አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ ልባቸው ወደ ሩዋንዳ ሸፍቷል

Mariano Barreto
አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ ልባቸው ወደ ሩዋንዳ ሸፍቷል

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ የሩዋንዳ ብሄራዊ ቡድንን ለማሰልጠን ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።

ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ የሩዋንዳ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ስቴፈን ኮንስታንታይን መልቀቃቸውን ተከትሎ ነው ቡድኑን ለማሰልጠን ፍላጎታቸውን ያሳዩት።

በግንቦት ወር 2006 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ለማሰልጠን የተቀጠሩት ማሪያኖ ባሬቶ በወር 18 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ይከፈላቸዋል።

አሰልጣኙ እስካሁን ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጋር ባደረጉት ቆይታ ሰባት ኢንተርናሽናል ጨዋታዎችን ያደረጉ ሲሆን፥ አምስት ጨዋታዎችን ተሸንፈው፤ በአንድ ጨዋታ አቻ እንዲሁም አንድ ጨዋታ አሸንፈው ዝቅተኛ ውጤት አስመዝግበዋል።

አሰልጣኙ ባለፈው ሳምንት እሁድ ከ23 አመት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን እየመሩ ድሬዳዋ ላይ ያደረጉትን ጨዋታ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት መሸነፋቸው ይታወሳል።

– Source: FBC

Leave a Reply

Your email address will not be published.