በሪዮ ኦሎምፒክ ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ ያስገኘው ፈይሳ ሌሊሳ ወደ አገሩ ቢመለስ ችግር እንደማይገጥመው አቶ ጌታቸው ረዳ ለፋና ገለጹ

Feyisa_Lelisa_RIOEC8L1LFJBD_768x432

በሪዮ ኦሎምፒክ በወንዶች ማራቶን ሁለተኛ ወጥቶ ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ ያስገኘው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ አገሩ ሲመለስ ምንም ችግር እንደማይገጥመው መንግስት አረጋገጠ።

የኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙዩኒኬሸን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፥ ለአገሩ የብር ሜዳሊያ ያስገኘው ይህ አትሌት በፖለቲካ አቋሙ ምክንያት የሚደርስበት ነገር አይኖርም።

ምንም እንኳ በኦሎምፒክ ህግ በመድረኩ የፖለቲካ አቋምን ማንፀባረቅ ባይፈቅድም፥ አትሌቱ ወደ አገሩ ሲመለስ ከሌሎቹ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን አባላት ጋር ጥሩ አቀባበል ይደረግለታል ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ የሪዮ ኦሎምፒክ ተሳትፎዋን በ1 የወርቅ፣ በ2 የብር እና በ5 የነሃስ በአጠቃላይ በስምንት ሜዳልያዎች ማጠናቀቋ ይታወቃል።

ውጤቱን ተከትሎም ከአለም 44ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 3ኛ ደረጃን ይዛለች።

ምንጭ:- ፋና

2 thoughts on “በሪዮ ኦሎምፒክ ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ ያስገኘው ፈይሳ ሌሊሳ ወደ አገሩ ቢመለስ ችግር እንደማይገጥመው አቶ ጌታቸው ረዳ ለፋና ገለጹ

Leave a Reply

Your email address will not be published.