አሰላለፍ ይፋ ሁንዋል፡–5ት ለዉጦች…ጋዜጠኞች መጡ!!

ተከላካይ ክፍሉ ላይ ከሊቢያዉ ጨዋታ የቀሩት አበባዉ እና ጀማል ብቻ ናቸዉ፡፡ያዉ በረኛም ስራዉ ግብ እንዳይጋ መከላከል ስለሆነ ነዉ፡፡

በስዩም ቦታ አሉላ ገብተዋል፡፡በአይናለም እና ደጉ ቦታ ደግሞ ሳላሀዲን ባርጌቾ እና ቢያድግልኝ ኤልያስ ሊብሮዎች ሁነዋል፡፡

አማካዩ እንዳለ ነዉ፡-አስራት እና አዳነ ተጣምረዋል፡-በመቀየሬ ስህተት ሰርቻለሁ ያሉትን ቱሳን ዛሬ በቀኝ በኩል ሲጫወት ምንያህለ በግራ አማከይ ነዉ፡፡

መሳይ (ፋሲካ) አስፋዉ እምብዛም ባልተለመደ ቦታ ከአጥቂ ጀርባ ይጫወታል፡፡ኡመድ ኡክሪ ብቸኛዉ አጥቂ ነዉ!!

ጨዋታዉ ምሽት 3ሰአት በኢትዮጵያ አቆጣጠር ይደረጋል፡፡ኮንጎ አሰልጣኙ በሰጡት መግለጫ ምንም ጉዳት እንደሌለባቸዉ ገልፀዋል፡፡ከመጀመሪያ የጋና ጨዋታቸዉ በፊት ተጫዋቾቹን አላቃቸዉም ያሉት ፈረንሳዊ አሰልጣኝ ዛሬ ካላሸነፍን እንወድቃለን ስለዚህ ጠንክረነወ ለመጫወት እንሞክራለን ብለዋል፡፡

የዋልያዉ አሰልጣኝም የሞት ሽረት ጨዋታ እንሆነ ገልፀዋል፡፡ክፍት ቦታዎችን ሞልተናል አሁን ለማሸነፍ ነዉ የምንገባዉ ብለዋል፡፡

ጋዜጠኞች ዛሬ ደርሰዋል፡፡መሸሻ ወልዴ–ሁሴን አብዱልቀኒ እና ደረጀ ጠገናዉ ብሎምፎንቴን ተገኝተዋል፡፡ትላንት ነበር ጆበርግ የገቡት!!እንገዲህ የዋልያዉን ጉዞ እየተከታተልን ማቅረቡን ቀጥለናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.