አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ ማን ናቸው ?

Amb Sahlework Zewde 1

በአፍሪካ ‹‹አስታሪቂዋ ዲፕሎማት›› ተብለው በክብር ሥማቸው ይጠራሉ::

ፈረንሳይ በሚገኘው ሞንቲፕሌር ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርታቸውን የተከታተሉት አምባሳደር ሳህለወርቅ አማርኛ፣ ፈረንሳይኛና እንግሊዝኛ ቋንቋን አቀላጥፈው መናገር ይችላሉ፡፡

አምባሳደር ሳህለወርቅ በአምባሳደርነትና በተለያዩ ሀላፊነቶች በታላላቅ አለማቀፋዊ ተቋማት አገልግለዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ፡-

• በአሁኑ ሰዐት በአፍሪካ ህብረት የተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ልዩ ረዳት እና በአፍሪካ ህብረት የተባበሩት መንግስታት ሀላፊ

• ከ 1989-1993 በሴኔጋል፣ ኬፕቨርዲ፣ ጊኒቢሳው፣ ጋምቢያና ጊኒ የኢትዮጵያ አምባሳደር

•ከ 1993-2002 በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደርና የኢጋድ ቋሚ መልዕክተኛ

• ከ 2002-2006 በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር፣ በዩኔስኮ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ እና የቱኒዝያና ሞሮኮ ተጠሪ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ የተባበሩት መንግስታት የተቀናጀ ሰላም ግንባታ ቢሮ ልዩ ተወካይና ሀላፊ ሆነውም ሰርተዋል፡፡

አምባሳደር ሳህለወርቅ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን እና በአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ እንዲሁም በኢፌዲሪ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ጀነራል ዳይሬክተር በመሆን በከፍተኛ ሀላፊነት ሰርተዋል፡፡

በ2011 በናይሮቢ የተባበሩት መንግስታት ቢሮ ዳይሬክተር ጄኔራል በመሆን በወቅቱ የተመድ ዋና ፀሀፊ ባን ኪ ሙን ተሹመው ያገለገሉት አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ከዋናና ምክትል ዋና ፀሀፊነት ቀጥሎ ያለውን ከፍተኛ የአመራር እርከን ያገኙ የመጀመሪያዋ ሰውም ናቸው፡፡
ምንጭ:- የኢትዮጵ ፕሬስ ድርጅት