ኢህአዴግ በአብላጫ ድምፅ ማሸነፉን የምርጫ ቦርድ በይፋ ገለጸ

ቦርዱ ዛሬ ሰኞ ሰኔ 15 ፣2007 በሒልተን ሆቴል የመጨረሻውን የማጠቃለያ የምርጫ ውጤት ይፋ አደረጓል፡፡
ፓርቲው ለመራጭነት ከተመዘገበው ህዝብ 82.4 በመቶውን ድምፅ ማግኘቱ ታውቋል፡፡
በዘንድሮው ምርጫ 212 ሴቶች ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነት የሚያበቃቸውን ድምጽ አግኝተዋል፡፡
ከአጋር ድርጅቶች ደግሞ አብዴፓ 9፣ ኢሶህዴፓ 24፣ ቤጉዴፓ 9፣ ጋኃዴን 3 እንዲሁም ሐብሊ 1 መቀመጫዎችን አግኝተዋል፡፡
ለክልል ምክር ቤት በተደረገው ምርጫ በትግራይ ህወሃት 152፣ አፋር አብዴፓ 93 እና አህዴድ 3፣ በአማራ ብአዴን 294፣ በኦሮሚያ ኦህዴድ 597፣ በኢትዮጵያ ሶማሌ ኢሶህዴፓ 273፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ቤጉዴፓ 99፣ በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ደኢህዴን 345፣ በጋምቤላ ጋህዴን 155፣ በሀረሪ ሐብሊ 18 እና ኦህዴድ 18 በማግኘት ማሸነፋቸው ታውቋል፡፡
በዘንድሮው ሀገራዊ ምርጫ ለ547 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች 52 የፖለቲካ ፓርቲዎች እና 9 የግል እጩዎች ናቸው የተወዳደሩት።
ለመራጭነት ከተመዘገበው ህዝብ ውስጥ ከ34 ሚሊዮን በላይ ህዝብ (93 በመቶ) ድምጽ መስጠቱ ታውቋል፡፡
ምንጭ፣ኢብኮ
like
EHADEG silashenefe betam des bilognal
so lie!