አዲሱ የኤር ባስ ምርት በኢትዮጵያ የተሳካ የበረራ ሙከራውን አደረገ

ህዳር 01፣ 2008

በስሬቱ የመጀመሪያ የሆነው ኤር ባስ A350 XWB በኢትዮጵያ የተሳካ የሙከራ በረራውን አደረገ።

አውሮፕላኑ በዱባይ የነበረውን ተማሳሳይ ትዕይት አጣናቆ  ዛሬ ህዳር 01፣ 2008 ረፋድ በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የበረራ  ሙከራውን ለማድረግ ነው አዲስ አበባ  የተገኘው።

ኤር ባስ A350 XWB አውሮፕላን ከሌሎቹ የኤር ባስ አውሮፕላኖች ሰፊው መሆኑ ይነገርለታል።

መቀመጫውን በፈረንሳይ ያደረገው ኤርባስ በአሁኑ ወቅት በአለማችን ከ41 ደንበኞቹ የA350 XWB አውሮፕላን ግዥ ጥያቄ እንደቀረበለት አስታውቋል።

ኩባንያው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያቀርበውን A350-900 አውሮፕላንም ገጣጥሞ እየጫረሰ መሆኑን  ቀደም ብሎ ገልጿል።

በጎርጎሮሳዊያኑ 2016 መግቢያ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዱሱን ምርት ከኤር ባስ ይረከባልም ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቦይንግ ኩባንያ 787 ድሪምላነር አውሮፕላንን አዞ ቀድሞ  በመረከብ ከአለም ሁለተኛ ከአፍሪካ  ደግሞ  የመጀመሪያ እንደሆነው ሁሉ ኤር ባስ A350ን በማስገባት ከአፍሪካ ቀዳሚው አየር መንገድ ያደርገዋል።

የአየር መንገዱ ከኤር ባስ ያዘዛችውን 14  አውሮፕላኖች በአራት አመት ውስጥ ሙሉ  ለሙሉ እንደሚረከብም የኢትዮጵያ  አየር መንገድ አመልክቷል።

ሪፖርተር፣ ስለሺ  ዳቢ

ምንጭ፦ ኢብኮ

1 thought on “አዲሱ የኤር ባስ ምርት በኢትዮጵያ የተሳካ የበረራ ሙከራውን አደረገ

  1. woww really really Ehtiopian airline I am proud of you!!! We are the leader of that is whey everything is tasted by Ethiopiand we are never and ever colonised !!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.