“አጋጣሚ ነው ግን….?”

Psychology of Coincidence

Psychology of Coincidence

“አጋጣሚ ነው ግን….?”

(ሳም አለሙ)

አንዳንድ ጊዜ “እንዴት ሊሆን ቻለ?” በሚል ጥያቄና ግርምት እንድንዋጥ የሚያስገድዱን አጋጣሚዎች ይፈጠራሉ…ለምሳሌ አሞኛል ብለን(የእውነት አሞን) ከአለቃችን ፍቃድ ወስደን ከስራ ቦታ ወደ ቤታችን እያመራን ነው እንበል..እንዳጋጣሚ ሆኖ ታዲያ ለረጅም ጊዜ ተለይቶን የቆየ ወዳጅ ጋር ተገጣጠምን…ይሄው ወዳጃችን ሳንገባበዝ አንፋታም በማለት “ግግም” ይላል…”ጥቂት አመም አርጎኝ ነው…” ብንለውም ወይ ፍንክች!!..ከቆይታ በኋላ ከካፌ ወይም ከሬስቶራንት ስንወጣ ታዲያ ከመሥሪያ ቤታችን አለቃ ጋር መላተም! ልብ በሉ ሰውየው ከዚህ ቀደም እዚያ አካባቢ በዚያ ሰዓት ላይ ተከስቶ አያውቅም!… አለቃችን ወዲያው ምንድነው ሚያስበው? እንደዋሸነውና ከዚህ በኋላ የሆነ ምክንያት አቅርበን ፍቃድ ብንጠይቀው ሊሰጠን እንደማይገባ ይወስናል…እዚህ ላይ ነው እንግዲህ ጥያቄዬ…ነገሩ እንዴት ሊሆን ቻለ? ከዚህ ቀደም በዚያ ሰዓት ከስራ ቦታው የማይወጣው አለቃችን እንዴት ትዝብት ላይ በሚጥለን አጋጣሚ ሊከሰት ቻለ? እንዲህ አይነቱን “አጋጣሚ” የፈጣሪ ወይም የሰይጣን እጅ ከበስተጀርባው እንዳለበት አርገው ሚያስቡ አጋጥመውኛል…አባባላቸው ውሀ ባያነሳም ጉዳዩ አወዛጋቢ ነው።ሌላ ምሳሌም ልጥቀስ..ስለሆነ ሰው እያሰባችሁ መንገድ ላይ ዎክ እያደረጋችሁ ሳለ በድንገት ከዚያ ሰው ጋር ተገናኝታችሁ አታቁም? በርግጥ እንዲህ አይነቱን ክስተት ነጮች Telepath በማለት ባጭሩ ሊገልጹት ይሞክራሉ….የሆነ ሆኖ በበኩሌ እንዲህ አይነቱን “አጋጣሚ” እንዳጋጣሚ ብቻ ልወስደው አልቻልኩም…ሰፋ ያለ ትንታኔ የሚያሻው ጉዳይ ይሆን?!

3 thoughts on ““አጋጣሚ ነው ግን….?”

  1. እኔ በጣም ብዙ ግዜ ያጋጥመኛል የሆነ ሠው ለገኘው ከሆነ ድንገት አሥበዋለው

  2. የተባሉት አጋጣሚዎች ሁሉ የሰይጣን ወይም ሌላ ቅንብር አይደሉም:: ይልቅ ደጋግመን የምናስባቸው ነገሮች ዕውን ይሆናሉ በThe Secrete ላይ እንደተጠቀሰው:: አሞኛል ብሎ ከቢሮ የወጣው ሰው ሻይ አየጠጣ ደጋግሞ ስለ አለቃው ጉዳይ ያስብ ነበር ማለት ነው:: ስለሆነም ተገናኙ:: በቃ እውነታው ይህ ነው::

Leave a Reply

Your email address will not be published.