ኢትዬ-ናይጄሪያዊዉ የዋልያ አጥቂ ይናገራል!!

 

“ አባቴ ከእንግሊዝ ጋር ጣሊያንን ተዋግትዋል”…ኢስማኢል አቡበከር ሰዉነት ቢሻዉ 1991 ላይ የኢትዮጲያ ታዳጊ ቡድንን ይዘዋል፤አዲስ አበባ ላይ በማጣሪያ ጨዋታ 2-2 ተለያዩ፤ለመልሱ ጨዋታ ግን አንድ አወዛጋቢ ተጫዋች ተፈጠረ፤ለቡድኑ ይመጥናል ተብሎ ይዘዉታል፤ማሰለፍም ይፈልጋሉ..ግን ደግሞ ፈሩ፤ተጫዋቹ አዲስ አበባ ነዉ የኖረዉ..ግን አባቱ ናይጄሪያዊ ናቸዉ፤ለ40 አመት ያህል ኢትዮጲያ ዉስጥ ኖረዋል..እናም ከኢትዮጲያዊት እናት ነዉ የወለዱት…ይህን ተጫዋች ብንወስደዉ አንድ ሰዉ አቃጥሮብን ያስቀጣናል፤ፊፋም ይከለክላል በሚል ክርክር ተነስቶ እስማኢል ከናይጄሪያ ጉዞ ቀረ!! ብሪሞ ሜዳ መቸስ ታቁታላቸሁ…እሱን እንኳ ብታጡት ልደታን ታስታዉሳላችሁ…እስማኢልም የተወለደዉ እዛዉ አከባቢ ነዉ፤ናይጄሪያን በጭራሽ አያቃትም፤በብሂራዊ ቡድን እና በክለብ ጨዋታ ትራንዚት ሲያደርግ ብቻ አየርዋን ለደቂቃዎች አሽትትዋል፤ጊዮርጊስን ጨምሮ በተለያዩ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ተጫዉትዋል፤በጋርዚያቶ ቡድን ዉስጥም በአርጀንቲናዉ የአለም ዋንጫ ላይ ተሰልፍዋል፤ከኮስታሪካ ጋር ምርጥ 11 ዉስጥ ገብትዋል፤የሆላንዱ ጨዋታ ቀን ደግሞ ተቀይሮ ገብቶ በአለም ወጠቶች ዋንጫ ዋልያን ወክሎ ተጫዉትዋል፤ “እኔ ስለናይጄሪያ ምንም ስሜት የለኝም፤የተማርኩት ከፍተኛ 4ት ነዉ፤ያደጉት ብሪሞ ሜዳ…ስለአባቴ ሀገር ባህል ሆነ ሌላ ነገር ምንም አላቅም…አባቴ በኢትዮጲያ የመጣ የመጀመሪያዉ ናይጄሪያዊ ነዉ፤እንግሊዝ ናይጄሪያን ቅኝ ስትገዛ እሱ ወታደር ሆነ..ወደ ኬንያም ተልኮ መጣ…ከዛም ጣሊያንን ከኢትዮጲያ ለማባረር በተደረገ ጦርነትም ተዋግትዋል…”ይላል ቤታችን ከምእራብ አፍሪካ ለሚመጡ ሰዎች እንደኢምባሲ ነዉ፤አባቴ በህይወት እያለ ከማሊ..ኒጀር..እና አከባቢዉ የሚመጡ ሰዎች ሳይቀሩ እኛ ቤት ነበር የሚያርፉት.. እስማኢል አሁን በአሰልጣኝነት ሙያ ዉስጥ ገብትዋል፤የ ሲ ላይሰንስ ስልጠና እና የሆላንዶችን የታዳጊ አሰልጣኞች ስልጠና ላይ ተካፍልዋል፤የከላባር ወበቅ ሀይለኛ ነዉ..ስለዚህ በካዉንተር መጫወት አለብን..ምክንያቱም ኢኮኖሚካል ፉትቦል መጫወት ምንችለዉ በዛ መንገድ ነዉ ባይ ነዉ፤ የኛና የነሱ ደረጃ ይለያያል፤እነሱ በብዙ ነገር ይበልጡናል፤በተለይ በአካል ብቃት ደረጃ..እናም እኛ ያንን ነገር ለማካካስ በፓስ እና እይታ በጣም የታደሉ ተጫዋቾችን መያዝ አለብን!!እስማኢል ነዉ የሚለዉ!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.