ናይጄሪያዊያን ቃላቸዉን ጠብቀዋል…የጥብስ ፍርፍር ያለህ በካላባር – ቴዲ አፍሮ….ፊደል ሬስቶራንት-ምን እንታዘዝ!?

 

ዋልያዉ ካላበር ጥሩ መስተንግዶ ተደርጎለታል፤ቻርተር አይሮፕላኑ እንዳረፈ የቀድሞዉ የአዲስ አበባ ከንቲባ የአሁኑ አምባሳደር አሊ አብዶ አቀባባል አድርገዉለታል፤ከዛም ወደ ሆቴል ተጉዞ ከሰአታት እረፍት በሁዋላ የመጀመሪያዉን ልምምድ ሰርትዋል፤ከዋልያዉ ጋር በቀጥታ በራራ ጋር አብሮ የተጉዋዙት ጋዜጠኞች የቲቪዉ ማንደፍሮ ታደሰ ና የፋናዉ ዮናስ አዘዘ ናቸዉ፤እነሱም ናይጄሪያዎች ቃላቸዉን እንደጠበቁ ተናግረዋል፤ምንም አይነት መጉላላት እንዳልነበረ ሆቴሉም ደረጃዉን የጠበቀ ባለ 5ት ኮከብ እንደሆነ ተነግርዋል፤ ዛሬ የመጀመሪያ ልምምድ በካላበር ዩኒቨርስቲ ሜዳ ተደርግዋል፤ብዙዎች እንደጠበቁት ሙቀቱ አስፈሪ አይደለም፤ነገር ግን ወበቁ ከፍተኛ መሆኑ ተነግርዋል፤ዛሬ አዲስ አበባ በሚገኘዉ ናይጄሪያ ኢምባሲ የሰማሁትም ይህንን የሚያረጋግጥ ነዉ፤”ልክ እንደአዲስ አበባችሁ ነዉ አየሩ…እንደዉም በጣም ልመላሜ ያለባት ከተማ ነች፤ሊያስቸግር የሚችለዉ ለመተንፈስ የሚከብድ አየር መኖሩ ነዉ”ምክትል አምባሰደሩ ነግረዉናል፤ ጨዋተዉ ካላበር መደረጉ ዋልያዉ በጣም ተጠቃሚ ነዉ ባይ ናቸዉ ሰዉየዉ..ሌጎስ ወይም አቡጃ ትእግስት የለሌለዉ በኳስ ያበደ ደጋፊ ባለቤቶች ናቸዉ፤ካላባር ግን ረጋ ያሉ ግን ደሞ በድጋፋቸዉ የማይታሙ ናቸዉ፤አንድ ሰዉ የሌጎስ ልጅ ነኝ ሲል እንደአዲስ አበባዉ ዶሮ ማነቂያ አልያም የጨርቆስ ልጅ ነኝ እንደማለቱ ነዉ…ይህንን የሚሉት ናይጄሪያዊዉ ሰዉ ናቸዉ!! ዛሬ 30ደጋፊዎች በቻርተር አይሮፕላኑ ከተለያዩ ሀገራት አምርተዋል፤የኢምባሲ ምንጮቼ እንደነገሩኝ ከካናዳ…ጀርመን..ዱባይ..ደቡብ አፍሪካ የመጡ ኢትዮጲያዉያን ወደ ካላባር አምርተዋል፤ዘፋኙ ቴዲ አፍሮም ከነ ባለቤቱ እዛዉ ይገኛል፤ታደለ ሮባም ካላባር ገብትዋል፤እናላችሁ ካላባር እንጀራ የለ ምን የለ…ሁልዋም ወደ አዲስ አበባ እየደወለች ማዘዝ ጀምራለች፤የፊደል ሬስቶራንት ባለቤት ኤፍሬም ኤርሚያስ ነገ ወደ ካላባር ያመራል፤እስከምሽቱ 4 ሰአት ብቻ 16 ምግቦችን ከካላባር በስልክ ታዝዋል፤ጥብስ ፍርፍር እና የፆም በየአይነቱ የአንበሳዉን ድርሻ ይወስዳሉ…ቴዲ አፍሮም ለነገ አርብ የፆም ለከነ ወዲያ የፍስክ ምግብ አዝዋል፤ካላባር ያላችሁ ያማራችሁ ነገር ካለ ከጥዋት በፊት ተናገሩ..4ሰአት ላይ መብረራችን ነዉ(የፊደል ሬስቶራንት አስተናጋጅ) በዋልያዉ አሰላለፍ ዙሪያ ለዉጦች እንደሚኖሩ ፍንጮች አሉ፤ከበረኛ ጀምሮ በተከላከይ ቦታ ላይ አንዲሁም የመሀል ክፍሉ የመቀያየር ነገር እንደሚኖረዉ የዉስጥ አዋቂ ምንጮች ይጠቁማሉ፤ስዩም ተስፋዬ በ2ት ቢጫ ቦታዉን ለአሉላ አስረክብዋል፤በስሱ ጉዳት ላይ የነበረዉ ደጉ ደበበ ከህመሙ አገግሞ በዛሬዉ ትሬኒንግ ተሰልፈዋል፤ምናልባት ግን ከ2ቱ ሊብሮዎች አንዱ መቀየሩ እንደማይቀር ይጠረጠራል፤ቢያድግልኝ ኤልያሥ በአንዱ ቦታ ታስብዋል፤ አማካይ ክፍሉ ላይ ልክ እንደደቡብ አፍሪካዉ ጌታነህ በቀኝ አዘንብሎ ሊጫወት ይችላል፤አዳነ ወደ ፊት አጥቂነት ሽመልስ ከአጥቂ ጀርባ የአስራት አጣማሪ ደግሞ ቱሳ…ነዚህ ግምቶቸ ናቸዉ…ከነገ በስቲያ ሲለይ ቀድሜ እንግራችሁዋለሁ!! ዛሬ በቀጥታ በቻርተሩ ካላባር ያመሩ አጠቃላይ የዋልያ ሰዎች 60 ናቸዉ፤በተለያዩ መንገዶች የሚመጡ ሰዎችም ነገ መንገዳቸዉን ይቀጥላሉ፤ብዙ ጋዜጠኞችን የያዘ ቡድን ነገ 4ሰአት ላይ ወደ ኢኑጉ ከተማ ይበራል፤ከዛም የ2ት ሰአት የመኪና መንገድ በሁዋላ ካላበር ይደርሳል፤እዚህ ቡድን ዉስጥ ደርቢዎቹ ታዲያሥ አዲስ እና ኢትዮፒካ ሊንክ(ሰይፋ ፋንታሁን፣፣ታደለ አሰፋ—–ዮናስ ሀጎስ…)ይገኛሉ፤ከቲቪም አንድ ሰዉ አለ፤የታዘዙትን ምግቦችን ይዞ ኤፍሬም ኤርሚያሥ ዋልያዉን ለመደገፍ አብሮ ይጓዛል..እዛዉ በልተዉ እንዳይጨርሱበት እንጂ….የነገ ሰዉ ይበለን!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.