በቤቱ ጉዳይ ዋልያዉ ቅር ተሰኝትዋል፡–ዲክሎፌናክም ጥያቄ ተነሳባት???

vitz

ያቺን ቀን በፍጹም ልረሳት አልችልም፡፡ያቺ ወጣት ሴት ያለችኝ ነገር በርግጥም ልብ ይነካል፡፡”ሚግን እኔ ነኝ ሞቶ ያገኘሁት፡-ሬሳዉን አጣጥቤ ከፍኜ ያስቀበርኩትም እኔ ነኝ፡-ከዛ ወዲህ አይደለም ስለኳስ ላወራ የሚያወሩ ሰዎች አጠገቤ ካሉ መሸሽ ጀምሬያለሁ፡፡የተረፈኝ ነገር ቢኖር የሚግ ልጅ የሚል ተቀጽላ እና ህይወቴ ሙሉ ከአእምሮዬ የማይወጣ ሀዘን ነዉ”ይህን ያለችኝ የሚግ ልጅ ነች፡፡

ሚግ ማለት አዳነ ግርማ አልያም ሳላሀዲን ሰኢድ ማለት ነዉ፡፡ለአፍሪካ ዋንጫ ከ32 አመታት በፊት ዋልያዉ ሲያልፍ እጅግ አስፈላጊዋን ወሳኝ ግብ ያስቆጠረ አጥቂ ነዉ፡፡ከሀገሪቱ መንግስት ፕሬዝዳንት እጅም የወርቅ ቀለበት ተሸልምዋል፡፡ግን ሚግ ስራ አጥቶ ክብር ተነፍጎት ህይወቱ ያለፈዉ መንገድ ዳር ላይ ነዉ፡፡

ይህን ነገር በኛ ዘመን ተጫዋቾች ላይ ለአንድአፍታ አስቡት፡-እንዴት መሆን የማይገባዉ ነገር እንደሆነ ዉስጥዎ ይነግርዋታል፡፡እናም የዋልያዉን መለያ የለበሰ ሁሉ ክብር ይገባዋል፡፡ዉጤት ያምጣ አያምጣ ሌላ ጉዳይ ሁኖ በእግር ኳስ ሀገሩን በመወከሉ ብቻ ክብር ይገባዋል፡፡

ዋልያዉ በደቡብ አፍሪካ ልምምድ የሚሰራበት ሜዳ የሴልቲክ ብሎምፎንቴን ነዉ፡፡የዚህ ቡድን ኳስ አቀባይ እንኳን (የዋልያዉ ጀሚል እኩያ) ዘናጭ መኪና አለችዉ፡፡ስራዉን እንደጨረሰ ሁሉም የመኪና በር ተከፍቶ ይጠብቀዋል፡፡እናም አስነስቶ ላጥ ይላል፡፡

በኢትዮጲያ እግር ኳስ በተለይም ከዚህ በፊት እግር ኳስ ጥቕም የማይገኝበት መብት የማይከበርበት ሙያ ሁኖ ቆይትዋል፡፡ለሀገር ድንቅ ዉለታ ያበረከቱ ሰዎች መንገድ ዳር አዳሪ ሁነዉ ህይዋታቸዉን አጥተዋል፡፡

መረጃ ይበራል ቢባል ቀላል ነዉ፡፡አሁን ከብሎምፎንቴን እና ከአዲስ አበባ ቀድሞ የት መረጃ ይደርሳል ብትሉኝ ያለ ጥርጥር ደቡብ አፍሪካ ነዉ መልሴ ከትላንት ወዲያ አንድ ሸገር ላይ ባለ ሬድዬ ጣቢያ ለዋልያዎቹ እንዴት መኪና እያላቸዉ ቤት ይጠይቓሉ በሚል መነገሩ ተጫዋቾቹንና አባለቱን ክፉኛ አሳዝንዋል፡፡

መኪና ቤት ይሆናል ወይ ከሚሉት አንስቶ እንዴት ይህን መሰል ነገር ለዉይይት ይቀርባል እስከሚሉት ድረስ ነገሩ አወያይትዋል፡፡በምንም መመዘኛ ቡድኑ ላይ የተሰለፉት ተጨዋቾች ሽልማት ቢሰጣቸዉ ሆነ ኮንዶሚንየም ቤት ቢያገኙ ተጠቃሚዉ እነሱና ቤተሰቦቻቸዉ ብቻ አደሉም፡፡ክብሩ ለመላዉ የእግር ኳስ ተጫዋቾችም ጭምር ነዉና፡፡ከዚህም በላይ ነገ እግር ኳስ ተጫዉቼ ሀገሬን ወክዬ አወክላለሁ ለሚለዉ ወጣት ጥሩ ሞራል ይሆናል፡፡

በነገራችን ላይ የዋልያዉ ተጫዋቾች መኪና የሌላቸዉ ጥቂቶች ናቸዉ፡፡በገዙት መኪና ለመሄድ ብለዉ ይሆናል፡፡አብዛኞቹ ቪትዝ ናቸዉ፡፡እናም መኪኖቹ ”ከ31 አመት በኋላ” የሚል ስያሜ ተሰጥትዋቸዉ ነበር፡፡ጥቂት ቆይቶ ደግሞ ከይሳቅ ወጌሻዉ የምትሰጠዉን የሁሉም በሽታዎች ማስታገሻ “ዲክሎፌናክ“በሚል እየተጠራች ነዉ፡፡አሁን ከቻን በኋላ ደግሞ የሚወጣለትን ስም እንጠብቃለን፡፡

ሙሉጌታ ከበደ ታሪካዊ ተጫዋች ነበር፡፡ካቆመ በኋላ ተቸግሮ ነበር፡፡ተስፋዬ ኡርጌቾም እንደዛዉ….ሙሉጌታ ወልደየስ ሲጎዳ መታከሚያ ከህዝብ ነዉ የተዋጣዉ፡፡ብዙዎች በችግር ህይወታቸዉን አጥተዋል፡፡ያ ነገር ዛሬ አለመደገሙን ማረጋገጥ ግድ ነዉ፡፡”ልጄ ተጫዋች እንዲሆን አልፈልግም” የምትል እናት እነዳትኖር!!!

ለማንኛዉም ትጥቅ ያዥ የያዠዉን መኪና ተጫዋቾች መያዛቸዉ እጅግ ያንሳል፡፡ቤቱም ቢሆን ካገለገሉት አኳያ ይገባቸዋል፡፡ዲክሎፌናክ መጓጓዣ እንጂ ማደሪያ አትሆንምና!!!

3 thoughts on “በቤቱ ጉዳይ ዋልያዉ ቅር ተሰኝትዋል፡–ዲክሎፌናክም ጥያቄ ተነሳባት???

  1. shelematuma keserut tarikawi sera antsar yansachewal bay negn yebelete tekemetaw degemo tadgiwoch yehen eyayu endiberetatu yadergachewal selezih beta asfelagi new bay negn

  2. tnx for sharing seya. it is very touching. i just remembered “wey hagere Ethiopia mogn nesh telala..yemotelish sayhon yegedelesh bela”.

Leave a Reply

Your email address will not be published.