አሰላለፍ ከካላባር ታወቀ!

 

ግብ ጠባቂ…ሲሳይ ባንጫ

ተከላካዬች—አሉላ ግርማ….አይናለም ሀይሉ….ሳላሀዲን ባርጌቾ…አበባዉ ቡታቆ

አማካይ—ሽመልስ በቀለ…አዳነ ግርማ…አስራት መገርሳ…ምንያህል ተሾመ

አጥቂ— ጌታነህ ከበደ…… ሳላሀዲን ሰኢድ

በመጨረሻዉ የደቡብ አፍሪካ የዋልያ ጨዋታ ከናይጄሪያ ጋር ሲደረግ ጀማል ፤አስራት ና አዳነ በቅጣትና ጉዳት ምክነያት አልተሰለፉም ነበር፤ዛሬ አዳነ እና አስራት ይገባሉ፤ከሜዳ ዉጭ ሁነዉ ቁጭታቸዉን ሲገልጹ የነበሩት ተጫዋቾች አሁን አድሉን አግኝተዋል፤ ሲሳይና ሞሰስ አሁን ከ10ወራት በሁዋላ ተገናኝተዋል፤ሲሳይ በዛ ጨዋታ ላይ በቀይ ካርድ የወጣበት ምክነያት ሞሰስ ነበር፤አሉላም ከሞሰስ ጋር ዛሬ ይፋለማሉ፤ ሳላሀዲን ሰኢድ ዛሬ ናይጄሪያ ላይ ጎል እንደሚያገባ ተናግረዋል፤ ናይጄሪያዎቹ መንገድ ላይ የሚያወሩት ነገር ሌላ ነዉ፤ለምን መጣችሁ…ጨዋታ አለ እንዴ የሚሉ ብዙ ናቸዉ፤ካላበር እግር ኳስ የሚታወቅባት ከተማም አትመስልም፤ ናይጄሪያ ዋልያዉን ከገጠመ በሁዋላ ሰኞ ከጣሊያን ጋር በለንደን ይጫወታል፤በዚህ ጉዳይ ኬሺ እንደሰጋ አብራርትዋል፤በጉዞ ሳቢያ የመጉላላት እና የመርፈድ ችግር እንዳይኖር በሚል ነዉ፤ ዋልያዉ አሁን ከደቂቃዎች በሁዋላ ወደ ስታድየም ያመራል፤ምሳ ተበልቶ አሰላለፍ ተነግሮ አልቅዋል፤የሳይኮሎጂ ባለሙያዉም ስራዉን አጠናቅዋል፤ ስታድየም እንገናኝ!!

7 thoughts on “አሰላለፍ ከካላባር ታወቀ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.