በጋና አደጋ የደረሰበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዕቃ ጫኝ አውሮፕላን የአደጋ መንስኤ ምርመራ ጊዜያዊ ሪፖርት ይፋ ሆነ

EAL Acra Accident - 1

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጋናው የኮቶካ አውሮፕላን ማረፊያ ባለፈው ወር መጠነኛ አደጋ የደረሰበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዕቃ ጫኝ አውሮፕላን የአደጋ መንስኤ ምርመራ ጊዜያዊ ሪፖርት ይፋ ሆነ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዕቃ ጫኝ አውሮፕላን በጋናው የኮቶካ አውሮፕላን ማረፊያ ባለፈው ወር መጠነኛ አደጋ ደርሶበት እንደነበር ይታወሳል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዕቃ ጫኝ አውሮፕላን አደጋ አጣሪ ቡድን 

የአደጋውን ዋንኛ መንስኤ የሚያመለክት ዝርዝር ሪፖርት በጊዜያዊ ሪፖርቱ አለማካተቱም ነው የተጠቀሰው።

የቀረበው የባለ 16 ገፅ ሪፖርት አደጋው በወቅቱ የነበረው መጥፎ የአየር ሁኔታ ለእይታ አስቸጋሪ በመሆኑ ሊከሰት መቻሉን ጠቅሷል።

የአደጋው አጣሪ ቡድኑ ሰብሳቢ ካፕቴን ሳሙኤል ቶምሰን የአደጋውን መንስኤ የሚዘረዝረው ሙሉ ሪፖርት በግንቦት ወር ይፋ አንደሚደረግ ገልፀዋል።

የበረራ ቁጥሩ ኢቲ- ኤ ኪው ቪ የሆነው ቦይንግ 737 400 የኢትዮጵያ ዕቃ ጫኝ አውሮፕላን ባለፈው ወር ነበር ከሎሜ ወደ አክራ አቅንቶ ለማረፍ ሲሞክር የመንደርደሪያ ቦታውን በመሳቱ በኮቶካ አውሮፕላን ማረፊያ አደጋው የደረሰበት።

በአደጋው ሶስት ሰዎች ተጎድተው በአክራ በሚገኝ ሆስፒታል ህክምና እንደተደረገላቸው ይታወሳል።

ምንጭ:- ፋና

4 thoughts on “በጋና አደጋ የደረሰበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዕቃ ጫኝ አውሮፕላን የአደጋ መንስኤ ምርመራ ጊዜያዊ ሪፖርት ይፋ ሆነ

Leave a Reply

Your email address will not be published.