሳካት የሚፈልጉ ማናቸውም ግለሰቦችና ቡድኖችን ፖሊስም ሆነ መላው የፀጥታ ሀይል የማይታገስና አስፈላጊውን እርምጃ የሚወስድ መሆኑን በጥብቅ ፖሊስ እያሳሰበ ወላጆችና መላው ማህበረሰብ ይህንኑ በመረዳትና በመገንዘብ ልጆቹን እንዲመክርና በእንዲሂ ያለህ ተግባር እንዳይሳተፉ በማድረግ የድርሻውን እንዲወጣ ሲል ፖሊስ ጥሪውን ጨምሮ ያቀርባል::
 
መስከረም 22 ቀን 2011 አ.ም